2011-02-23 18:21:43

የር.ሊ.ጳ የዕለተ ሮቡዕ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (23.02.11)


ቅዱስ ኣባታችን ዛሬ ጥዋት የዕለተ ሮቡዕ ሳምንታዊ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ ከማስተማራቸው በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስትያን ዙርያ ከሌሎች ቅዱሳን ምስል ጋር የተጨመረውን የቅዱስ ማሩን ምስል ባርክዋል። በዚሁ ኣጋጣሚ የሊባኖስ ፕረሲደንት ሚሸል ሱለይማንና ባለቤቱ የኣንጾክያና አጠቃላይ የማሮናውያን ፓትርያርክ ብፁዕ ኣቡነ ሚሸል ሳባሕ በሮም የሚገኙ የማሮናውያን ማኅበር የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዝዮ በርቶነና ብዙ የክብር እንግዶች ተገኝተዋል። የቅዱሱን ሐውልት የቀረጹ መሃንዲስ ማርኮ ኣጉስቶ ዱወኛስም ተገኝተው ነበር።

በተፈጸመው ሥርዓተ ቡራኬ የማሮናውያን ተወካዮች በኣርብኛና በጣልያንኛ እንዲሁም የምስሉ መሃንዲስ በእስፓኝና ቋንቋ ስለ ቅዱሱ ታሪክና ለሊባኖስ ማኅብረ ክርስትያንና ለማሮናውያን የሚሰጠው ክብርና ደስታን ገልጠዋል።

ቅዱስ ማሩን በ4ኛው ክፍለ ዘመን ኣጋማሽ የተወለዱ ካህን ሲሆኑ በመጨርሻ ላይ የብሕትውና ሕይወት በመምረጥ በአንጾክያ ኣከባቢ በሚገኘው የታውሩስ ተራራ በብቸኝነት የኖሩ ናቸው። የቅዱስ ማሩን ቅድስናና ተኣምራቶች በግዛቱ ብዙ ዝና ስላተረፉ ብዙ ተከታዮች ኣግኝተዋል። ቅዱስ ዮሐንስ ኣፈወርቅ በ405ዓም ያለውን ኣክብሮትና ፍቅር የሚገልጥና ስለእርሱ እንዲጸልይለት በማማጠን መልእክት እንደላከላቸው ይነገራል።

ቅዱስ ማሩን የማሮናይት ቤተ ክርትያን መንፈሳዊና ገዳማዊ እንቅስቃሴ ኣባት መሆናቸውም ይነገራል። ይህ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በሰሜን ሲርያና በሊባኖስ ኃያል ተሰሚነት ኣለው። ቅዱስ ማሩን ሕይወቱን ሙሉ ስይሩስ በሚባል ተራራ በሲርያ ኣሳለፈው። ቦታው ክፋር ናቦ ተብሎ የሚጠራ በኦል ያምቦስ ተራራ የሚገኝ ሆኖ የማሮናይት እንቅስቃሴ ምንጭ ነው ተብሎ ይታመናል። የማሮናይት እንቅሳቃሴ ሊባኖስ ላይ የደረሰው የቅዱስ ማሩን የመጀመርያ ተከታይና የሊባኖስ ሐዋርያ በማለት የሚታወቀው ኣብርሃም ዘስይሩስ ኣረመነት በሊባኖስ ሲስፋፋ ባየ ግዜ አረሜናውያንን ወደ ክርስትና ለመምለስ የቅዱስ ማሩንን መንገድ ማስተማር በጀመረበት ግዜ ነው። የቅዱስ ማሩን ተከታዮች መንኮሳትና ምእመናን ዘወትር የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርት እምነት ይዘው ተጉዘዋል።



