2011-02-04 15:39:23

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ መናንያን እና የሐዋርያዊ ማኅበረሰብ አባላት የወንጌል መሥካሪያን


የላቲን ሥርዓት አምልኮ ግፃዌ የምትከተል ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ከትላትና በስትያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእየሩሳሌም ቤተ መቅደስ የቀረበበት ዕለት በተከበረበት ዕለት ከዚሁ በዓል ጋር በማያያዝ ሥነ ቲዮሎጊያዊ እና መንፈሳዊ ትርጉም መሠረት በማድረግ ታስቦ የዋለው የመናንያን የገዳማውያን እና የሐዋርያዊ አገልግሎት ጥሪ ቀን ምክንያት፣ ቅዱስ አባታችን የመናንያን ማኅበር አባላት ካህናት እና ደናግል የተሳተፉበት ከትላንትና በስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሁለተኛ ጸሎተ ሠርክ መምራታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ። RealAudioMP3

ይህ የላቲን ሥርዓት አምልኮ ግፃዌ የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ያከበረቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቀደስ የቀረበበት ዓቢይ በዓል በሌላ መልኩ በዓሉ የመናንያን እና የገዳማውያን እንዲሁም የሐዋርያዊ አገልግሎት ማኅበር አባላት በዓል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ሁለተኛ ጸሎተ ሠርክ መርተው ባሰሙት ስብከት፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን እና ኅብረሰተሰብ ልሙድ እና ተቀባይነቱ እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለው ሃይማኖት ከማኅበራዊ ሕይወት የመነጠሉ እና የማግለሉ ተግባር አሳሳቢነቱ እና መሠረታውያን እሴቶችን በማናጋት እና በመተካት ላይ ያለው ማመን እና አለ ማመን ሁሉም ያው ነው የሚለው የጸረ እሴቶች ተዛማጅ ባህል እየተስፋፋ ባለበት ዓለም፣ መናንያን ካህናት ደናግል እና የሐዋርያዊ ማኅበረሰብ አባላት ያልተዛባ ቃል እና ሕይወት ያጣመረ ግልጽ እና ብሩህ የክርስትና ሕይወት መስካሪያን ይሆኑ ዘንድ አሳስበዋል።

ድኽነት ተአዝዞ እና ድንግልና በመቀበል እና ለዚህ ጥሪ እሺ በማለት የሚኖሩ ገዳማውያን መናንያን ካህናት ደናግል እና ወንድሞች የሰው ልጅ ልብ እና ቀልብ የሚከተለው መንገድ እንዲለይ እና ወደ አዲስ ኪዳን ሕይወት ያቀና እንዲሆን በማድረጉ ዓላማ ይተጉ ዘንድ ቅዱስ አባታችን አደራ በማለት፣ እውነተኛ ብርሃን የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማበሠር የሁሉም ካህናት ደናግል እና ወንድሞች ተልእኮ መሆኑ በማብራራት፣ በሚፈጽሙት ወንጌላዊ ማህላ ሐዋርያዊ ተግባር፣ ገደብ የሌለው የመላ ሕይወት ኃላፊነት በጋለ ጽናት ካለ ማወላወል እውነት እና የእውነት ውበት አብሣሪያን መሆን ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዓለም የእግዚአብሔር ብርሃን ቦግ ብሎ እንዲታይ በማድረግ ተልእኮ ለማገልገል ሕይወታቸውን ለእግዚአብሔር የሚሰው መናንያን ገዳማውያን ካህናት እና ደናግል ሕዝበ እግዚአብሔር ሊከተለው ለሚገባው ሕይወት አርአያ ናቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ተአዝዞ እና መሥዋዕት ኅያው እግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑ ያረጋገጠበ ዕለት ሲታሰብ፣ መናንያን በጠቅላላ በመካከላችን ለእግዚአብሔር መንግሥት ኅላዌ የርቱዕ አንደበት ትእምርት ናቸው። ስለዚህ ካህናት ደናግል በጠቅላላ መናንያን ሕይወታቸው ለክርስቶስ እና ለቤተ ክርስትያን እጅ ሲያስረክቡ የሰውል ልጅ ሊረዳው በሚችለው ኅያው አንደበት በመካከላቸው የእግዚአብሔር ከኛ ጋር መሆኑ መስካሪያን ናቸው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.