2011-02-25 15:02:12

በአንድ ወንድ እና በአዲስት ሴት መካከል የሚጸና ቃል ኪዳን/ጋብቻ


የተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የጋብቻ ተግባር ለመንከባከብ በሚል ርእስ ሥር በ እ.ኤ.አ. በ1996 ዓ.ም. ከባህርያዊ የጋብቻ ባህል እርሱም በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል ከሚጸናው RealAudioMP3 የተለየ ማንኛው ዓይነት ትዳር/ጋብቻ የሚከለክለው ፈደራላዊ ሕግ በመንግሥታቸው የሕግ እና ፍትህ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሪክ ሆልደር ተደግፈው የጾታዊ ሥሜት ዝንባሌ መሠረት ያለው አድልዎ የሚያስፋፋ ኢሕገ መንግሥታዊ ሕግ ነው በሚል ምክንያት ግብረ ሶዶማ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ትዳር መመሥረት በሕግ መፍቀድ የሚደገፉ መሆናቸው የሰጡት መግለጫ፣ የግብረ ሶዶማ ስሜት ያላቸው ዜጎች መብት እና ፈቃድ ተሟጋች ማኅበር የርእሰ ብሔር ኦባማ ሐሳብ ሲደገፉ፣ በሕዝባዊ አስተያየቶች እና የፖለቲካ መድረኮች ተቃውሞ እየተሰነዘረባቸው መሆኑ ተገልጠዋል።

ጋብቻ ወይንም ትዳር በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚጸና የጋራ ሕይወት መሆኑ የታመነበት ለዘመናት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው መሠረታዊ ባህል የሚያናጋ ነው በማለት የርእሰ ብሔር ኦቦማ ውሳኔ እርሱም በአንድ ወንድ እና ሴት የሚለው እ.ኤ.አ የ 1996 ዓ.ም. የጋብቻ ተግባር አስከባሪ ፈደራላዊ ሕግ የመንግሥታቸው የሕግ እና ፍትህ ጉዳይ ቢሮ እንዲከበር ከማድረጉ ውሳኔ እንዲቆጠብ የሰጡት ውሳኔ፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት በመቃወም የርእሰ ብሔር ኦባማ መንግሥት የዛሬ 15 ዓመት በፊት በወቅቱ በነበረው የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል ርእሰ ብሔር ያጸደቀው ሕግ እንዲያከበር እና የአገሪቱ ሕገ መንግሥት በሙላት በመታዘዝ እና እግብር ላይ ማዋል ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ የተባበሩት አሜሪካ መንግሥት የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ያመለክታል።

የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የአብላጫው ሕዝብ አስተያየት አንዳዊ ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚመሠረተው ጋብቻ ጋብቻ በሚል ቃል መግለጡ የማይስማማበት መሆኑ ሲገለጥ፣ ከጠቅላላ 50 የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ውስጥ በአምስት የአገሪቱ መንግሥታት ብቻ አንዳዊ ጾታ ባላቸው እርሱም የግብረ ሶዶማ ጾታዊ ስሜት ባላቸው ሰዎች መካከል ጋብቻ የሚፈቀድ መሆኑ ነው የሚታውቀው። በሌሎች ሰባት የአገሪቱ መንግሥታት ባህላዊ ጋብቻ በጽናት ለመከላከል የሚያግዙ ፈደራላዊ ደንቦች በቅርቡ ለማጽደቅ እንደሚሹ ሲረጋገጥ፣ ሆኖም ርእሰ ብሔር ኦባማ የጾታዊ ስሜተ አድልዎ ለማግለል የሁሉም መብት እና ፈቃድ ዋስትና መስጠት የሚለው የግብረ ሶዶማ መብት እና ፈቃድ ተከራካሪ ማኅበራት የሚከተለው ሐሳብ መሠረት ያደረገ ውሳኔ እያንጸባረቁ መሆናቸው ይንገራል።

ስለ ጉዳዩ በተመለከተ ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበር ጥበብ የመሠረተ ሥነ ምግባር መምህር ሮበርት ጋል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይህ የሁሉም መብት እና ፈቃድ ለማክበር በሚል ሰበብ በማንገብ የሚደረገው ቅስቀሳ መሠረታዊ የጋብቻ ጥልቅ ምሥጢሩ የሚጻረር ነው። ስለዚህ በሕገ መንግሥት ሥር ወንድ እና ሴት ብሎ የለም የሚለው ሐሳብ የተቀበልን እንደሆነ ጋብቻ ሳይሆን የቤተሰብ መሠረት የሆነው ትዳር መኖርም የለበትም። ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በተባበሩት የአሜሪካ መንግሥታት በሕግ መወሰኛ ምክር ቤት እና በሕግ አውጪ አካል መካከል የኃላፊነት ውጥረት እና ግጭት የሚቀሰቅስ ነው። ስለዚህ የርእሰ ብሔር ኦባማ መንግሥት አንድ የፖለቲካ ርእዮተ ዓለም መሠረት በማድረግ ያነሳሳው ፍላጎት እርሱም እያንዳንዱ ነጻ ነው ከሚለው ጾታዊ መለያው ጭምር መወሰን ይችላል ከሚለው ወንድ ወይንም ሴት ሆነህ ብትወለድ ግድ የማይል ጸረ መሠረታዊ መሆን የሚቃወም ተግባር ብቻ ሳይሆን ጸረ ሃይማኖት ጭምር ነው። ይህ የርእሰ ብሔር ኦባማ መንግሥት ፍላጎት ብሔራው አቀፍ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ መድረክ በተለይ ደግሞ በማደግ ላይ በሚገኙት አገሮች ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችል ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.