2011-02-07 13:03:13

ዳካር፦ ዓለም አቀፍ ማኅበራዊ ጉባኤ “ስለ አፍሪቃ ልማት”


ትላትና በሰነጋል ርእሰ ከተማ ዳካር ዓለም አቀፍ ማኅበራዊ ጉባኤ በአፍሪቃ ልማት ላይ በማተኮር መጀመሩ ሲገለጥ፣ ይህ ከ 300 በላይ የሚገመቱ ርእሰ ጉዳዮች የሚዳስስ ከ 60 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ተጋባእያን የሚያሳትፍ ጉባኤ፣ ዓለም አቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ፣ የአካባቢ እና የተፈጥሮ ደህንነት በደቡብ እና በሰሜኑ ዓለም ብቻ ሳይሆን በድቡባውያን ክልል አገሮች RealAudioMP3 ዘንድ መደጋገፍ እና ትብብር ለሰው ልጅ እድገት የደቡብ ዓለም ተሳትፎ በጠቅላላ በአፍሪቃ እና ስለ አፍሪቃ ኤኮኖሚ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ አስተዋጽኦ ጉዳይ ላይ በማነጣጠር የሚከናወን መሆኑ የአፍሪቃ የገበሪዎች እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ማማዱ ቺሶክሆ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

የአፍሪቃ የግብርናው ኤክኖሚ በተለይ ደግሞ ይህ የቤተሰብ የግብርና ኤኮኖሚ በአፍሪቃ 85% የአፍሪቃ የግብርናው ኤክኖሚ የሚሸፍን መሆኑ ጠቅሰው፣ 55% የአፍሪቃ ሕዝብ በዚህ የግብርናው ኤክኖሚ በሚያስገኘው ገቢ ዕለታዊ ሕይወቱን የሚመራ ሲሆን፣ የግብርናው ኤኮኖሚ ጥያቄ የበለጸገው ዓለም በሕግ እንዲመራ ያደረገ መሆኑ አብራርተው፣ ሆኖም ግን ምግብ ለሕይወ አስፈላጊ ከሆኑት መሠረታውያን ፍላጎቶች ውስጥ ተቀዳሚ ሲሆን፣ ስለዚህ እያንዳንዱ አገር በዚህ ኤኮኖሚ ረገድ ዋስትና ለማረጋግጥ የሚችል መሆን አለበት። በምግብ አቅም እራሱን ያልቻለ አገር፣ የዜጎቹ እና የአገሪቱን ድኅንነት እና ኅልውና ዋስትና ማረጋገጥ አይችልም ብለዋል።

አፍሪቃ የአፍሪቃውያን ነች ሲባል በአፍሪቃውያን ትብብር አፍሪቃውያን በሚያሰኛቸው የጋራ ክብር የጸና መደጋገፍ መቀራረብ ለአፍሪቃ እጅግ ወሳኝ መሆኑ ለመግለጥ ነው። ይህ የዳካር ዓለም አቀፍ የማኅበራዊ ጉባኤ የአፍሪቃ ኅላዌ፣ እና የአፍሪቃ የመጻኢው ኅላዌ ያጣመረ እቅድ በኤኮኖሚው በማኅበራዊው እና በፖለቲካው ዘርፍ እጅግ ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ የአፍሪቃ የግብርናው ኤክኖሚ የሚከተለው ባህላዊ የሙያ ሥልት በእድ ጥበብ የተደገፈ መሆን አለበት፣ ስለዚህ ወቅታዊነት ያለው ማድረግ፣ የአፍሪቃ የፖለቲካ አካላት አፍሪቃ እንደ ምርት ለገበያ ማቅረብ የሚከተሉት ጸረ አፍሪቃዊ ተግባራቸውን ማቋረጥ ይኖርባቸዋል። ይህ ደግሞ የአፍሪቃ የምርት አቅርቦት አቅም በሙሉ መብት እና ፈቃድ ከሌሎች አገሮች ጋር መደራደር እንጂ ዝቅ አድርጎ በመመልከት የሌሎች ውሳኔ በማስከበር የሌሎች ፍላጎት ለማርካት እሺ ባይ ክፍለ አለም መሆኑ የለበትም፣ ይህ ደግሞ ለአፍሪቃ መሪዎች በቀጥታ የሚመለከት ጉዳይ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም በአፍሪቃ ተቀባይነት ያለው የኤኮኖሚ እቅድ የሚከተል የአፍሪቃ ልማት የሚያነቃቃ የጋራ መርሃ ግብር ወሳኝ ነው ካሉ በኋላ የግብርና ማኅበራት መደገፍ በአፍሪቃ አገሮች መካከል የምርት አቅርቦት ልውውጥ ማሳየል የኅብረ ስነ ሕይወት ሃብት ማክበር ባህላዊ የልማት ዘርፍ መለያ የመሳሰሉትን በማክበር እና መሻሻል የሚገባው ለጋራ ጥቅም አልሞ በማሻሻል የአፍሪቃ አገሮች የእርስ በርስ መቀራረብ ማጎልበት ለአፍሪቃ ልማት መሠረት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.