2011-02-07 13:02:16

ሕንጸት ስለ ምሉዕ/ ተሟላ ሕይወት


ከትላንትና በስትያ የኢጣልያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አነሳሽነት በኢጣሊያ 33ኛ የሕይወት ቀን በብሔራዊ አቀፍ ደረጃ ተከብሮ መዋሉ ተገለጠ። ይህ ሕንጸት ስለ ምሉዕ/ የተሟላ ሕይወት በሚል መርኅ ቃል ሥር የተከናወነው የሕይወት ቀን በመላ ኢጣልያ የሕይወት ጉዳይ በሚመለከቱ እና የሕይወት ባህል በሚያነቃቁ የተለያዩ አውደ ጥናቶች እና ትርኢቶች ጭምር RealAudioMP3 ተደግፎ መከናወኑ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

ስለ ሕይወት ጉዳይ ተሟጋች እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር የኤውሮጳ የሕዝብ ተወካዮች ምርክ ቤተ አባል ካርሎ ካሲኒ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ብሔራዊው የሕይወት ቀን በኢጣሊያ ጽንስ ማስወረድ በሕግ የተፈቀደ ሆኖ እርሱም ጽንስ ማስወረድ ከወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ተነስቶ፣ በሕግ የማያስቀጣ ድርጊት ነው ተብሎ ከጸደቀበተ ዓመት ወዲህ ይኸንን የሞትን ባህል ለመቃወም እና የሕይወት ባህል ለማነቃቃት ታቅዶ የተጀመረ የሕይወት ቀን መሆኑ በማብራራት፣ ዘንድሮ ሕንጸት ስለ ምሉዕ ሕይወት እርሱም ሕይወት ከመጸነስ እሰክ ባህርያዊ ሞት በሙላት እንዲከበር የሚጠራ እና ማኅበራዊ እና ግላዊ ኅሊና በዚህ የሕይወት ባህል እንዲታነጽ በሚያነቃቁ እቅዶች ታስቦ መዋሉ አመልክተዋል።

በመገናኛ ብዙኃን ጭምር በአሁኑ ወቅት አብነተ እና አርአያ ሆነው የሚሰበኩት ጾታዊ ስሜት የሚያደናግር እና ቤተሰብ ግድ የማይል አሉታዊ መርሃ ግብሮች የሚያጎሉ በመሆናቸው ይኸንን ጸረ ሕይወት የሆነውን ባህል ደረቅ የሕይወት ባህል ደጋፊ በመሆን ተቃውሞ ማካሄድ ሳይሆን በሕይወት ባህል ዘርፍ ሕዝብን በማነቃቃት እና በማነጽ ባህላዊ ተቃውሞ በማከናወን ስለ ሕይወት ጥበቃ እና አክብሮት መንቀሳቀስ ወሳኝ መሆኑ የሚገልጥ ሐሳብ እጅግ የጎላበተ ዕለት ነው ብለዋል።

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ኤቫንጀሉም ቪተ-ወንጌላዊ ሕይወት በተሰኘው አዋዲ መልእኽታቸው አማካኝነት ሁሉም በጋራ የሕይወት ባህል እንዲገነባ እና በዚህ ዓለማ ሁሉም እንዲንቀሳቀስ አደራ ብለው እንደነበር ካሲኒ በማስታወስ፣ ሁሉም ቀድሞ የተወሰነ ነው ምንም ለማድረግ አይቻልም እየተባለ የሞት ባህል ጭምር ቅቡል አድርጎ የሚመለከት የደነዘዘ ባህል በንቃተ ኅሊና እና በሥነ ባህል መግጠሙ እጅግ ወሳኝ ነው። የሕይወት ትርጉም በተመለከተ ሥነ ሰብእ የሚመለከተው ጥያቄ፣ በማጤን የሕይወት ክብር ለይቶ በማጉላት ሁሉም ሃይማኖት በጋራ ማስገንዘብ እና ማስተማር ይጠበቅባቸዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.