2011-03-03 11:31:51

የር.ሊ.ጳ የዕለተ ሮቡዕ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (02.03.11)


ኤፈ. 4፣32 ‘እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።’

(በጣልያንኛ ቋንቋ ያቀረቡት ኣስተምህሮ)

ውድ ወንድሞቼና ኣኅቶቼ!

የዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ከትረንቶ ጉባኤ በኋላ በነበረው ግዜ የኖረ የመንፈሳዊ ሕይወት ኣስተማሪና ተወዳዳሪ ያልነበረው ጳጳስ ስለ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ይናገራል። በወጣትነቱ ባጋጠመውና ባጣጣመው ነጻነት የሚሰጥ የእግዚአብሔር ፍቅር ለክህነት ጥሪ ኣብቅቶት መጀመርያ ካህን ከዛም የጀነቫ ጳጳስ ሆነ። ያኔ ጀነቫ የካልቪኒዝም ፀረ ማርያም እንቅስቃሴ ቅድመ ግንባር ነበረች። በነበረው የትምህርት ብስለት የግሉ የርኅራሄና የግብረ ሠናይ ሥጦታ እንዲሁም ለውይይት በነበረው ክፍትነትና የመንፈስ እርጋታ እና እንደ መፈሳዊ መሪ በነበረው ኣስደናቂ ብልኅነት የዘመኑ ኮከብ መሪ ኣደረጉት።

ከመፈሳውያን ጽሑፎቹ ብዙ ኣድናቆት ያተረፈው ‘ለመንፈሳዊ ኑሮ መግቢያ’ የሚል ይገኝባቸዋል። መጽሓፉ የሚያስተምረው እያንዳንዱ ክርስትያን ባለበት የሕይወት ኑሮ ለፍጽምና የተጠራ መሆኑን ያስምርበታል። ይል ኣባባል ከብዙ ዓመታት በኋላ ሁለትኛው የቫቲካን ጉባኤ ያቀረበው የሁሉ ሰው የቅድስና ጥሪ ኣስቀድሞ የተመለከተ ነው። ሌላው ጽሑፍ ደግሞ ‘በእግዚአብሔር ፍቅር ላይ ሐተታ’ በሚል ርእስ የተዘጋጀ ሲሆን ገዛ ራሳችንና እውነተኛ ነፃነታችንን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ እናገኛለን በማለት ያስተምራል። የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘሳለስ ሰብአዊና ክርስትያናዊ ትምህርት ዛሬም ቢሆን ገና ብቁ ትምህርት ነው። የዚሁ ታላው ቅዱስና የቤተ ክርስትያን ሊቅ ቅድስናን ለማግኘት እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍቅር በመወለዳችን የሚገኝ ደስታችንና ፍቅራችን እንድናገኝ ይርዳን።

(በእንግሊዘኛ ቋንቋ ያቀረቡት ኣስተምህሮ)

ውድ ውንድሞችና እህቶች፣ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ ‘የእግዚአብሔር ፍቅር ሐተታ’ በሚለው መጽሓፉ ‘እግዜአብሔር የሰው ልጆች ልብ አምላክ ነው’ ይላል። በእነዚህ ቀለል ባሉ ቃላት መንፈሳዊና የፍቅር ይዞታ አገላለፅ የሚያስተምረንን ቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳለስ ትልቁ የቤተክርስቲያን መምህር ላስታውስ እፈልጋለሁኝ።

ቅዱሱ በፈረንሳይ ሃገር በ1567 ዓም ተወለዱ። ቤተሰባቸው በግዜው ከነበሩት የሳቮያ ልዑላን የሚወለዱ ሲሆኑ እነሱም በአምተኛውና በስድተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ ከነበሩት ሲሆን በዛን ግዜ ከነበሩት የእውቀትም ሆነ የባሕል ስነ ጥበብ ትምህርት ከፍተኛ ከቀሰሙት ውስጥ ናቸው። ከልጅነት ትምህርታቸው በኋላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በፈረንሳይ ዋና ከተማ በፓሪስ የቴኦሎጂ ትምህርት በመማር አጠናቅቀዋል። ወላጅ አባቻቸውም ይሹት እንደነበረው በጣልያን በፓዶቫ ዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርት በመማር በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቀዋል።

