2011-01-31 14:56:24

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፣ ምን አይነት እና የተኛው ውህደት


የቅድስት መንበር የዜና እና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምት መገባደጃ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ አንቀጽ በመቀጠል ትላንትና በየዓመቱ በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አነሳሽነት እ.ኤ.አ. በጥር ወር የሚካሄደው የአንድ ሳምንት ስለ ክርስትያኖች እንድነት የሚከናወነው የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የሚያሳትፈው የጋራው ጸሎት ርእሰ ጉዳይ በማድረግ፣ የክርስትያኖች አንድነት እንዲረጋገጥ ለሚደረገው የጸሎት ሳምንት የላቲን ሥርዓት የአምልኮ ግፃዌ የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስያን RealAudioMP3 ጳውሎስ ክርስቶስ የተቀበለበት እና የተለወጠበት ዕለት በሚከበርበት ቀን የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ ለዚህ በዓል ዋዜማ ሮማ ፎሪ ለሙራ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተመርቶ በቀረበው የመጀመሪያ የሥርክ ጸሎት በማታወስ፣ ኩላዊት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ክርስቶስ የተመኘው የክርስትያኖች አንድነት እንዲረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ቅድሚያ የሚሰጠው መንፈሳዊ ዓላማ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን ጸሎተ ሠርክ በመምራት ባስተላለፉት መልእክት አቢያተ ክርትያን ለውህደት እንጂ የእርስ በእርስ መከባበር ላይ በሚለው አመለካከት ላይ ብቻ እንዳይረኩ፣ ለአንድነት የሚደረገው የጋራው ጥረት ግቡ ውህደት እንጂ የእስር በርስ መከባበር መቀባበል እንዳልሆነ የሚያሳብ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ አንቀጽ በመጥቀስ፣ መቀባበል እና መከባበር ኅብረአዊነትም አስፈላጊ ነው፣ ሆኖም እነዚህ እሴቶች ውኅደት ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ክርስቶስ የጸሎት ርእሰ ጉዳይ በማድረግ የገለጠው ጥልቅ ፍላጎት የክርስትያኖች ውህደት ነው። ይኽ ውህደት በእምነት በቅዱሳት ምሥጢራት እና በአገልግሎት የሚገለጥ፣ የሚኖር እና የሚመሠከር ነው። ስለዚህ ለውህደት የሚደረገው ጥረት መሪው እና ውህደቱን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ጨለምተኛ ጉዞ መሆን አይችልም፣ መሆንም የለበትም። ከክርስቶስ ጋር ከሚጸናው ከእውነተኛው ግኑኝነት የሚመነጭ አቢይ ጸጋ ነው ካሉ በኋላ፣ ለውህደት የሚደረገው ጥረት በሥነ ውበት ጽንሰ ሃሳብ ላይ የሚቀር ሳይሆን በተጨባጭ ተግባር ለማረጋገጥ ያነጣጠረ መሆን አለበት፣ ስለዚህ የእምነት የቅዱሳት ምሥጢራት የሥነ ቤተ ክርስትያን እና የአገልግሎት ውኅደት ለማረጋገጥ ያለመ መሆን እንዳለበት ቅዱስ አባታችን በመልእክታቸው እንዳብራሩ አባ ሎምባርዲ በማስታወስ ርእሰ አንቀጹን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.