2011-02-02 15:30:47

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ የአቢያተ ክርስትያን ውህደት


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ዳሪዩስ ኮዋልቺዝክ ዘወትር ማክሰኞች በጣልያንኛ ቋንቋ ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የማይሻሩ ውሳኔዎች በማስደገፍ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላንትና ሁለትኛው የቫቲካን ጉባኤ ኡኒታቲስ ሬዲንተግራዚዮ በሚል ርእሥ ሥር እ.ኤ.አ. ሕዳር 21 ቀን 1964 ዓ.ም. የጸድቀው ስለ አቢያተ ክርስትያን እና የማኅበረ ክርስትያን አንድነት RealAudioMP3 ጉዳይ የሚመለከተው ውሳኔ በማስደገፍ ባቀረቡት የሥርጭት መርሃ ግብር፣ በክርስትያኖች መካከል ያለው ልዩነት የክርስቶስ ፍቃድ እና ፍላጎት የሚቃወም መሆኑ ሁሉም አቢያተ ክርስትያን የሚያምኑበት ጉዳይ ነው። ነገር ግን በተለያየ ምክንያት እየተወገደ ነው። አንድነት እና ውህደት እንዴት ዳግም ለማረጋገጥ ይቻላል የሚል ጥያቄ በማቅረብ፣ ለውህደት የሚደረገው ጥረት የተለያዩ አቢያተ ክርስያን ግብረ ገብ መሠረት በማድረግ የሚያጸድቁት ውሳኔዎች አማካኝነት እጅግ እየተነካ ሂደቱ እና ጥረቱም ጎታታ እና ሊጨበጥ የሚታሰበው የውህደቱ ግብ እንዲርቅ እያደረገ ነው።

ውህደት ሊጨበጥ የማይቻል ነገር ግን ደስ የሚያሰኝ የሥነ ውበት ሀሳብ አድርጎ መመልከት ሳይሆን የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 17 ቁጥር 21 ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ እና በአባቱ መካከል ያለው አንድነት ሱታፌ የሚያደርግ “ሁሉም አንድ እንዲሆኑ” በማለት የጸልየው ጸሎት እግብር ላይ ለማዋል ያቀደም መሆን አለበት። ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እውነት መንገድ እና ሕይወት አንድ እርሱ ብቻ ነው። ስለዚህ አንድ እንዲሆኑ የሚለው ጥሪ ይኸንን የሚያጎላ ሲሆን፣ በውሳኔው ቍጥር ሶስት ድህነት በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብቻ መሆኑ ቢገልጥም፣ አንድ ካቶሊክ ካቶሊክ ካልሆነ ይበልጣል ማለት አይደለም ሲሉ አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.