2011-02-11 13:25:03

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. አዲስ ሓዋርያዊ ልኡክ ሾሙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በስሎቨኒያ ሓዋርያዊ ልኡክ በኮሶቮ ሐዋርያዊ ወኪል እንዲሆኑ በህንጋሪ ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት በኢጣሊያ ቨነቶ ክፍለ ሃገር ቨነዚያ አውራጃ ለምትገኘው የካኦርለ ከተማ RealAudioMP3 ስዩመ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጁሊኡስዝ ጃኑስዝ መሾማቸው የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል ከሰጠው መግለጫ ለማወቅ ሲቻል፣ የማኅተም ክፍሉ መግለጫ አክሎ እንደሚያመለክተውም፣ በስሎቨኒያ ሐዋርያዊ ልኡክ እንዲሆኑ የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ጁሊኡስዝ ጃኑስዝ በኮሶቮ ሓዋርያዊ ወኪል በመሆን የሚያገለግሉም ሲሆን፣ የሐዋርያዊ ወኪል ተልእኮአቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መዋቅራዊ አደረጃጀት በማስተግበር ሐላፊነት የሚገለጥ ሆኖ፣ ስለዚህ ይህ የአገልግሎት ኃላፊነት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የውስጥ ጉዳይ ያተኮረ ነው። ከሐዋርያዊ ልኡክ ኃላፊነት እርሱም ሕጋዊ ነክ ጉዳዮች እና የአገረ ግዛት ጉዳይ የማይመለከት እንዲሁም ዲፕሎማሲያዊ ጥያቄዎችን የማያጠቃልል ኃላፊነት ጭምር መሆኑ በማብራራት፣ በክልሉ ለምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን የምእመናን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ከፍተኛ ፍላጎት ተገቢ መልስ እንዲያገኝ የሚደገፍ ኃላፊነት መሆኑ የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ ያብራራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.