2011-02-04 15:42:52

ሩሲያ፣ ቤተ ክርስትያን በማኅበራዊ ሕይወት


የመላ ሩሲያ እና የሞስኮ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪል የሩሲያ ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን እንዲመሩ የተሾሙበት ሁለተኛው ዓመት ምክንያት ሞስኮ በሚገኘው በመድኃኔ ዓለም የኦርቶዶክስ ካቴድራል መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፣ በዘመናችን የክፋት መንፈስ ከምን ጊዜም በበለጠ አይሎ የሚንቀሳቀስበት በተለያየ መልክ ጦሩን በማሰማራት RealAudioMP3 በተለይ ደግሞ ጸረ ቤተ ክርስያን የሆኑንት አመለካከት እና አካላትን በማነቃቃት እምነት የግል ነው እንዲባል እና ይኽ ሐሳብ እውነት እና መንገድ በማድረግ እምነት ከማኅበራዊ ሕይወት እንዲገለል እያደረገ መሆኑ በመጥቀስ፣ ፍች፣ ጽንስ ማስወረድ፣ የሰው ክብር ልክ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ እየተስፋፋ ዓለማችን እያናጋ ነው ካሉ በኋላ፣ ይኸንን የክፋት መንፈስ ለመገሰጽ እና ለማሸነፍ ብቸኛው መንገድ በቃል እና በሕይወት እምነትን በማኅበራዊ ሕይወት መኖር እና መመስከር ነው እንዳሉ ኤሺያን ኒውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የሩሲያ ሕዝብ አስተያየት ጉዳይ የሚያጠና ማእከል የጠቀሰ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት፣ በሩሲያ ሁለት ሶስተኛው ቤተ ክርትያን በማኅበራዊ ሕይወት አቢይ አስተዋጽኦ እንደምትሰጥ እና አስፈላጊ መሆኑ እንደሚያምን ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.