2011-02-21 15:20:58

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፦ በእምነት ማደግ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከትላንትና በስትያ ጧት ሮማ የሚገኘው የፊሊፒስን ጳጳሳዊ ተቋም የተቋቋመበት 50ኛ ዓመት ምክንያት አባላቱን ካህናት ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

ለቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. በፊሊፒንስ ጳጳሳዊ ተቋም ተማሪዎች ካህናት RealAudioMP3 ስም የሰላምታ መልእክት ያቀረቡት የፊሊፒንስ ጳጳሳዊ ተቋም አለቃ አባ ግረጎርይ ራሞን ጋስቶን ስለ ግኑኝነቱ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይህ ሮማ የሚገኘው የፊሊፒንስ ካህናት ጳጳሳዊ ተቋም በር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ መልካም ፈቃድ እና ፍላጎት የዛሬ 50 ዓመት በፊት የተመሠረተ መሆኑ በመግለጥ፣ ይህ ተቋም ብዙ የፊሊፒንስ ውሉደ ክህነት አባላት እዚህ በሮማ በተለያዩ ጳጳሳዊ መናብረተ ጥበብ በተለያዩ የቲዮሎጊያ የትምህርት ዘርፎች ሊቅነት አስመስክረው ወደ አገራቸው ተመልሰው ሓዋርያዊ አገልግሎት እንዲፈጽሙ በማድረግ ተልእኮ አቢይ አስተዋጽዖ የሰጠ እና በመስጠት ላይ መሆኑንም ገልጠው፣ ቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዚህ ጳጳሳዊ ተቋም ተማሪዎች የፊሊፒንስ ውሉደ ክህነት አባላት ተቀብለው የሰጡት መሪ ትምህርት በእምነት ማደግ በሚል መሠረታዊ ሀሳብ ላይ ያተኮረ እና ተማሪዎቹ በቲዮሎጊያ እና በመንፈሳዊነት እንዲሁም በሮማዊት ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ታሪክ ታንጸው ወቅቱ የሚጋርጠው እክል በማሸነፍ ሰብአዊ እና መንፈሳዊ ሕንጸት በማግኘትም ክህነታዊ ጥሪያቸውን ዕለት በዕለት በመንከባከብ የክርስቶስ ፍጹም ፍቅር መስካሪያን እንዲሆኑ አደራ ያለ መልእክት ነበር ካሉ በኋላ ካህናቱ የላቀው የቲዮሎጊያ ትምህራቸውን አጠናቀው ወደ አገራቸው ተመልሰው በሚሰጡት አገልግሎት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመሰክሩ የሚያሳስብ መሆኑ ገልጠዋል።

ማንኛውም ለከፍተኛ የቲዮሎጊያ ትምህርት ከተለያዩ ሰበካዎች እዚህ ሮማ የሚላኩት ካህናት ምንም’ኳ ለትምህርት የተላኩ ቢሆንም ቅሉ ሓዋርያዊ አገልግሎት የማከናወኑ ተቀዳሚው የጥሪያቸው ዓላማ ማግለል እንደማይገባቸው በማሳሰብ፣ በዚህ አጋጣሚም ለፊሊፒንስ ሕዝብ እና በፊሊፒንስ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በመጸለይ ሐዋርያዊ ቡራኬም በመስጠት መሰናበታቸው ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምደመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.