2011-02-10 09:48:19

ኬኒያ፣ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ


እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. በኬኒያ ተካሂዶ የነበረው ሕዝባዊ ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ውጥረት እና ግጭት ሳቢያ ቤት እና ንብረታቸው ጥለው የተፈናቅሉት የአገሪቱ ዜጎች ወደ ክልላቸው ተመልሰው ዕለታዊ ኑሮአቸውን ዳግም እንዲመሩ በማድረግ ውሳኔ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው የኬኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የፍትህ እና የሰላም ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ዛከኡስ ኦኮት ፊርማ ያኖሩበት መልእክት በይፋ ማቅረቡ ሲገለጥ፣ በወቅቱ ተከስቶ በነበረው ግጭት ሳቢያ ከ 300 ሺሕ በላይ የሚገመት የአገሪቱ ዜጋ ለመፈናቀል እና ሌሎች ከሺህ በላይ የሚገመቱት ለሞት አደጋ ማጋለጡንም የጠቀሰው የኬኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ፣ አክሎ የተፈናቀለው ሕዝብ አለ ምንም ችግር ወደ መጣበት በሚገባ ይሸኝ እና እለታዊ ኖሮው ዳግም ለመገንባት የሚያስችለው መሠረታዊ ድጋፍ ይቀርብለት ዘንድ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ሕገ መንግሥት በማክበር እና ፍትሕ በማስቀደም ብቻ የዜጎች ሰላም እና ጸጥታ ዋስትና ማረጋገጥ እንደሚቻል ያመለከተው ሐሳብ የኬኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ በትክክል ለአገሪቱ ርእሰ ብሔር እና መራሔ መንግሥት የሚመለከት ሲሆን፣ በአገሪቱ ተከስቶ ለነበረው ግጭት ተጠያቂዎች ለይቶ ለፍርድ ለማቅረብ ዓለም አቀፍ የአያው ፍርድ ቤት ያጠናቀረው ሰነድ በትክክል ተጠያቂ ከሆኑት ውስጥ በአሁኑ ወቅት በኬኒያው መንግሥት በሃላፊነት የተቀመጡት እና የቀድሞ ሚኒስትር እና የፀጥታ ኃይል አባላት ዋና አዛዥ የሚገኙባቸው ሲሆን፣ የኬኒያው መንግሥት ይኸንን ወደ ፍትሕ የሚያሸጋግረው ውሳኔ ይስማማበት ዘንድ ብፁዓን ጳጳሳት ባስተላለፉት መልእክት ጥሪ አቅርበዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.