2011-02-23 15:43:06

የአፍሪካ ደቡባዊ ክልል አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


የአንጎላ ቦትስዋና ሎሶቶ ናሚቢያ ሞዛምቢክ እና ሳኦ ቶመ እና ፕሪንስ ደሴቶች ደቡብ አፍሪካ እና የዚምባብዌ ብፁዓን ጳጳሳት የሚያጠራንፈው የአፍሪካ ደቡባዊ ክልል አግሮች ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ በቅርቡ RealAudioMP3 ባካሄዱት 9ኛው የምልዓተ ጉባኤው ምዕራፍ ፍጻሜ ባጸደቀው የጋራ መግለጫ ሰነድ በዚምባብዌ ያለው ማኅበራዊ ሰብአዊ ኤኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑ በመጥቀስ ሁኔታው ያሳደረብቸው ሥጋት ለደቡብ የአፍሪካ ክልል አገሮች የልማት ማኅበር በይፋ ማቅረባቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የአፍሪካ ደቡባዊ ክልል አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት የጋራው ጉባኤ ባወጣው የጋራ መግለጫ፣ የአፍሪካ ደቡባዊ ክልል አገሮች የልማት ማኅበር የዓለም አቀፍ የግብርና ፖሊቲካ እቅድ እንዲረጋገጥ በማድረጉ ሂደት ባሳየው የነቃ ተሳትፎ፣ በዚምባብዌ ተከስቶ የነበረው ፖሊቲካዊ ውጥረት ለማግለል እንዲቻል የርእሰ ብሔር ሮበርት ሙጋቤ የፖለቲካ ሰልፍ እና የመራሔ መንግሥት ሞርጋን ዝቫንጊራይ የፖለቲካ ሰልፍ ያካተተ የአገር አንደነት መንግሥት እንዲመሠረት በማድረጉ ጥረት ተቀዳሚ ሚና ለመጫወት መብቃቱ ያመለከተው የብፁዓን ጳጳሳት የጋራው ጉባኤ መግለጫ አክሎ በሁለቱ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ሰልፎች መካከል ተከስቶ የነበረው አለ መግባባት ዚምባብዌ ለማኅበራዊ እና ፖሊቲካው ብሎም ኤክኖሚያዊ ውጥረት ዳርጓት እንደነበር እና አወዛጋቢው ጉዳይ ተወግዶ በአገሪቱ ሰላም ለማረጋገጥ የአገር አንድነት መንግሥት መመሥረቱ ብቸኛ አማራጭ የሌለው መፍትሔ መሆኑ የልማቱ ማኅበር አምኖበት እና እንዲመሠረት በማረጉ ፊና ያሳየው ያላሰለሰ ጥረት በማስታወስ፣ ሆኖም ግን ይኸው ይህ የአገር አንድነት መንግሥት ከተመሠረተበት ሁለት ዓመት ወዲህ ምንም’ኳ አንዳንድ መሻሻል የታየ ቢመስልም ቅሉ፣ የአገሪቱ ሕዝብ አሁንም በከፋ ድኽነት ተጠቅቶ እንደሚገኝ በማብራራት፣ በአገሪቱ የሚታየው ያልተሟላ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ማሻሻል፣ የተሟላ የሕንጸት አገልግሎት መጓደል፣ በአገሪቱ ያለው የኤኮኖሚው ፖሊቲካ አስተማማኝ ባለ መሆኑ ምክንያት ለመዋዕለ ንዋይ እንቅፋት መሆኑም ጭምር ብፁዓን ጳጳሳቱ በመተንተን በአገሪቱ የሚታየው አስከፊው ድኽነት ለመቅረፍ በሁሉ መሥክ ፍትህ ማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ እንዳሰመሩበት ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ።

በዚምባብዌ እ.ኤ.አ. በዚህ 2011 ዓ.ም. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እና የርእሰ ብሔር ምርጫ እንደሚካሄድ እና ለዚህ ወሳኝ ምርጫ በሚገባ ለማረጋገጥ ያግዛሉ ተብለው ተዘርዝረው የነበሩት መርሃ ግብሮች ገና ገቢራዊ ባለ መሆናቸው ምክንያት በአገሪቱ ዳግም ውጥረት ሊቀሰቅስ እንደሚችል ያደረባቸው ሥጋት ገሃድ በማድረግ፣ የሕዝብ ፍላጎት ተገቢ መልስ ለመስጠት የሚተጋ ፖሊቲካ ብፁዓን ጳጳሳት ባወጡት የጋራው ሰነድ መግለጫ አስፈላጊ ነው በማለት እንዳሰመሩበት ፊደስ የዜና አገልግሎት አመለከተ። ይህ በእንዲህ እንዳለም በቅርቡ በቱኒዝያ እና በግብጽ ሕዝባዊ አቢዮት እያረጋገጠው ያለው ለውጥ እና እንቅስቃሴው ጭምር በተሌቪዥን በመከታተል ቅጅ ለማስቀረት ይቀርጹ የነበሩት ወደ 40 የሚገመቱ የዚምባብዌ ዜጎች በዚምባብዌ ያለው ሕጋዊ መንግሥት ለመገልበጥ የሚያነሳሳ ወንጀል ነው በሚል ክስ ለእስር መዳረጋቸው ከዚምባብዌ የሚተላለፉ ዜናዎች ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.