2011-02-21 16:05:06

ዓቢይ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ዕለት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብፅእና እንዲታወጅላቸው ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት፣ ጳጳሳዊ የአበይት በዓላት ሥርዓተ አምልኮ ሠራኢ ብፁዕ አቡነ ጉይዶ ማሪኒ የበዓሉ ሂደት እና መርሃ ግብር እንዲሁም ሥነ ሥርዓት በተመለከተ ማብራሪያ መስጠታቸው RealAudioMP3 የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ይህ በአምስት የአከባበር ሥነ ሥርዓት ተከፋፍሎ የተዘጋጀው፣ በቅድሚያ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. የሮማ ሰበካ ያዘጋጀው በሮማ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ የሚመራ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቀጥታ በምስል እና በድምጽ የተቀረጸ መልእኽት አማካኝነት ለሁሉም ምእመናን ዕለቱ የቤተ ክርስትያን በዓል መሆኑ የሚተነትን መልእክት በማስተላለፍ ቡራኬ የሚሰጡበት ሮማ በሚገኘው በቺርኮ ማሲሞ ሜዳ የዋዜማ ሥነ ሥርዓት እንደሚከወን የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል መግለጫ ሲያመለክት፣ በመቀጠልም እሁድ ግንቦት 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳማዊ በይፋ ብፅና ከታወጀላቸው በኋላ በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በኑዛዜ መንበረ ታቦት ፊት ለሁሉም መንፈሳዊ ነጋድያን ጸሎት እና አስተንትኖ ምክንያት የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱስ አጽም እንደሚቀመጥ እና እ.ኤ.አ. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ የሚመሩት የምስጋና መሥዋዕተ ቅዳሴ እንደሚቀርብ እና በመሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜም የር.ሊ.ጳ. አዲስ ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቅዱስ አጽም በቫቲካን ባሲሊካ ቅዱስ ሰባስቲያን ቤተ ጸሎት እንደሚያርፍ የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.