2011-02-02 15:29:34

የኤውሮጳ ህብረት፦ የሃይማኖት ነጻነት ውሳኔ ሰነድ


የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምነት በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው ጸረ ክርስትያን ዓመጽ መሠረት በማድረግ ሰፊ ውይይት በማካሄድ እና በዓለማችን ለስደት እና አድልዎ ለአመጽም ከተጋለጡት የተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ለከፋው ዓመጽ የተጋለጠው የክርስትናው እምነት መሆኑ በመገንዝብ፣ በክርስትያኖች ላይ የሚጣለውን ዓመጽ ርእሰ ጉዳይ በማድረግ ሰፊ ውይይት RealAudioMP3 በማካሄድ የሃይማኖት ነጻነት በሚል ርእስ ሥር ያጸደቀው ውሳኔ ለኤውሮጳ ኅበረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ማስተላለፉ እና ይኽ ምክር ቤት የውሳኔው ሰነድ መሠረት በማድረግ በመወያየት በተራው ባጸደቀው ውሳኔ፣ የክርስትያኖች ስደት እና መከራ የሚለው አገላለጥ ጠቅላለ ባለ መልኩ የአማኒያን ስደተ እና መከራ በሚል መጠሪያ እንዲተካ ማድረጉ ለማወቅ ሲቻል የኅብረቱ ውሳኔ ሙሉ በሙሊ ለማጽድቀ ያለው እቅድ መሸጋገሩ ተገልጠዋል።

ይኸንን ውሳኔ መሠረት በማድረግ የሥነ ሕግ ሊቅ ፕሮፈሶር ካርሎ ካርዲያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በዓለማችን በሥፋት ለስደት እና ለዓመጽ እንዲሁም ለአድልዎ ተጋልጦ የሚገኘው ማኅበረ ክርስትያን መሆኑ እውነት ሆኖ እያለ፣ ነገር ግን ይኸንን እውነት ለመግለጥ ለምን እንዳስፈራ ይገርማል። ኤውሮጳ ክርስትያናዊ ባህል መሠረትዋ መመስከር ማለት ሌላውን ባህል ማግለል ሳይሆን በትክክል እራስዋን እንድታውቅ እና ለሌላው ለምሳወቅ ለምታደርገው ፖለቲካዊ ባህላዊ እና ማኅበራዊ ጥረት አቢይ እና ግልጽ ድጋፍም ነው። መሠረቱን በመካድ ሌላውን ተመስሎ ለመኖር የሚደረገው ጥረት ሌላው በሚገባ ለመረዳት እና ለመቀበል መሠረት የሌለው ባዶ ይሆናል ብለዋል። ሌላው ለማወቅም ያዳግታል።

ይኽ የኤውሮጳው የተዛባ እና እርግጠኝነት አልቦ ምርጫ የአሁን ሳይሆን የቆየ ነው። ስለዚህ የኤውሮጳ መሠረታውያን እሴቶች በሁሉም የዓለማችን ክልሎች እና በማንኛውም ወቅት ግልጽነት በተሞላው አሠራር መንከባከቡ እና መከላከሉ አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው። ስለዚህ የኤውጳው ክርስትያናዊ መሠረት ያለው ባህልዋ እውቅና መስጠት ማለት ለኤውሮጳ አቢይ ኃላፊነተ እና ከዚህ መሠረታዊ ባህልዋ ጋር የተስተካከለ ሕይወት ትኖር እና ታንጸባርቅ ዘንድ ትእዛዛዊ ግብረ ገብ ይሆንባታል፣ ስለዚህ ክርስትና የሚለው ቃል ባይጠቀስ ይበጃል ለሚለው አመለካከት ይገፋፋል ይኽ ግን ብርታት ሳይሆን ድክመትን ነው የሚያመለክተው ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልል ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.