በወጣትነቱ ግዜ የቅዱስ አጎስጢኖስና የቅዱስ ቶማስ ዘአኲናስ የሕይወት ጥሪና ኑሮን በመጠመድና በማሰልሰል በራሱ የወደፊት የሕይወት ምርጫ ላይ ክርስቶስን አውቆ ለዘላለም መዳን የሚለው ቃል ለመንፈሳዊ ምርጫ በጣም የከበደውና ከራሱ ከእኔነቱ ጋር በዘመኑ በነበረው የቴኦሎጂ ትምህርት አመለካከት ጋር ብዙ መንፈሳዊ ውግያዎቹን እንደተዋጋ ያስተምረናል።

አጥብቆ በመፀለይ ግዜውን ቢያሳልፍም ነገር ግን ጥርጥር በውስጡ በመንፈሳዊ ውግያ ትግል ሲበዛበት ብዙ ግዜያትም ለመብላትም ለመጠጣትም ለመተኛትም ቢሆን ብዙ ችግር እንደነበረበት ያስተምረናል።

መንፈሳዊ ውግያው እማይችለው ደረጃ ደርሶ ሲጨነቅ በፓሪስ በሚገኘው የዶሜኒካን ቤተክርስቲያን በመግባት የፀለየውን ፀሎት ስንመለከት “ ምንም ነገር ቢደርስብኝ አምላኬ ሆይ ሁሉም ነገር አባት ሆይ በእጅህ ነው ያንተ መንገድ እውነትና ትክክለኛ ፍርድ ነው፡ አንተ በኔ ላይ የምትፈፅመውን ማንኛውንም ዓይነት ውሳኔ ….አንተ ምን ግዜም አባቴ ሆይ እውነተኛ ዳኛና መሓሪ አባት ነህ ….አፈቅርሃለሁ አምላኬ ሁሉ ግዜም በምህረትህ ተስፋ አደርጋለሁ ምስጋናዬም ለዘላለም ከአፌ አይለይም ኦ ጌታ ኢየሱስ አንተ ምንግዜ በዚህች በምኖርባት ምድር ተስፋዬና ደህንነቴ ነህ’ ብሎ ያሳረገውን ጸሎት በመጽሓፍቱ እናገኛለን።

የ20 ዓመት ዕድሜ የነበረው ወጣቱ ፍራንቼስኮ ከመንፈሳዊ ውግያ ነፃ በመሆን ሙሉ ሰላሙን በፊናው ከእግዚአብሔር ፍቅር ጋር በቀጥታ የተተሳሰረ እንደሆነና አምላኩን ለማፍቀር ለሚጠይቀው ጥያቄ በተዘዋዋሪ መልስ እንዲሰጠው በመጨነቅና በመጠየቅ ሳይሆን አምላክ እራሱ እንደሚሻውና እርሱ ግን ፍቅሩና እምነቱ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ ለሙሉ በመተው እንደሆነ ያስተምረናል።

ምንም እንኳን ወላጅ አባቱ የክህነት ምርጫውን አጥብቀው ቢቃወሙም የ ጥሪውን ታሕሳስ 18 ቀን 1593 መዓርገ ክህነት ተቀበለ። በ1602 ዓም የጂኔቭ ከተማ አቡን ሆነው ተሾመዋል።

በዛን ግዜ የጄኔቭ ከተማ የፕሮተስታንት ሃይማኖት ዋና ቅስቀሳ እምብርት የነበረች ሲሆን የአቡኑ ጽ/ቤት ከከተማው ወጣ ብሎ በተራሮችና በኮረብታ ላይ ትገኝ በነበረው ትንሽ ከተማ በአኔሲ ይገኝ ነበር።

