2011-02-19 11:48:20

የቅዱስ ጳውሎስ ዓመት በሚል ኣርእስት የተዘጋጀ መጽሓፍ ለንባብ በቃ


ቅ.ኣ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ከሦስት ዓመታ በፊት ባወጁት መሠረት የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ዓመት መከበሩ የሚታወስ ነው። ይህንን የማይረሳና የጸጋ ዓመት በማስታወስ በግራዝያኖ ሞታ ትጋት የተጠናቀረውና የተዘጋጀው መጽሓፍ ብቫቲካን መዝገበ መጻሕፍት ሕትመት ቤት ታትሞ ለንባብ በቃ። ትናንትና ጥዋት በቅድስት መንበር የሕትመት ኣደራሽ መጻሓፉን ለሕዝብ ያቀረቡ ብፁዕ ካርዲናል ኣንድረኣ ኮርደሮ ላንዛ ዘሞንተዘሞሎ እና የቅዱስ ጳውሎስ ጳጳሳዊ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል ፍርናቸስኮ ሞንተሪዚ ናቸው። በጉባኤው የኤውሮጳ ኣዲስ ስብከተ ወንጌል ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚከላም ተገኝተው ነበር።

ብፁዕ ካርዲናል ኮርደሮ ላንዛ ዘሞንተዘሞሉ መጽሓፉን ኣስመልክተው በሰጡት ኣስተያየት “መጽሓፉ ኣለ ምንም ማጋነን እጅግ ትክክለኛና ሃብታም መጽሓፍ ነው፣ በቤተ ክርስትያን ለመጀመርያ ግዜ የተከበረበውን የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ዓመት ከሰኔ 2008 እስከ ሰኔ 2009 በትክክለኛ ሁኔታ የሚገልጥ ታሪካዊ ፍጻሜ ነው።’ ብለዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ ኣንደኛ ሊቀ ካህናት በመሆን ብ2005 ዓም በር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ የተሾሙ ብፁዕነታቸው ር.ሊ.ጳ የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ዓመትን ያወጁበትን መንፈስ በማስታወስም፣ ‘ቅዱስነታቸው ቅዱስ ጳውሎስ ሃብታም ከሆኑ የቤተ ክርስትያናችን ምንጮች የእምነታችን ምንጭ ከሆኑ ኣንዱ ሲሆን ያልታወቀና በጥሩ ሁኔታ ያልተተሮጎመ ባሉኝ ግዜ ቅዱስነታቸው ዓመት ሐዋርያውን ለማወጅ ዋነኛ ምክንያት ይህንን ሃብት ለማወቅና ለማሳወቅ ነው ባሉኝ ግዜ ሌላ ምክንያትስ የትኛው ይሆን ብየ በልቤ ሳሰላስል የምናደርገውን ሁሉ ብቻችን ኣይደለም የምናደርገው፣ ከወንድሞቻችን ሊሎች ክርስትያኖች ሆነን ነው የምናደርገው ኣሉኝ” በማለት ትውስታቸውን ተርከዋል።
በዓመተ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ በሮማና በዓለም ሙሉ ብዙ ነገሮች ተከናውነዋል፣ ግራዝያኖ ሞታም እነኚህን ክንዋኔዎች በጥራትና በጥንቃቄ በመጽሓፉ ኣስፈረዋል። ዓመቱ የጸጋ ዓመት ነበር፣ እውነትም እኛ ካቀድነውና ከገመትነው በላይ በመሄድ የጸጋ ዓመት ሆኖልናል ሲሉም ጸሓፊው በዓመቱ ለተከናወኑት ሃይማኖታዊና ባህላዊ ክንዋኔዎች እንዲሁም በየኣብያተ ክርስትያናቱ የተደረጉ ንግደቶች ሥርዓተ ኣምልኮዎች ጉባኤዎች ትዕይንቶችና በቅዱስ ጳውሎስ ባሲልካ የተደረገው ማሳደስ የፈጠረው ኣዲስ የኑዛዜ ቦታና የቅዱስ ጳውሎስ መቃብርን በቀላሉ ለማየት የተደረገው ኣዲስ የቤተ ክርስትያኑ ትልቅ በር በኣድናቆት ኣስታውሰዋል።
ሊቀ ጳጳስ ሪኖ ፊዚከላም በበኩላቸው ‘ዓመተ ቅዱስ ጳውሎስን የምናስታውስበት ታሪካዊና ቅርሳዊ ነገር ያለ እንደሆነ ይህ ዛሬ የምናበረክትላችሁ ‘የቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ዓመት’ የሚለው መጽሓፍ ከዋና ምንጭ የተገኙ ለሚመጡ ዓመታት መሠረታዊ የታሪክ መጣቀሻ ሆኖ የሚኖር ነው፣ ምክንያቱ ጸሓፊው ለቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ማኅበረ ሰብ የማይረሳውን ዓመተ ጳውሎስ በሰው ልጅ ኣእምሮ ቀርጾ የሚያስቀሩ በተለያዩ ኣካላት የተደረጉ ዓመቱን እውን ያደረጉ ተግባሮችና ሁኔታዎችን መዝግቦ ኣቅርበዋልና’ ሲሉ መጽሓፉ ለወደፊት ትውልድ ምን ያህል የዕውቀት ሃብት ይዞ እንደሚጓዝ ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.