2011-02-25 15:01:02

ቅዱስ አባታችን፣ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍታት


ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነዲክቶስ 16ኛ ትላንትና ጧት በቫቲካን የረፓብሊካዊት ሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሚሸል ስለይማንን ትቀብለው እንዳነጋገሩ የቅስት መንበር የማህተም እና ዜና ክፍል ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ RealAudioMP3 በሊባኖስ በሙስሊሞች እና በማኅበረ ክርስትያን መካከል ያለው ሰላም የተካነው ማኅበራዊ ኑሮ ለአገሪቱ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በዓለማችን ክርስትያኖች እና ሙስሊሞች በነጻነት እና ተከባብሮ መኖር ለሚለው ክብር ቀስቃሽ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በመግለጥ፣ ይኸ ክብር ለማረጋገጥ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት እና ትብብር ዘወትር እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ያመለክታል። ስለዚህ የሃይማኖት መሪዎች እና የመንግሥት የበላይ አካላት እና ባለ ሥልጣናት የሕዝባቸውን ኅሊና ለሰላም እና ለእርቅ በማነጽ በሊባኖስ በጉጉት የሚጠበቀው መረጋገት እና ሰላም የሚደግፍ ብሔራው እና ዓለም አቀፋዊ ወቅታዊ ፈታኝ ሁኔታዎች የሚቋቋም መንግሥት እንዲጸና ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር የማኅተም እና ዜና ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

በመጨረሻም በተካሄደው ግኑኝነት ስለ መካከለኛው ምሥራቅ እና በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ዓረብ አገሮች እየታየ ያለው አንገብጋቢ ሁኔታ በመጥቀስ፣ የተቀሰቀሱት ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ ማግኘት ይገባቸዋል የሚለው የጋራው እማኔ እንደተሰመረበት እና በመካከለኛው ምሥራቅ ለማኅበራዊ ጥቅም አቢይ ሚና የሚጫወተው ማኅበረ ክርስትያን ሁኔታ ትኵረት ይሰጠውም ዘንድ ጥሪ መተላለፉ የቅድስት መንበር የማህተም እና የዜና ክፍል በመግለጥ፣ አክሎ የሊባኖስ ርእሰ ብሔር ስለይማን ከቅዱስ አባታችን ከተሰናበቱ በኋላ በቅድስት መንበር የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ተጠሪ ብፁዕ አቡነ ዶመኒክ ማምበር ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ጋር መገናኘታቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.