አቡን ሆነው ያገለግሉ የነበሩበት ቦታ እንደተራራውና ኮረብታው ውበት ነዋሪውም ጥሩና አነስ ያለ ሲሆን ኑራቸውም የኑሮው ግፊትና ሂደት ውጣ ውረዱን ይመስል ነበር። በዛን ግዜ ቦታውን ሁኔታውን በመመልከት በጻፈው መጽሃፍ ላይ እግዚአብሔርን በሙሉ ፍቅሩና ውበቱን በነዚህ የተፈጥሮ ውብ ተራራዎች ላይ እንዳገኙት በዛ የሚኖሩ ልበ ንፁሃን በሙሉ ልባቸው እንደሚያፈቅሩትና እንደሚያመልኩት በተራራው የሚገኙ እንስሳዎች ሲራራጡ ማየትና የተራራው በረዶ ማየት ያለ ማረፍ እግዚአብሔርን ማመስገን ይመስላል ሲሉ ለናታቸው ለሻንታል በጥቅምት ወር 1606 ዓም በጻፉት ደብዳቤ ላይ እናገኛለን።

በህይወት ዘሙኑ ተግባሩ በፀሎቱ ደቀ መዝሙር አገልጋይ መምህር ፀኅፊ በመሆን ያቀረበው አስተዋፆ ሰፊ ሲሆን በተለይም በትሬንቶ በተካሄደው ጉባኤ ላይ በዘመኑ ይካሄድ በነበረው የሃይማኖት መስፋፋት ከፕሮቴስታንቶች ጋር በዘመኑ ከነበሩ ቴኦሎጂዎች ጋር በመነጋገርና ጥናት በማቅረብ በአውሮፓ ደረጃ ዲፕሎማሲን በመወከል የሃይማኖቶች ሕብረት በመክፈት አቢይ ሚናን ተጫውቷል።

ቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳለስ ካበረኸተው በቀዳሚነት አስተዋጾ የሚታወቀው አበነፍስ በመሆን ብዙ ነፍሳትን እግዚአብሔርን እንዲያውቁና ወደ እርሱ እንዲቀርቡ በማድረጉ ነው። ለወጣቷ ወ/ሮ ሻርሞዚ በፃፈው ‘ለምንኵስና ሕይወት መግቢያ’ በተሰየመው መጽሓፉ በዛን ዘመን ከተነበቡት መጽሓፍት አንዱ ሲሆን የሚያስተምረን የነበርቸውን መንፈሳዊ ውህደትን ነው። ይህም ከቅድስት ጆቫና ፍራንቼስካ ዘሻንታል ጋር የነበረውን መንፈሳዊ ትብብርና ሕብረት አዲስ የመንፈሳዊ ማኅበር መመስረትን ያስተምረናል።

ጆቫና ፍራንቼስካ ዘሻንታል ቅዱሱን ካወቀች በኋላ የሙንኩስና ሕይወትን ለመኖር በመምረጥ ቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳለስ በመሰረተው ገዳም ማኅበር ገባች። ሕይወታቸው እግዚአብሔርን በማገልገልና በትህትና በየቀኑ በሚኖሩት ማኅበራዊ ኑሮ ላይ በጎ በማድረግ ነው። በ1615 ሰኔ ወር ለአቡነ ማርክሞንድ በጻፉት ደብዳቤ ላይ ያቋቋሙትን የደናግል ማኅበርን መንፈሳዊ ልጆቻቸው በሕይወታቸው አምላካቸውን ብቻ እንዲያመልኩና በሙሉ ልባቸው እንዲያወድሱት እንደሚሹ ሲገልፁ በ1622 ዓ.ም. በ 55 ዕድሜያቸው ከዚ ዓለም በሞት ተለዩ።

