2011-02-23 15:41:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን አገልግሎት ለማጠናከር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በህንድ የካሊኩት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሴፍ ካላዚፓራምቢል የስደተኞች እና የተጓዦች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሆነው እንዲያገለግሉ መሾማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ብፁዕ አቡነ ካላዚፓራምቢል እ.ኤ.አ. በ 1962 ዓ.ም. በህንድ ኬራላ RealAudioMP3 ግዛት በምትገኘው ቫዱዛላ ከተማ ተወልደው እ.ኤ.አ. በ 1978 ዓ.ም. ምሥጢረ ክህነት ተቀብለው ሮማ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኡርባኒያኑም መንበረ ጥበብ በሕገ ቀኖና ሊቅነት አስመስክረው ከ 1998 የስሜተ ጵጵስና እስከ ተቀበሉበት 2002 ዓ.ም. ድረስ በህንድ ቨራፖልይ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ሆነው እንዳገለገሉ ሲገለጥ፣ በቅዱስ አባታችን ውሳኔ መሠረት፣ ለዚህ አዲስ የአገልግሎት ኃላፊነት እስከ ተሾሙበት ዕለትም በህንድ የካሊኩት ሊቀ ጳጳስ በመሆን በማገልግል ላይ እንደነበሩም የቅድስት መንበር መግለጫ ካሰርጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።

በፊሊፒንስ ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት የስካላ ስዩመ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ጆሴፍ አዳምስ በግሪክ ሓዋርያዊ ልኡክ ሆነው እንዲያገለግሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደሾሙዋቸው ሲገለጥ፣ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ጆሴፍ እ.ኤ.አ. በ 1944 ዓ.ም. በፊላደልፊያ ተወልደው እ.ኤ.አ. በ 1970 ዓ.ም. ምሥጢረ ክህነት እንደተቀበሉ መግለጫው በማስታወስ፣ እ.ኤ.አ. በ 1996 ዓ.ም. ስሜተ ጵጵስና እንደተቀበሉ እና ለሐዋርያዊ ልኡክ ኃላፊነት ወደ ግሪክ እስከ ተላኩበት ዕለት እ.ኤ.አ. ከ 2007 ዓ.ም. ጀምረው በፊሊፒንስ ሐዋርያዊ ልኡክ ሆነው በማገልገል ላይ እንደነበሩም የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.