2011-02-19 11:35:42

የር.ሊ.ጳ መልእክት ለዓለም ዓቀፍ የጥሪ ቀን


የዘንድሮ ዓለም ዓቀፍ የጥሪ ቀን እአአ እፊታችን ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓም ተስታውሶ እንደሚውል ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና ኣመልክተዋል። ይህንን በተመለከተ ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት ጽፈዋል። የመልእክቱ ዋና ይዘት በዓለም ውስጥ የሚገኙ ኣብያተ ክርስትያን በያሉበት የክህነትና የምንኵስና ጥሪ እንዲያስታውቁ ወጣቶችን ደግሞ ለጥሪ እንዲያበራታቱ ኣደራ የሚል ነው። የመልእክቱ ትርጉም እንደሚከተለው ነው።

የቅዱስ ኣባታችን መልእክት ለ48ኛ ዓለም ዓቀፍ ለሐዋርያዊ ጥሪ የሚደረግ ጸሎት እንደላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ ከትንሣኤ በኋላ 4ኛ እሁድ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓም።

አርእስት፣ ‘በየክልሉ ኣብያተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ጥሪ ማሳሰብ’

ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ እፊታችን ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓም ለሚታወሰው 48ኛ ዓለም ዓቀፍ ለሐዋርያዊ ጥሪ የሚደረግ ጸሎት እንደላቲኑ ሥርዓተ ኣምልኮ ከትንሣኤ በኋላ 4ኛ እሁድ ይደርጋል፣ ይህ ዕለት ‘በየክልሉ አብያተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ጥሪ እንድናሳስብ ጥሪ ያቀርብልናል። ከሰባ ዓመታት በፊት ስመጥር ር.ሊ.ጳ ፕዮስ 12ኛ ‘ለክህነታዊ ጥሪ የሚያገልግል ጳጳሳዊ ተግባር’ መሥርተዋል። የተለያዩ ሃገረስብከቶች ጳጳሳት ይህንን ተከትለው በየክልላቸው በካህናትና በምእመናን የሚራመዱ የሓዋርያዊ ጥሪ ጸሎት ተግባር መሥርተዋል። ይህ ተግባር መልካሙ እረኛ በወንጌለ ማቴዎስ 9፣36-38 ‘ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው። በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። መከሩስ ብዙ ነው፥ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፤ እንግዲህ የመከሩን ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞች እንዲልክ ለምኑት አላቸው።’ ለሚለው ጥሪ መልስ ነው። ሐዋርያዊ ጥሪን የማራመድና የመንከባከብ ተግባር ወንጌል ተዘግቦ ያለው ብሩህ ኣብነት ኢየሱስ ሐዋርያቱን እንዲከተሉት ያቀረበው ጥሪና በፍቅርና በአሳቢነት ያስተማራቸው ሁሉን ያብራራል። ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው ወንጌል 10፣9 ላይ ኢየሱስ የመጀመርያ ተባባሪዎቹን የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲሰብኩ እንዴት እንደመረጣቸው ይተርካል። ከዚህ አካሄድ የምናማረው ነገር አለ፣ ጌታ ከሁሉም ኣስቀድሞ ሐዋርያቱን ከመምረጥ በፊት ሌሊቱን ሙሉ ብቻው ሆኖ ጸሎት እንዳሳረገ፣ እንዲሁም ሌላ ግዜ ከሚያደርገው ዕለታዊ ጸሎት ለየት ባለ መንገድ ያኔ ባደረገው ጸሎት ለረጅም ግዜ እንዳስተነተነና የኣባቱን ፍላጎት እንዳዳመጠ ይነግረናል። የሐዋርያት ጥሪ ኢየሱስ ከኣባቱ ጋር ካደረገው ጥብቅ ግኑኝነትና ውይይት ይወለዳል። የክህነትና የምንኩስና ጥሪ መጀመርያ ከሕያው እግዚአብሔር ጋር ከሚደረግ ቀጣይ ግኑኝነትና ከቁምስናም ይሁን ከክርስትያን ቤተ ሰብ እንዲሁም ለጥሪ በሚደረግ ጸሎት ወደ መከሩ ጌታ በሚያርግ የማያቋርጥ ጸሎት ፍሬ ናቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በይፋ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮውን ከመጀመሩ በፊት በገሊላ ሐይቅ ኣከባቢ ለመሥራት ዕቅድ የነበራቸው ኣንዳንድ ዓሣ ኣጥማጆችን ጠርቶ ‘ተከተሉኝ፣ ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው። ማቴ 4,19’። ከተከተሉትም ብኋላ መሲሓዊ ተልእኮውን በተለያዩ ምልክቶች ኣሳያቸው፣ እነኚህም ምልክቶች ጌታ ለሰው ልጅ የነበረውን ፍቅርና የኣባቱ ምሕረት ስጦታን የሚያመለክቱ ነበር። የደህንነት ተግባሩን ለመቀጠል እስኪችሉ ድረስም በቃሉና ብሕይወቱ ኣስተማራቸው፣ በመጨረሻም ‘ኢየሱስም ከፋሲካ በዓል በፊት፥ ከዚህ ዓለም ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ አውቆ፥ ዮሐ 13,1’። የሞቱና የትንሣኤው ማስታወሻ የሆነውን ኣደራ ሰጣቸው፣ ወደ ሰማይ ከመውጣቱም በፊት ‘ሂዱ ሁሉንም የእኔ ተከታዮች ኣድርጓችው ማቴ 28፣19 በማለት ወደ መላው ዓለም ላካቸው።

