2011-02-09 16:02:37

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፦ ለምግባረ ፍቅር ማነጽ


የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ከትላንትና በስትያ በቫቲካን ዓመታዊ ምልአተ ጉባኤው መጀመሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖን ግሮቾሎቭስኪ የተመሩትን ተጋባእያን ተቀብለው፦ ማነጽ የፍቅር ተግባር፣ ለሚሠዋ ፍቅር የሚገዛ ሊቅነት ማሠልጠን፣ ኃላፊነት እራስን ለዚህ ተግባር በሙላት ቃልን እና ተግባርን የሚያጣምር ንቃት ማለት መሆኑ የሚያስረዳ መሪ ቃል መለገሳቸው እና ባሰሙትm ንግግር ጉባኤው የሚወያይባቸው ዋና ዋና ነጥቦች ማእከል በማድረግ ሰፊ ማብራሪያ እና መሪ ቃል መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖን ግሮቾለቪስኪ ስለ ጉባኤው እና የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መሪ ቃል በማስደገፍ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የማስተማር ተግባር፣ የሕንጸት ተልእኮ ማከናወን የቤተ ክርስትያን ተቀዳሚ ዓላማ መሆኑ በማብራራት፣ በዚህ በምንኖርበት ወቅታዊው ዘመን ማስተማር ቀላል ተልእኮ እንዳልሆነ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለተጋባእያኑ በሰጡት መሪ ቃል የጠቀሱት ነጥብ መሆኑ ገልጠው፣ ምክንያቱም የወቅቱ ማኅበረሰብ ማመን አለማመን ያው ነው፣ እሴቶች ብሎ ነገር የለም፣ ሁሉም የተፈቀደ ነው የሚለው ህልዎተ እግዚአብሔር የሚቀስረው የኅሊና ድምጽ ግድ የማይለው ተዛማጅ ባህል እማኔ በማድረግ የሚኖርበት በመሆኑ ለኵላዊ እውነት ግንዛቤም አስተውሎም የማይሰጥ ሆኖአል፣ ይኸ ሁሉ አወዛጋቢው ባህል የማስተማር ተግባር እጅግ አስቸጋሪ ሙያ እና ተልእኮ እንዲሆን አድርጎታል። ከዚህ አንጻር አስተማሪነት እና ማስተማር በቀላል የሚታይ ተልእኮ እና ኃላፊነተ እንዳልሆነ ለመረዳቱ አያዳግትም። ስለዚህ ሁሉም በተዛማጅ ባህል ሥር የሚገለጥ ከሆነ ማስተማሩ ጥቅም የሌለው ሆኖ ይቀራል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዳሉት ማስተማር ወይንም አስተማሪነት የሚሠዋ ፍቅር ተግባር ነው። ግኡዝ እውቀት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ከሕይወት ጋር ለተቆራኘ ተግባር ማዘጋጀት እና የላቀ ክብር የሚመሰከርበት የእውነት መድረክም ነው። ስለዚህ በተደጋጋሚ ቅዱስነታቸው ለሚሠዋ ፍቅር የሚገዛ ሊቅነት በማለት ሲገልጡ፣ ማስተማር ወይንም በሕንጸት ተልእኮ መሳተፍ ለዚህ ተልእኮ እራስን በሙላት ለማቅረብ አሳልፎ መስጠትን እና ቃል እና ተግባር የሚያጣምር ንቃት እንደሚጠይቅ ለማስገንዘብ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል ግሮቾለቪስኪ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታንች ስለ ድረ ገጽ እና ደረ መሥክ እንዲሁም የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንጸትም በመጥቀስ ጉባኤው በነዚህ ሁለት ነጥቦች ጭምር የሚወያይ መሆኑ በመግለጥ፣ የድረ ገጽ ሊቃውንት በጉባኤው ተገኘተው ሰፊ አስተምህሮ በመስጠት፣ ይህ አዲስ መሣሪያ የሚሰጠው አቢይ ጥቅም በመለየት ለኢንዳስትሪው ኤኮኖሚ ለባህላዊ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ለአስፍሆተ ወንጌል ለትምህርተ ክርስቶስ የሚያገለግል መሆኑ በጥልቅ ይተነተናል። ስለዚህ ውሉደ ክህነት እና የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በዚህ የእወቅት ዘርፍ ተገቢ ሕንጸት እዲያገኙ መደገፍ፣ አስፈላጊ መሆኑ ገልጠው፣ የዚህ አዲስ መሣሪያ የተጠቃሚነት ተግባር በንቃት እና በጥንቃቄ እና በማስተዋል መጠቀሙ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስ አባታችን አስምረውበታል ይህ ነጥብ ጉባኤ በስፋት የሚዳስሰው ጉዳይ እንደሚሆን ብፁነታቸው አብራርተዋል።

በመጨረሻም ይህ ዓመታዊ ምልአተ ጉባኤ በአሁኑ ወቅት የተዛባውን የፍልስፍና ጽንሰ-ሐሳብ በጥልቀት በመዳሰስ፣ ፍልስፍና በተቆነጸበ ጥራዝ ነጠቃዊ አገላለጥ ሳይሆን ቃሉ እንደሚለው ለጥበብ ፍቅር ማለት በመሆኑ ለሁሉም የትምህርት ዘርፎች መሠረት ነው። ሁሉም ለጥበብ ካለው ፍቅር በመንደርደር በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ለመሰልጠት መሻት አለበት። ኵላዊ እና ሁሉም በሁሉም እውነትን ለመለየት የሚያግዝ የጥበብ ፍቅር ነው ካሉ በኋላ፣ ጉባኤው በፍጻሜ የሚያቀርበው የማጠቃለያ ሰነድ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጥልቅ ጥናት ተደርጎበት በሚሰጡት ፈቃድ መሠረት ሥልጣናዊ ትምህርታቸ ታክሎበት ለንባብ እንደሚቀርብ ገልጠው የሰጡትን ቃል ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.