2011-02-07 13:04:32

ስፐይን፦ “መጽሓፍ ቅዱስ በቤተ ክርስትያን ሕይወት”


እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ታሕሳስ ወር ይፋዊ የሆነው የስፐይን ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ይፋዊ መጽሓፍ ቅዱስ መሠረት በማረግ እ.ኤ.አ. እስከ ጥር 9 ቀን 2011 ዓ.ም. የሚዘልቅ የስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መጽሓፍ ቅዱስ በቤተ ክርስትያን ሕይወት በሚል ርእስ ሥር የተመራ ስለ ቅዱስ መጽሓፍ እና አገላለጥ እንዲሁም ትርጓሜው፣ መጽሓፍ ቅዱስ በሊጡርጊያ ሕይወት፣ RealAudioMP3 በውሉደ ክህነት በምእመናን ሕይወት በሚሉት ንኡሳን ርእሰ ጉዳዮች የተሸኘ ዓውደ ጥናት ከጥር 6 ቀን ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው።

በስፓንሽ ቋንቋ አዲስ ትርጓሚ ቅዱስ መጽሓፍ የክርትያን ደራስያን ቤተ መጻሕፍት ማተሚያ ቤት አማካኝነት ታትሞ መቅረቡ የሚዘከር ሲሆን፣ ይህ ትርጉም ያዛሬ 10 ዓመት በፊት ተጀምሮ በጥልቅ ጥናት የተደገፈ የቅዱስ መጽሓፍ ሊቃውንት እና ብፁዓን ጳጳሳት የቅዱሳት ምሥጢራት እና የሥነ አምልኮ ሊቃውንት የላቲን እና የግሪክ እንዲሁም የኢብራይስጥ ቋንቋ ሊቃውንት በማሳተፍ የተደረሰ መሆኑ ሲገለጥ፣ የአንድ ቋንቋ ባህርይ እና ሂደታዊ ለውጡ እና እድገቱን የሚያጠና የሥነ እውቀት ሊቃውንት የሥነ ቅዱስ መጽሐፍ ሥነ ጽሑፋዊ እና ቲይሎጊያዊ ተመራማሪዎች ጭምር በማስተባበር እና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሊጡርጊያ መጽሓፍ ሕዳሴ ውሳኔ በማስደገፍ ጥልቅ ጥናት የተደረገበት አዲስ ሕትመት መሆኑ ሲገለጥ፣ ይኸንን መጽሓፍ ቅዱስ በቤተ ክርስትያን ሕይወት በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ያለው አውደ ጥናት በንግግር የከፈቱት የስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪይ ኣሩኮ ቫረላ ሲሆኑ፣ መጽሓፍ ቅዱስ በቤት ክርስትያን ሕይወት የተሰኘው የአውደ ጥናቱ ዋናው ርእስ በማስደገፍ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ምኅበር ኅየንተ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. የእግዚአብሔር ቃል በቤተ ክርስያን ሕይወት እና ተልእኮ በሚል ርእስ ሥር የተካሄደው የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዘጋቢ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦየለት አስተምህሮ እንደሚያቀርቡም ሲገለጥ፣ የስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኽዋን አንቶኒዮ ማርቲነዝ ካሚኖ መጽሓፍ ቅዱስ በስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ታሪክ በሚል ርእስ ሥር አስተምህሮ እንደሚያቀርቡም ተገልጠዋል።

የሥርዓተ አምልኮና የቅዱሳት ሚስጢራት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኽዋን ሚገል ግረነስከ መጽሓፍ ቅዱስ እና ሊጡርጊያ በሚል ርእስ ሥር፣ እንዲሁም የካቶሊክ ሃይማኖት ሥርወ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ልዊስ ፍራንሲስኮ ላዳሪያ ፈረር፣ መጽሓፍ ቅዱስ እና የቤተ ክርስትያን ሥልጣናዊ ትምህርት በሚል ራስ ሥር የፍትኅ እና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርኮሶን አስተምህሮ እንደሚያቀርቡም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.