2011-02-10 09:43:12

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ የአቢያተ ክርስትያን ውህደት


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ዳሪዩስ ኮዋልቺዝክ ዘወትር ማክሰኞች በጣልያንኛ ቋንቋ ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የማይሻሩ ውሳኔዎች በማስደገፍ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላንትና ሁለትኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 28 ቀን 1965 ዓ.ም ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ያጸደቁት ኖስትራ አኤታተ - ያለንበት ዘመን የተሰኘው ድንጋጌ መሠረት ባቀረቡት አስተምህሮ፣ ሁሉም ሃይማኖቶች እኵል ናቸውን፣ ሁሉም ሃይማኖቶች እውነተኞች ናቸውን? የሚለውን ጥያቄ በማስቀደም እንዲሁም ሁሉም ሃይማኖቶች እኩል አይደሉም ሁሉም ሃይማኖቶችም እውነተ እንዳልሆኑ ድንጋጌው በማስደገፍ መልስ ከሰጡ በኋላ አሊታዊ መልሱን ሲያስረዱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው ካሉ በኋላ ከዚህ ጋር በማያያዝ ጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ እግዚአብሔር አይደለም ለማለት ይቻላልን? ሁለቱ አገላለጦች አንድ ናችው፣ በሌላው መልኩም እውነትን የሚገልጡ ናቸው ብሎ ማቅረቡ እና በእኵል ደረጃ ማስቀመጥ ግን ሥህተት ነው።

ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከሌሎች ክርስትያን ካልሆኑት ሃይማኖቶች ጋር የምታከናውነው ግኑኝነት እና የምታካሂደው ውይይት፣ እውነተኛይቱ ቤተ ክርስትያን እግዚአብሔር በፍቃዱ ለሁሉ ሰው ዘር ያስተዋዋቃት ስትሆን እርሷም እውነተኛው ሃይማኖት የሚኖርበታ ካቶሊክ እና ሓዋርያዊት ቤተ ክርስትያን መሆንዋ ካለው ግንዛቤ እና ውሳኔው የሚመነጭ መሆኑ በማብራራት ውሳኔው በቁጥር ሁለት ላይ አክሎ፣ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሌሎች ሃይማኖትች ዘንድ ያለው እውነት እና ቅዱስ ነገር አታገልም፣ ምክንያቱም በነዚህ ሃይማኖቶች አማካኝነት የሚገለጠው እውነት ከሚያበራው ጮራ የመነጨ ሲታፌአዊ እውነት ስላለ ነው። ሆኖም ይህ ግንዛቤ ቤተ ክርስትያን መንገድ እውነት እና ሕይወት (ዮሐ. 14፣ 6) የሆነውን በቀጥታ ትሰብካለች፣ ይህ አገላለጥ ክርስትያን ያልሆኑት ሃይማኖቶችን የሚመለከት ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚሉትም ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር የሚደረገው ውይይት ስለ ነጻነት እና እውነት ካለን ከጋራ አካፋይ ከሆነው መረዳዳት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።

የአብርሃም ዘር ከሚለው መንፈሳዊነት ጋር የተቆራኘው የአሁድ ሃይማኖት በመግለጥም የክርስትናው እና በአህይሁ ሃይማኖት መካከል ያለው ግኑንነት ውሳኔ በማብራራት፣ ጸረ ሴማዊነት ተግባር ቤተ ክርስትያን በማውገዝ ሆኖም የሁለቱ ሃይማኖቶች የጋራው ግኑኝነት በአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ ከደረሰው በደል እና እልቂት ላይ ብቻ የታጠረ ወይንም የተመረኮዘ ሳይሆን በቲዮሎጊያዊ እና ሥነ መጽሓፍ ቅዱሳዊ የምርምር ጥናት ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበት በውሳኔ ቁጥር አራት ላይ የተመልከት መሆኑ እንዳለበት በማብራራት የሰጡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.