2011-02-10 09:49:57

ሱዳን፣ ያለድንበር የሐኪሞች ማኅበር ጥሪ


ባለፉት ሁለት ውራት በሰሜናዊ የዳርፉር ክልል በሱዳን መንግሥት ወታደሮች እና በተቃዋሚ ታጣቂ ኃይሎች መካከከል በተካሄደው ግጭት ሳቢያ በብዙ ሺሕ የሚገመቱ የክልሉ ነዋሪዎች ቤታቸውን እና ንብረታቸው ጥለው ለመፈናቀል አደጋ መጋለጣቸው እና ለተወሳሰበ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙም አለ ድንበር የተሰኘው የሐኪሞት የግብረ ሠናይ ማኅበር የሰብአዊ አደጋ ማስጠንቀቂያ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሻንጊል ቶባያ በዳርአልሳላም እና በታቢት የሚገኙት የዳርፉር ተፈናቃይ ዜጎች ያለው የሰብአዊ ሁኔታ እጅግ የሚያሳብ ከመሆኑም ባሻገር፣ ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑት መሠረታዊ እርዳታ ባስቸኳይ ካላገኙ ለከፋ እና ለተወሳሰበ አደጋ እንደሚጋለጡ ያለ ድንበር የሐኪሞች ማኅበር ጥሪ ያመለክታል።

እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር በክልሉ ተከስቶ የነበረው ግጭት ብዙ ሕዝብ ለስደት እና ለመፈናቀል አደጋ መዳረጉ እና እነዚህ በሻኤሪያ ክልል ባለው ጊዚያዊ መጠለያ የሚገኙት ተፈናቃዮችን ለመርዳት በሱዳን ከ 1979 ዓ.ም. የሰብአዊ እርዳታ እና የጤና ጥበቃ እርዳታ በማቅረብ ላይ የሚግኘው ያለ ድንበር የሐኪሞች ማኅበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.