2011-02-04 15:37:59

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃን ለሁሉም አድርሱ


የአማኑኤል ማኅበረሰብ መሥራች ፒየረ ጉርሳት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት 20ኛ ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና የማኅበሩ አባላት ተቀብለው በማነጋገር መሪ ቃል መስጠታቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን በዚህ በምንኖርበት ዘመን በሚሥጢረ ቅዱስ ቁርባን ላይ የጸና በእውነተኛ ሕይወት የሚመራ የታደሰ ንቁ ሐዋርያዊ አገልግሎት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ በማብራራት፣ የግል እና የማኅበራዊው ሕይወት ጥልቅ መንፈሳዊነት በጥልቅ ለመረዳት እና ለመለየት እና ቃለ እግዚአብሔር ለማበሠር በቅዱስ ቁርባን RealAudioMP3 ፊት የሚደረገው አስተንትኖ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በዚህ በተደናገረው እና የሕይወት አመክንዮ ለመለየት ጥረት በሚደረግበት ዓለም የክርስቶስ ብርሃን ማበሠር እጅግ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ነው። ከዚህ ሓሳብ በመንደርደር ሁሉ ቀናተኛ ልኡከ ወንጌል ይሆን ዘንድ አሳስበዋል። ቃል እግዚአብሔር ለማበሠር የተጠሙ እንሁን ብለዋል። በዚህ በምንኖርበት ዘመን በተለይ ደግሞ በቤተሰብ በወጣቱ የኅብረተ-ሰብ ክፍል እና ማኅበረ ምሁራን ዘንድ ቃል እግዚአብሔር ማበሠር አንገብጋቢ ጥሪ መሆኑ አብራርተዋል።

የቁምስናዎች ንቁ የወንጌል አብሳሪያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ጥሪያቸውን ዳግም በማደስ፣ መንፈሳዊ እና ልኡከ ወንጌል የጥሪ ሃላፊነታቸውን በጥልቅ የመለየቱ ሂደት ማጎልበት ይኖርባቸዋል ካሉ በኋላ፣ የማኅበረሰብ አማኑኤል አባላት ካህናት ደናግል እና ዓለማውያን ምእመናን ወደ ቤተ ክርስትያን የሚመለሱት የቤተ ክርስትያን ልጆች ለሚሹት ጥልቅ ትምህርተ ክርስቶስ በቃል እና በሕይወት አብሣሪያን በመሆን እምነታቸው በእውነተኛው ቲዮሎጊያዊ ቤተ ክርስትያናዊ እና ቅዱሳት ሚሥጢራዊ አድማስ ያለው ሆኖ እንዲኖር እና በማኅበረ ክርስትያን መካከል ውህደት እንዲኖር ይደግፉ ዘንድ አሳስበዋል።

ይህ ውህደት ከተራው ስለ ሌላው ማሰብ፣ መቻቻል ከሚለው ሃሳብ ላይ የጸና ሳይሆን፣ ከክርስቶስ ጋር ከሚጸናው ውህደት እና በጋራ እና በግል ከሚሰጠው አገልግሎት የሚመነጭ ሆኖ ማንኛውም ስብአዊ ግኑኝነት የሚያነቃቃ ኅያው የወንድማማችነት ፍቅር መስካሪ ይሆኑ ዘንድ ለአማኑኤል ማኅበረ-ሰብ አባላት አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.