ቅዱሱ የሕይወት ዘመናቸው ዕድሜ ምንም እንኳን አጭር ቢሆንም ቅሉ በሙሉ ጉልበት ግዜ ኅይልና ልብ እግዚአብሔርን በመፈለግና በማገልገል እንደሆነ እንማራለን።

ከዕውቀቱና ከቀለም ትምህርቱም አሁንም ቢሆን ከሱ የቀሰምነው ብዙ ትህምርቶችን እንማራለን። ከቅዱሱ ፍቅር፡ ደግነት ርሕራሄን ሲያስተምረን ጥንትም እንደነበረው ዛሬም የሚያስተሳስረን ባሕል አክብሮ ነፃነት ሕብረት ወዳጅነትን ያንፀባርቃል። በተለይም እለታዊ ኑሮውም በነዚኅ ላይ በማመርኮዝ እነዚኅ ቃላት ባለፈውም ሆነ ባሁኑ ስናዳምጣቸው በቅርቡ በቤተሰባችን ያደግንባቸው የታነፅንባቸው ቃላቶች ናቸው።

በፊሎቴላ በ1607 በጻፈው መጽሃፍ ላይ ሙሉ ለሙሉ እግዚአብሔርን በማገልገል በዘመኑ ለነበረው አመለካከትና አስተያየት አብዮተኛ ቢመስልም፣ መልዕክቱ ሙሉ በሙሉ ለእግዚአብሔር በመሰጠት በሕብረተሰባችን መኖር እንደሚቻልና እያንዳንዱም የራሱን ድርሻ በኅላፊነት መስራት እንዳለበትና በተለይም በትዳር ቤተመንግስትና በከተማና ከፍተኛ የስልጣን ቦታዎች የሚገኙትን ለማስተማር ነው= ከሁለት መቶ ክፍለ ዘመን በውኅላ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ልዮን 13ኛ የቅዱሱን ድርሰቶች በማንበብ የቤተክርስቲያን ሊቅ ብለው ሲሾማቸው ቅዱስም ተብለው እንዲጠሩ ካደረጋቸው ነጥቦች ከጻፈቸው መጽሃፍት ውስጥ እውነተኛ ምህረት የተባለው መጽሃፍ ቅዱሱ የጻፈው በዘመኑ ከተነበቡት ታዋቂ መጽሃፍት ነው፣ መጽሃፉ ከቤተመንግስት ጀምሮ በየወታደሩ ድንዃንና የፍርድ መስሪያ ቤቶችና ገበሬዎና አምራቾች ያነበቡት መጽሃፍ መሆኑ ይታወሳል፣

የቅዱሱን ጥናት በመመርኮዝ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ከክህነት ጥሪ ውጭ የሚኖሩትን ምዕመናንን ጥሪን ሲያቀርቡ ጥሪውም ሕይወታቸውን በቅድስና እንዲኖሩ ነው= በዘመናችችን መንፈሳዊነት የሕብረት ጸሎትን በማያያዝ በእግዚአብሔር ጸጋ አምላኩን እንዲያከብርና እንዲያገለግል ለካህናት ብቻ ሳይሆን ምእመናንም ጭምር መሆኑ ይታወሳል= ሌላውም በ1616 የእግዚአብሔር ፍቅር ሐተታ በሚል ኣርእስትበጻፈው መጽሓፍ ላይ በቴዮቲሞ ከተማ በመንፈሳዊ ዕድገት ለበሰሉ ክርስቲያኖች ባስተማረው ትምህርት ላይ ስንመለከት የሰው ልጅ አስተሳሰቡን በተመረኮዘ እውቀቱ ሳይሆን ሕሊናው ቢያዳምጥ ከተፈጥሮና ከአካባቢው ጋር የበለጠና የጠለቀ የተያያዘ ሲሆን ይሕም እንደ ሰማይ ከፍታ መንፈሳዊ እድገቱን የውስጡም ከልቡ ጥልቀት ጋር በማያያዝ ከፍታውን ማየት እንደሚቻል ሲያስተምረን አይናችንን ጨፍነን በዚህ መስመር ብናስብና ብናስተውል መልሱ ፍቅር መሆኑን ያስተምረናል= ፍቅር ከመንፈሳዊውም ሆነ ከአለማዊው ጋር አስተሳስሮ እንደሚያኖረን ያስተምረናል=

ከቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳልስ ሰውን አስመልክቶ የሰጠው ትንተና ዓለማችን እንድትማላ ካደረጋት አንዱ የሰው መፈጠር ነው፣ ለሰው ልጅ ፍጽምና የሚሰጠው መንፈስ ነው። ለመንፈስ ፍጽምና የሚሰጠው ፍቅር ሲሆን ለፍቅር ሙላት የሚሰጠው ደግሞ በጎነት ስለሆነ እነዚህ አስፈላጊዎችና የተሳሰሩ መሆናቸውን ኣስተምረዋል።

ቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳልስ በጻፋቸው መጽሃፍት ውስጥ በተለይም ለመንፈሳዊ እድገትና ትምህርት የሚያስተምሩን ሲሆን በነዚህ መጽሃፍት ውስጥ የእርሱ አገላለጥ የሰው ልጅ ከአምላኩ ጋር ያለውን የግሉን ግንኙነትና አምላኩ አባቱ= ጌታው= ትዳሩ= ግዋደኛው= ፍቅሩን ሲገልፅ እንደ እናት ፍቅር ልጅዋን የምትመግብ ብሎ ያስተምረናል=

እግዚአብሔር አባት ልጆቹን በፍቅር ብቻ እንደፈጠረን በሙሉ ነፃነት እንደ ሚያኖረን ነው= ምክንያቱም ፍቅር ማንንም አይገዛም አያስገድድም= ነገር ግን ፍቅር ትዕዛዝን አክብሮትን ሲገልፅ ከፍቅር የሚበልጥ ምንም ነገር እንደሌለና በፍቅር ውስጥ የሚገኘው ኅይል ከሁሉም የሚበልጥ መሆኑን ያስተምረናል=

ቅዱሱ ለእግዚአብሔር ፍቅር ከጻፋቸው መጽሃፍትና ደብዳቤች አንዱ ጥቅምት 14 ቀን 1604 ዓም ለቅድስት ጆቫና ዘሻንታል እኛ በሕይወታችን የምንመረኮዘው የምናደርገው በሙሉ በፍቅር እንጂ በግዳጅ እንዳልሆነ ትዕዛዛትን በፍቅር ማክበር ካለመታዘዝ መራቅና መፍራትን ነው። ሌላው አደራ በነጻነት መንፈስ እንዲኖሩ ሲሆን ይሕም አለመታዘዝን እንደማያጠቃልልና ነገር ግን ለመረጡት መንፈሳዊ ኑሮ ምርጫ እንዲኖሩበት ነው። ቅዱሱ ከተወልን መንፈሳዊ ዕድገት ሃብቶች በመመርኮዝ ሌሎች በዘመናችን እንደ ቅዱስ ጆቫኒ ዘቦስኮና ቅድስት ተሬዛ ዘለዚዩ እናገኛለን።

ውድ ውንድሞቼና እህቶቼ አሁን በምንኖርበት ሕብረተሰብ ብዙዎች ነፃነትን የሚፈልጉት በማመፅና በረብሻ ነው። በተለይም በአሁኑ ግዜ የዚኅ ቅዱስ ትምህርት መንፈሳዊና ሰላም ለደቀመዝሙሮቹ እውነተኛው የነፃነት መንፈሳዊ ሕይወት ፍቅርን አጠቃሎ ያስተማረውን መዘንጋት የለብንም። ቅዱስ ፍራንቼስኮ ዘሳለስ ለክርስቲያን ወንድሞች ሕይወቱ እውነተኛ ምስክርነትን ሲተውልን በቅኔው በግጥሙና በኖረው ሕይወት ያስተምረናል።








All the contents on this site are copyrighted ©.