ጌታ ኢየሱስ የእርሱ ለሆኑት ሁሉ ‘ተከተለኝ’ በማለት የሚያቀርበው ጥሪ ብዙ የሚጠይቅና ከፍ ያለ ስሜት የሚያሳድር ነው። ጓደኞቹ እንዲሆኑና በቅርብ ቃሉን እንዲሰሙና ከእርሱ ጋር ለመኖር ይጠራቸዋል። ራሳቸውን ለእግዚአብሔር መስጠት እንዳለባቸውና በሕገ ወንጌሉ መሠረት የእግዚአብሔር መንግሥት ለማስፋፋት እንዲዘጋጁ ያስተምራቸዋል። ‘እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።ዮሐ12,24’ ሲልም ጭፍን ከሆነ ስሜታቸውና ፍላጎታቸው እንዲሁም በገዛ ራሳቸው ከመተማመን ወጥተው በእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲገዙና በእርሱ እንዲመሩና ከዚህ በሚወለደው ወንድማማችነት እንዲኖሩ ይጠራቸዋል። ‘እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ፣ ዮሐ 13፣35’ ሲልም የኢየሱስ ማኅበር ኣባላት መሆናቸው ከሌሎች ለይቶ የሚያሳውቃቸው የፍቅር ምልክት መሆኑን ይነግራቸዋል። ዛሬም ቢሆን ኢየሱስን መከተል ብዙ ይጠይቃል። ዓላማህ በሆነ በኢየሱስ ማትኮር ጠለቅ ባለ መንገድ ማወቁ ቃሉን ማዳመጥ በቅዱሳት ምሥጢራት ማግኘቱ በሌላ ኣነጋገር ፍላጎትህን ከፈቃዱ ጋር ኣንድ ለማድረግ መማር ከበድ ያለ ነው። ለክህነት ለሚዘጋጁ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ለየት ባለ መንገድ በተገቡ የቤተ ክርስትያን ኣስተማሪዎች እውነተኛና ዋና በሆነ ተኰትኵቶ ለተደቀሰ ሕይወት መዘጋጀትን ያመለክታል። ጌታ ሁሉ ግዜ እየጠራ ነው፣ የእርሱን ተልእኮ በመከተል ቤተ ክርስትያኑን እንዲያገለግሉ በሁሉም የሕይወት ደረጃ ለሚገኙ የሰው ልጆች ከመጥራት ኣቋርጦ ኣያውቅም፣ ቤተ ክርስትያንም ይህንን ስጦታ ለመጠበቅ ለማድነቅና ለማፍቀር የተጠራት ናት፣ ቤተ ክርስትያን የክህነት ጥሪ መጀመርና ወደ ብስለት ደረጃ ከፍ ማድረግ ኃላፊነትዋ ነው። በተለይ በዚሁ ዘመናችን የጌታ ድምጽ በሌሎች ድምጾች የታፈነ በሚመስልበት ግዜ እና ሕይወትህን በመሰዋት እርሱን ለመከተል የሚደረግ ጥሪ እጅግ ከባድ ሆኖ በሚታይበት ግዜ እያንዳንዱ ክርስትያናዊ ማኅበረሰብ እያንዳንዱ ምእመን ኃላፊነቱን ኣውቆ የክህነት ጥሪ የሚያዳብርበት መንገድ መሻትና በእምነት መሥራት ኣለበት። ለክህነትና ለገዳማዊ ሕይወት ዝንባሌ የሚያሳዩትን ሰዎች መበረታታትና መደገፍ ኣስፈላጊ ነው፣ በእንዲህ ዓይነት ድጋፍ ባለ ጥሪዎቹ የማኅበረሰቡ መንፈስ በመረዳት ለእግዚአብሔርና ለቤተ ክርስትያን እሺ ብለው ሊመልሱ ይችላሉና። እኔም በበኩሌ በዘርአ ክህነት ሊገቡ ለወሰኑ በጻፍኩት መልእክት ‘ይህንን ለማድረግ በመወሰናችሁ ጥሩ ውሳኔ ኣድርጋችኋል፣ ምክንያቱም በዚሁ በተክንሎጂ ብልፅግና እጅግ ከፍ ብሎና በግሎባሊዘይሽን ኣንድ ሆነ ባለው ግዝያችን ይሁን በቀረው ግዜ፣ የሰው ልጆች ሁል ግዜ እግዚአብሔር ሊያስፈልጋቸው ነው፣ ይህ እግዚአብሔር በኩላዊት ቤተ ክርስትያን በሚሰበስበን ኢየሱስ ክርስቶስ ኣድርጎ እውነተኛን ሕይወት ከእርሱና በእርሱ እንድንማር እውነተኛ ሰብኣውነትን እንድንከትልና እንድናበለጽገው ኣሳይቶናል’ በማለት መልእክት ለዘርአ ክህነት ተማሪዎች በተሰኘው መልእክቴ ጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓም ጽፌለሁ። ዛሬም ቢሆን በየቦታው የምትገኝ ቤተ ክርስትያን የክህነት ጥሪን ጉዳይ ቅድምያ በመስጠት ስለ እርሱ መስበክና የክህነት ጥሪ ግብረ ተልእኮ ማጐልበት ኣለባት። ይህንን ለማድረግ ደግሞ በተለያዩ ደረጃዎች ስለ የክህነት ጥሪ ማስተማ ኣለባት፣ በቤተ ሰብ ደረጃም ይሁን በቁምስና ደረጃ እንዲሁም ለወጣቶች የተለያዩ ማኅበራትና እንቅስቃሴዎች በማዘጋጀት ኢየሱስ ከመጀመርያዎቹ ኣርድእት ያደርገው እንደነበረ በማድረግ ከጌታ ጋር ጓደኝነት እንዲኖራቸው ያድርጉ፣ ይህ ጓደኝነት በግላዊ ጸሎትና በማኅበራዊ ሥርዓተ ኣምልኮ በመሳተፍ የጌታን ቃል በጥሞና ማዳመጥና ማስተንተን ቅዱስ መጽሓፍን ልዩ ጓደኛ በማድረግ ሕይወትን የሚለውጥና የሚያሳድግ እርምጃ በመውሰድ የጌታን ፈቃድ ማጤን ያስፈልጋል። ምክያቱም እውነተኛ ሕይወትና ደስታ ሊገኝ የሚችለው ለእግዚአብሔር ፍቅር ልብን በመክፈት ብቻ ነው። ‘በየክልሉ ኣብያተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ጥሪ ማሳሰብ’ ስንል በቂ ዝግጅትና ይዘት ያለው የክህነት ጥሪ ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ በማዘጋጀት ኢየሱስን የመከተል መንገድና ከእርሱ የሚገኘው ሃብትና ደስታ ለመላው የሕይወት ዘመን የሚሆን መሆኑን ማስገንዘብ ነው።

