2011-02-04 15:40:43

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ማዘጋጃ መሪ ቃል


ዩካት በሚል መጠሪያ እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ለካቶሊክ ወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ ደግፊ ሰነድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመግቢያ ጽሑፍ ያስቀደመ 300 ገጽ አዘል የወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ በቅርቡ ለንባብ እንደሚቀርብ ሲገለጥ፣ ይህ ጥያቄ እና መልስ በማስከተል የተደረሰ የክርስትና እምነት ለማወቅ የሚያግዝ እና የክርስትና እምነት መለያ የሚያሳወቅ መጽሓፍ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ነሓሴ ወር በማድሪድ ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አቢይ ድጋፍ ይሆንም ዘንድ በሰባት ቋንቋዎች RealAudioMP3 ታትሞ እንደሚቀርብ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ ለወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ አስፈላጊ መሆኑ ቀድሞ በማድረግ የለዩት የኦስትሪያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሾንቦርን መሆናቸው ሲገለጥ፣ እነዚህ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ምክንያት የሚገናኙት እንዴት መዘጋጀት እንዳለባቸው እና እምነትን ባልተወሳሰበ ግልጽ በሆነ ሐሳብ የሚያስረዳ ወጣቱ አቢይ እና ጥልቅ እምነት ቀለል ባለ መንገድ እንዲገነዘብ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ይኽ ዩካት በሚል ርእሥ ሥር የሚታተመው የወጣቶች ትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ፣ ምንን ነው የምናምነው፣ የክርስትናው ምሥጢር በዓለ ሂደቱ፣ የክርስቶስ ሕይወት እና ጸሎት በክርስትናው ሕይወት በተሰኙት አራት ምዕራፎች የተከፋፈለ መሆኑ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመግቢያው ጽሑፋቸው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ መሠረት ያደረገ የሁለት ሺሕ የቤተ ክርስትያን ሕይወት የሚያንጸባርቅ በተለያየ መልኩ ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍል እንደ ክፍለ ምደባው መተንተን እና ለይቶ በማቅረብ ማስረዳት አስፈላጊ መሆኑ በማስመር፣ መሠረታዊው የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ትምህርተ ክርስቶስ የሚያብራራ ነው። ስለዚህ ስለ ሌሎች የሚናገር ልበ ወለድ መጽሓፍ ሳይሆን ለእያንዳንዳችን የሚናገረ ስለ እያንዳንዳችን ዕድል ፈንታ የሚያወሳ የትምህርተ ክርስቶስ መጽሓፍ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመግቢያው ጽሑፍ በማብራራት፣ በተለያዩ ወቅት እና መልክ የክፋት መንፈስ ዓለማችን ምንኛ እንዳናጋ እና ይህ የክፋት መንፈስ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ጭምር ሰረጎ በመግባት እምነትን ለማናጋት ሙክራ ያደረገ ቢሆንም ቅሉ ወጣቱ በዚህ ሳይሰናከል እና ከእግዚአብሔር ለሚሸሽ ሕይወት ሳይጣደፍ የክርስቶስ አካል የሆነቸው የቤተ ክርስትያን አካል መሆኑ ተገንዝቦ ቤተ ክርስትያናን በማፍቅር እውነተኛ መልክዋን በመለየት በክርስቶስ ፍቅር ያፈቅርዋትም ዘንድ ተጠርተዋል በማለት ምዕዳን ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.