2011-03-02 15:16:01

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለወንጌል ታማኞች በማኅበራዊ ፍትኅ እና በሰላም ጎዳና ተጓዦች


እ.ኤ.አ. በዚህ ትላትና በተገባው የመጋቢት ወር የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የጸሎት ሐሳብ የላቲን አሜሪካ አገሮች ለወንጌል ታማኞች እና በማህበራዊ ፍትኅ እና በሰላም ጎዳና ተጓዦች የሚል መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ። ይህ ሐሳብ እ.ኤ.አ. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በብራዚል በተካሄደው የመላ ላቲን አሜሪካ እና ካራይቢ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት RealAudioMP3 አምስተኛው ይፋዊ ጉባኤ ለመሳተፍ ለፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉዞ (ለወንጌል ታማኝ እና ማኅበራዊ ፍትኅ ማነቃቃት) መሪ ቃል እንደነበርም የሚዘከር ነው።

ላቲን አሜሪካ ለተጋረጠባት ማኅበራዊ ችግር ለመቅረፍ ለወንጌል ታማኝ የሆኑ ክርስትያኖች እንደሚያስፈልጉዋት ቅዱስነታቸው በተለያዩ ወቅት ከላቲን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ባካሄዱት ግኑኝነት በሰጡት መሪ ቃል በመደጋገም ያሉት ሐሳብ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ እ.ኤ.አ. ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም. የላቲን አመሪካ ጳጳሳዊ ድርገት አባላት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት፣ በላቲን አመሪካ እና ካሪቢያን ለመጪው የቤተ ክርስትያን ዕጣ ዕድል የክልሉ ክርስትያኖች የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የኖሩት የሕይወት ሥልት በጥልቅ መረዳት እና በመኖር እርሱም ያልተወሳሰበ ደስተኛ እና በጸና እምነት በጸሎት እና በቅዱሳት ምሥጢራት ሱታፌ በመግለጥ መኖር ወሳኝ መሆኑ በማብራራት፣ አክለውም ካለ መታከት የሰው ልጅ ክብር ለማኅበራዊ ባህላዊ እና ኤክኖሚያዊ የዕድገት ጉዞ ተቀዳሚ እና መሠረታዊ መሥፈርት በመሆኑ ታሪክ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመገንባት ለማገዝ የሰው ልጅ ክብር እውቅና መስጠት እና ማስፋፋት ወሳኝ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ይጠቁማል።

እ.ኤ.አ. የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በላቲን አመሪካ የጳጳሳዊ ተቋማት እና ድርገቶች አባላት ተቀብለው መሪ ቃል ሲለግሱ፣ ምሥጢረ ተክሊል እና ቤተ ሰብ የሰው ልጅ ውስጣዊ ማንነት መግለጫ በሆነው እውነት እና ዕጣ ዕድል ላይ የጸና መሆኑ በማብራራት ከሰው ልጅ መሆናዊ እውነት ላይ የጸና በባለ ትዳሮች ፍቅር ታማኝነት እና የተረጋገጠ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል የሚቋቋም ቅዱስ ውህደት መሆኑ በማብራራት፣ ቤተ ሰብ እና ምሥጢረ ተክሊል ይኸንን እውነት መሠረት በማድረግ ዘመን አመጣሽ የተዛማጅ ባህል የሚያረማምደው ከማንኛው ዓይነት የሕይወት ምርጫ እና ተግባር ይገኝ፣ ተፈላጊው ደስታ እና ፈንጠዝያ ነው ከሚለው አመለካከት እና የሥነ ፍጆት መርህ ከሚያደርግ ሕይወት መከላከል ወሳኝ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 2007 ዓ.ም. በብራዚል ሳን ፓውሎ እና በአፓረሲዳ ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው፣ ላቲን አመሪካ የተስፋ ክፍለ ዓለም መሆንዋ ካቶሊክ ምእመና ሊመሰክሩት ይገባቸዋል። በማንኛው ዓይነት መንገድ የሰውል ልጅ ክብር ሊጣስ እና ሊረገጥ አንደማይገባው አብራርተው፣ ክርስትያኖች በትንሣኤ ካለን እምነት የመነጨ የእምነት ጽናት መሠረት ተስፋ እና እውነት መስካሪያን ሆነው መገኘት አለባቸው፣ ማንኛው ዓይነት በኅብረተሰብ የሚጋረጠው ጸያፍ ተግባር እና በግብረ ገብ ያልተካነ ሕይወት በልቅ የፍጆት ጽንሰ ሀሳብ የሚመራ ማኅበርሰብ ከክርስቶስ ወንጌል እና ከእግዚአብሔር የራቀ ነው። ስለዚህ ለዚህ ዓይነት ጸረ ሕይወት ባህል የእውነተኛው ሕይወት መስካሪያን በመሆን የማግለል ጥሪ የሁሉም ክርስትያን ምእመናን ኃላፊነት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ በማስታወስ ጠቅሶታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.