ለየት ባለ መንገድ በጵጵስና ወንድሞቼ ለሆናችሁ በጌታ ለተሰጣችሁ በክርስቶስ የማዳን ተልእኮኣችሁ ቀጣይነት እንዲኖረው እንዲሁም ለሁሉም እንዲዳረስ እንድታደርጉ እናንተ ጳጳሳትን እማጠናለሁ። በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ክርስቶስ ጌታ በሚለው ክፍል ቍ.15 ኣደራ እንዳለው ‘የክህነትና የድንግልና ጥሪ በተለይም በስብከተ ወንጌል ተልእኮ በሚያስፈልጋቸው ኣከባቢዎች በተቻለ መጠን እንድታሳድጉ እጅግ ኣስፈላጊ ነው። የጌታ ጥሪዎች ወደ ተመረጡ ሰዎች ልብ እንዲደርሱ ጌታ የእናንተ መተባበር ያስፈልገዋል፣ በሰበካ የጥሪ ማእኮሎች የሚሰሩትን ኣገልጋዮች እንድትንከባከብዋቸው ኣደራ፣ እነርሱ የክህነትና የድንግልና ጥሪን የሚያራምዱና የዚህ ኣገልግሎት ሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮን በማዘጋጀት የጸሎትና የድጋፍ ምንጭ ናቸው፣ ይህንን ተልእኮ የሚያንቀሳቅስና ፍሬ እንዲሰጥ ዋስትና የሚሆኑ እነኚህ ሰዎች ናቸው። ውድ ወንድሞቼ ጳጳሳት እንተላዕለኩሉ ቤተ ክርስትያን በዓለም ውስጥ እኩል የሆነ የካህናት መዳረስ እንዲኖረስ በእናንተ ላይ የጣለችውን ኣደራ እንዳስታውስችሁም እፈልጋለሁ፣ የካህናት ጥሪ እጥረት ላላቸው ሰባካዎች ለመርዳት የምታደርጉት መተባበር ለማኅበሮቻችሁና የዚህ ክህነታዊ ኣገልግሎት ምስክርነት ለሚቀበሉ ምእመናን ለመላዋ ቤተ ክርስትያን ኣስፈላጊነት ክፍት የሚሆን የእግዚአብሔር ቡራኬ ምንጭ ይሆናል።

ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ በክህነታዊ ኣስተዳደግ በሚለው ኣንቀጹ ቍ.2 ላይ የክህነት ጥሪ መበረታታት የቤተ ክርስትያን ምእመናን ሁሉ ኃላፊነትና ግዴታ ነው፣ ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ ከሁሉ ኣስቀድመው በክርስትያናዊ ኣና`ና`ራቸው እንከል የሌለባቸው በመሆን ሲኖሩ ነው’፣ ያለውን ማስታወስ ያስፈልጋል። በተለያየ መንገልድ በየቁምስናው ከካህናት ጋር ለሚተባበሩት ሁል ወንድማዊ ልዩ ሰላምታ በማቅረብ እንዲበረቱ እደራ እላለሁ። በተለይ ደግሞ በክህነታዊ ጥሪ ግብረ ተልእኮ ለተሰማሩ ካህናት ቤተ ሰቦች የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተማሪዎች እና ይህንን ግብረ ተልእኮ ለሚያራምዱ እንዲጐለብቱ ኣደራ እላለሁ። ካህናት ደግሞ ከጳጳሳቶቻቸውና ከወንድሞቻቸው ካህነት የኣንድነት ምስክር እንዲሆኑ በዚህም ለኣዲሱ የካህናት ትውልድ ዋስትና እንዲሆኑ ኣደራ እላለሁ። ቤተ ሰቦችም በእምነት በፍቅርና በምግባረ ሠናይ የበለጸጉ በመሆን ልጆቻቸው የክህነትና የድንግልና ጥሪን በደስታ እንዲቀበሉ እንዲረድዋቸው ይሁን። የትምህርተ ክርስቶስ ኣስተማሪዎችና የተለያዩ የካቶሊካውያን እንቅስቃሴዎች መሪዎች እንዲመርዋቸው እንዲያነቅዋቸው ለተሰጥዋቸው ወጣቶችን መለኮታዊ ጥሪኣቸውን ኣውቀው እንዲችሉና ጥሩ በሆነ መንገድ እንዲከተሉት እንዲኰትኵትዋቸው እደራ እላለሁ። የተከበራችሁ ወንድሞቼና እኅቶቼ፣ ጥሪን ለማሳደግና ለመኰትኰት የተሰጣችሁ ኣደራ በቤተ ክርስትያን ኣንድነት ሥር ሲተዳደር የሐዋርያዊ ግብረ ተልእኮ ትርጉምና ችሎታ በማግኘት ለውህደትና ኣድነት ኣገልግሎት ይውላል። ለዚህም ነው እያንዳንዱ የማኅበሩ ክርትያኑ ሕይወት ማለት ትምህርተ ክርስቶስ ለዕድገት የሚደረገ የተለያዩ ስብሰባዎች ሥርዓተ ኣምልኮኣዊ ጸሎቶች በተለያዩ መካነ ንግደቶች የሚደረጉ ንግደቶች በሕዝበ እጝዚአብሔር ኅሊና ልዩ የሆነ ዕድል ይፈጥራል በተለይም በወጣቶች ላይ የሚያሳድረው ስሜት የቤተ ክርስትያን ኣባል መሆንና ነጻና ብሩህ የክህነትና ድንግልና ጥሪ ኃላፊነት ስሜት ይፈጥራል።

የክህነትና የድንግልና ጥሪ መልስ በማግኘት ወደ ፍሬ የማድረስ ችሎታ የኣንዲት ቤተ ክርስትያን የሕይወት ምልክት ነው። እመቤታችን ድንግል ማርያም የእግዚኣብሔር መለኮታዊውን የማዳን ዕቅድ በመቀበል ባሳየችው ኣብነትና ስለእኛ በምታቀርበው ኣማላጅነት በእያንዳንዱ ማኅበረ ክርስትያን ለማሳው ዘወተር ኣዳዲስ ሰራተኞች ለሚጠራ ጌታ እሺ የሚሉ እንዲበዙ የእመቤታችን ድንግል ማርያም እርዳታን ሳናቋርጥ በመተማመን እንጠይቅ፣ በዚህ መልካም ምኞት ለሁላችሁም ሐዋርያዊ ቡራኬየየን ከልቤ እልክላቸዋለሁ።

ከቫቲካን ከተማ ኅዳር 15 ቀን 2010 ዓም ተላከ።








All the contents on this site are copyrighted ©.