2011-02-21 15:23:43

ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ፍትህ ቀን


የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ለብሔራዊ እና ለዓለም አቀፍ መረጋገት ቅድሚያ መሰጠት የሚገባው የሥነ ምግባር ትእዛዝ የሆነው ማኅበራዊ ፍትህ መሠረት መሆኑ ትላትና ታስቦ የዋለው ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ፍትህ ቀን RealAudioMP3 ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ፣ ዓለም አቀፍ የኤክኖሚ ቀውስ በማስታወስም በሁሉም መሥክ የሰብአዊ ክብር መከበረ እንዳለበት እና የምንኖርበት ዓለም ለሁሉም ዋስትና የሚሰጥ ማንንም የማያገል መሆን አለበት ብለዋል።

የኢጣሊያ መንግሥታዊ ያልሆኑትን የግብረ ሠናይ ማኅበራትን የሚያቅፈው ማኅበር ሊቀ መንበር ሰርጆ ማረሊ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ባን ኪ ሙን እንዳሉት ማኅበራዊ ፍትህ ሥነ ምግባራዊ ትእዛዝ ነው ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት የሚለው ብቻ ሳይሆን ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው መሆኑም ያስተምራል። በዓለማችን ገደብ ያጣው እና ለመቅረፍም እጅግ አስቸጋር የሆነው በድኻው እና በሃብታም መካከል ያለው የኑሮ ደረጃ ልዩነት፣ የድኻ ዓለም ዜጎች አገራቸውን ጥለው ወደ ሃብታም አገሮች የሚያደርጉት ጸዓት፣ ስደተኛው በማባረር በመቀበል ብቻ የሚፈታ ሳይሆን፣ ማኅበራዊ ፍትህ በማረጋገጥ ብቻ ነው ለማስወገድ የሚቻለው። ምክንያቱ ለስደት የሚዳርገው ችግር ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ እና ተመሳሳይ ዘርፈ ብዙ ምክንያት ቢሰጠውም ቅሉ ዋናው እና መሠረታዊ መንስኤው የማኅበራዊ ፍትህ መጓደል ነው። ስለዚህ ማኅበራዊ ፍትህ ማረጋገጥ ለመረጋገት እና ለተሟላ እድገት እና ሰላም መሠረት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.