1ቆሮ፣2፣1-8 ‘እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ በቃልና በጥበብ ብልጫ ለእግዚአብሔር ምስክርነቴን ለእናንተ እየነገርሁ አልመጣሁም። በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና። እኔም በድካምና በፍርሃት በብዙ መንቀጥቀጥም በእናንተ ዘንድ ነበርሁ፤ እምነታችሁም በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ እንዳይሆን፥ ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል በጥበብ ቃል አልነበረም። በበሰሉት መካከል ግን ጥበብን እንናገራለን፥ ነገር ግን የዚችን ዓለም ጥበብ አይደለም የሚሻሩትንም የዚችን ዓለም ገዦች ጥበብ አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምሥጢር እንናገራለን።  ከዚችም ዓለም ገዦች አንዱ እንኳ ይህን ጥበብ አላወቀም፤ አውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር’

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣

የዛሬው ትምህርተ ክርስቶስ ስለ ትልቁ ኢየሱሳዊ የንባበ መልኮትና የቤተ ክርስትያን ሊቅ ስለሆነው ስለ ቅዱስ ሮበርት በላርሚን ይናገራል። ከትረንት ጉባኤ በነበረው ግዜ ቅዱስ ሮበርት በላርሚን መጀመርያ በሉቨይን ቀጥሎም በሮማዊ ኮልጅ ትምህርተ ንባበ መለኮት ኣስተምረዋል። እርሱ ከደረሳዎች ትላልቅ ድርሳናት ኣንዱ ኮትሮቨርስየ የሚለው ያኔ በተነሳው የፕሮተስታንት ንባበ መለኮትና ላይ በጤናማ ታሪካዊና ንባበ መለኮታዊ ትንታኔ በመመሥረት ተችተዋል። ሆኖም ግን ዋናው ትልቁ ድርሳኑ የክርስትና ኣንቀጸ እምነት ትምህርተ የሚል መጽሓፍ ነበር። በሮማን ኮለጅ የነበሩ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ኣበ ነፍስ በመሆንም ኣገልግለዋል፣ ከእነዛ ተማሪዎች ቅዱስ ኣሎይስዩስ ጎንዛጋ ይገኝባቸዋል። ቅዱስ ሮበርት በክለመንት 8ኛ ካርዲናል ሆነው በመሰየም የካፕዋ ሊቀ ጳጳስ ሆነዋል፣ በዚሁ ሃገረ ስብከት ለሶስት ዓመታት በትልቅ ትጋት ከሰበኩና የተለያዩ የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮዎች ከፈጸሙ በኋላ ለቅድስት መንበር ኣገልግሎት ወደ ሮም ተጠሩ። በቀረው ዕድሜኣቸውም የቅዱስ ኢግናጽዩስ መንፈሳዊ ሕንፀት የሚገልጹ የተለያዩ መጻሕፍት ጽፈዋል፣ በዚሁ መጽሓፍት በክርስቶስ ምሥጢርና በፍቅር እርሱን ስለመምሰል ለማስተንተን የሚረዱ መንፈሳዊ ምክሮች ለግሰዋል። የቅዱስ ሮበርት በላርሚን ኣብነት የክርስትና ቅድስናን ለማግኘት መላው ተግባራችን ለመዋሃህድና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ቅርብ ለመሆን እንዲያበቃን በዚህም በመንፈሳችን ወደ ጌታና የቃሉ እውነት ውሳጣዊ ለውጥ በማድረግ ለቤተ ክርስትያን መታደስ እንድንተባበር ያድርገን።

በኒው ዚላንድ የምትገኘውን የክራይስትቸርች ከተማ ባለፈው መስከረም ካጋጠመው በከፋ መንገድ ኣውዳሚ የሆነ ኣዲስና ኃይለኛ ርዕደ መሬት ኣጋጥመዋት ብዙ ሕይወት ማጥፋቱ የብዙ ሰዎች ሁኔታም ኣለመታወቁ መግለጫ የሌለው የንብረት ውድመት መድረሱ ተገንዝብናል። በዚሁ ከባድ ግዜ ሃሳቤ በዚሁ ኣሳዛኝ ትራጀዲ በሚፈተኑ ላይ ነው ያለው፣ ጌታ ሥቃያቸው እንዲያቀልላቸው እንዲሁም ሰዎቹን ለመርዳትና ለመደገፍ ስለሚታገሉት እንጸልይ፣ ሕይወታቸው ስላጡ በማድረገው ጸሎት ሁላችሁ እንድትተባበሩኝ እማጠናለሁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.