2011-02-02 15:28:34

ብፁዕ ካርዲናል ፒያዘንቻ፦ ወንጌላዊ ልኡክነት የካህን ሕይወት


የካህን እውንተኛው መለያው በክህነት ዘንድ ያለው አውነተኛ ባህርይ የሆነው ወንጌላዊ ልኡክነት በቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስትያን ጋር በሚል ርእስ ሥር የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ለመላ ወሉደ ክህነት መልእክት ማስተላለፉ የሚዘከር ሲሆን፣ ሓዋርያዊ ቀናተኛ እና ልኡከ ወንጌል የካህን ማንነት መግለጫ ሲሆን፣ ካህን ትሪያ ሙነራ ማለት ሶስት የተግቡ ሥልጣን ወይንም ኃላፊነት እነርሱም አስተማሪ ቀዳሽ እና አስተዳዳሪ መሆናቸው የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ለወሉደ ክህነት ባስተላለፈው ዓዋዲ መልእክት በማብራራት RealAudioMP3 ፣ ይኽ ቅዱስ ማኅበር እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. ባካሄደው ይፋዊ ጉባኤባወጣው ፍጻሜ ሰነድ መግቢያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡትን አስተምህሮ መሠረት በማድረግ፣ ይህ የ2011 ዓ.ም. ዓዋዲው መልእክት ካህን በቤተ ክርስትያን በቤተ ክርስትያን ሕይወት እና በቲዮሎጊያ አገላለጥ ጥልቅ ትርጉሙ እና ተልእኮ የሚያብራራ መሆኑ የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲፍናል ፒያቸንዛ ዓዋዲ መልእክቱን በይፋ ባቀረቡበት እለት ማብራራታቸው የሚዝከር ነው።

በዚህ በምንኖርበት ዓለም ቤተ ክርስትያን በባህርይዋ ተጋዥ ነች፣ ይኽ ደግሞ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ልኡከ ወንጌላዊነት የቤተ ክርስትያን እውነተኛ እና ጥልቅ ባህርይ መሆኑና የቤት ክርስትያን ኅልውና በገዛ እራሷ ላይ የሚጸና ለገዛ እራስዋ ሳይሆን የኅልውናዋ መሠረት እና ምንጭ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሆኑና እግዚአብሔር ከእኛ ጋር መሆኑ የሚያረጋግጠው ቃል በመጀመሪያ ነበር ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ይኽም ቃል እግዚአብሔር ነበር፣ ሥጋ ለብሶም በመካከላችን አደረ ለሚለው እውነት ምልክት በመሆን በዓለም እና ወደ ዓለም የምትንቀሳቀስ ነች የሚል ሐሳብ የሠፈረበት ዓዋዲ መልእክት መሆኑ ለማወቅ ሲቻል። በዚህ እውነተኛውን ባህል እና ማኅበራዊ ሕይወትን የሚያናጋው ተዛማጅ ባህል እየተስፋፋ ባለበት ዓለም የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. አካሂዶት በነበረው ይፋዊ ጉባኤ የተሳተፉት ብፁዓን ጳጳሳት የቤተ ክርስያን እና የውሉደ ክህነት ተልእኮ በቤተ ክርስትያን ዳግም እንዲታደስ በማመን ካህን ክህነታዊ ጥሪው አለ ፈርቃ በእውነተኛ ሐዋርያነት እየኖረ ልኡከ ወንጌል መሆኑ በመገንዘብ የቤተ ክርስትያን ኵላዊነት ባህርይ ጭምር በሱታፌ እንዲኖር መጠራቱ ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖረው ይገባል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያመለክታል።

የካህን አገልግሎት የግል ሰብአዊ ብቃት የሚያጸናው መርሃ ግብር አማካኝነት ግቡን የሚመታ እና ኵላዊው አንቀጸ ሃይማኖት ብቻ የሚደጋግም ተልእኮ ሳይሆን እውነተኛ ደቀ መዝሙር በመሆን ከሚኖር ሕይወት የሚመነጭ መሆኑ የካህናት ጉዳይ የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ያስተላለፈው ዓዋዲ መልእክት ያብራራል።








All the contents on this site are copyrighted ©.