2011-01-31 14:57:35

እውነተኛ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያግዙ ተግባሮች


ባለፈው እሁድ በቅድስት መሬት ሰላም እንዲረጋገጥ በሚል ሃሳብ የተመራ በየዓመቱ የሚከናወነው ዓለም አቀፍ የጸሎት ቀን ባለፈው እሁድ መከናወኑ ሲገለጥ፣ በዚህ ሶስተኛው ዓለም አቀፍ ስለ ቅድስት መሬት ሰላም የጸሎት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ትላትና እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከኢጣሊያ ውስጥ እና ከውጭ የመጡ በብዙ ሺሕ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት RealAudioMP3 ከሓዋርያዊ ሕንፃ መስኮት ሆነው ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከመምራታቸው በፊት ባሰሙት ስብከት፣ ሰላም ምኞች እና ሐሳብ ሆኖ እንዳይቀር እውነተኛ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የሰላም ተግባሮች ያስፈልጋሉ እንዳሉ እለቱን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት በቅድስት መሬት የቅድስት መንበር ቅዱሳት ሥፍራ እና ንብረት አስተዳዳሪ አባ ፒዛባላ በማስታወስ፣ በዚሁ ስለ ቅድስት መሬት ሰላም እንዲረጋገጥ በሚል ሐሳብ ርእሥ ሥር በተካሄደው ጸሎት በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት አምልኮ የምትከተለው ክቶሊክ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ እና ምእመናን በውህደት መሳተፋቸው ገልጠዋል።

ቅድስት መሬት ከላየ ሰማይ በእግዚአብሔር ዓይን እንመለከታት ዘንድ ቅዱስ አባታችን ያቀረቡት የአደራ ጥሪ አባ ፒዛባላ በማስታወስ፣ ይኽ ደግሞ ጸሎትን በማስቀደም የሚረጋገጥ መሆኑ አብራርተው፣ በእግዚአብሔር ዓይን ቅድስት መሬትን መመልከት ማለት ጸሎት፣ ነጻነት፣ መከባበርን፣ ፈራጅ አለ መሆን፣ ቅድመ ፍርድ ከመስጠት መቆጠብ፣ መለወጥን እና በእግዚአብሔር መንፈስ መመራትን በይቅር ባይነት ምኅረት እና መቀባበልን ያመለክታል ብለዋል።

በዚህ አጋጣሚ በሰሜን አፍሪቃ ሕዝባዊ ንቅናቄ እያረጋገጠው ያለው ለውጥ ተስፈኛ እና አሥጊም ነው። ምክንያቱም የሚያረጋገጠው መርሃ ግብር ገና የሚታይ ነውና። ሆኖም በዚያ ክልል የዚህ ዓይነት ሕዝባዊ ንቅናቄ ይመጣል ብሎ ያሰበ ማንም አልነበረም፣ ስለዚህ በዓለማችን ሁሉም የሰውል ልጅ የሚመኘው ለውጥ እና ሰላም ሁሉንም የሚያከብር ሁለ ገባዊ ኅብረአዊነት የሚደግፍ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲከበር የሚያግዝ የሰላም መሠረት የሆነው የሃይማኖት ነጻነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን ተስፈኛ ነኝ በማለት በዚህ ስለ ቅድስት መሬት ሰላም የጸሎት ቀን ስለዚሁ ጉዳይ ጭምር መጸለዩ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.