2011-02-11 13:29:30

እንግልጣር፣ የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ርክስትያን ሲኖዶስ


የኵላዊት እና የውህደት እንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ ለውህደት የጋራ ድርገት፣ ሥነ ማርያም የሚመለከት የሥርወ እምነት ክፍል የሆነው ዓንቀጽ ርእሰ ጉዳይ በማድረግ ያጠንቃረው ሰነድ RealAudioMP3 ለውኅደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ መቅረቡ ተገልጠዋል።

ይህ ማርያም፣ ጸጋ እና ተስፋ በክርስቶስ በሚል ርእስ ሥር የካቶሊክ እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ዓለም ዓቀፍ የጋራው ድርገት ያጠናቀረው ሰነድ፣ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና እንዲሁም የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን በተናጥል በጥልቀት እንደሚያጤኑት የዌስት ሚኒስትር ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆርጅ ስታክ እንደገለጡ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።

የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ማርያም ጸጋ እና ተስፋ በክርስቶስ በሚል ርእስ ሥር የካቶሊክ እና የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሥለ ቅድስት ድንግል ማርያም የሚመለከተው በሥርወ እምነት ዘንድ ያለው በማስደገፍ በመወያየት ያጠናቀረው ሰነድ ከትላትና በስትያ ድምጽ በምስጠት ከተቀበለው በኋላ፣ በካቶሊክ ቤተ ርክስትያን ሥርወ እምነት ዘንድ ያለው እርሱም የማርያም አለ አዳም አጢአት መጸነስ የአዳም ሐጢአት ያልነካት ንጽሕት እና እርገተ ማርያም የሚገልጥ ነጥብ እና የማርያም ተልእኮ ሥልጣን የሚመለከት ጥያቄ በውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን በቤተ ክርስትያን መከፋፈል ያስከተለው ቅድመ ኅዳሴ እና ቅድመ ጸረ ኅዳሴ ተግባር በፊት የነበረው ውህደት ላይ የጸና የካቶሊክ እና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን የጋራው ትውፊት የአበው ትምህርት እና ቅዱስ መጽሓፍ በማስደገፍ ጥልቅ እና ተጨማሪ ጥናት እንዲደረግበት የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ውሳኔ ማቅረቡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.