2011-01-31 14:54:24

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ እምነት እውቀት እና ጥበብ


በፊሊፒንስ ርእሰ ከተማ ማኒላ ከተመሠረተ 400ኛው ዓመት እያከበረ ለሚገኘው ለቅዱስ ቶማስ መንበረ ጠበብ በዓለ ምሥረታው ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመንበረ ጥበቡ የጉባኤ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ወደ ሚገኘው ዓወደ ጥናት በምሥል የተቀረጸ መልእክት ማስተላለፋቸው የቅስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

በዚህ የቅዱስ ቶማስ መንበረ ጥበብ RealAudioMP3 የጉባኤ አድራሽ በመካሄድ ላይ ባለው ዓውደ ጥናት ተማሪዎች እና አስተማሪዎች እንዲሁም የቀድሞ ተማሪዎች አስተማሪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸ ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይህ መንበረ ጥበብ እንዲመሠረት በማድረግ በፊሊፒንስ እውቀት ባህል እና ሕንጸት እንዲነቃቃ ላደረጉት ካህናት እና ደናግል ዓለማውያን ምእመናንን በማመስገን፣ የሃይማኖት ሥነ ምርምር እና በሌሎች የትምህርት ዘርፎች አማካኝነት በቅዱስ ቶማስ መንበረ ጥበብ እምነት እውቀት እና ጥበብ ለፊሊፒንስ ህዝብ የዛሬ 400 ዓመት በፊት የተጀመረው የተሟላ የሕንጸት መርሃ ግብር የሚደነቅ መሆኑ ቅዱስነታቸው እሳቸውን ወክለው በምሥረታው በዓለ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የካቶሊክ ትምህርት የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ዘኖን ግሮቾሎቪስኪ በተገኙበት ባስተላለፉት በምሥል የተቀረጸ መእልክት በመግለጥ፣ የማኒላው ቅዱስ ቶማስ መንበረ ጥበብ በሩቅ ምሥራቅ ክልል የመጀመሪያው የካቶሊክ መንበር ጥበብ መሆኑ ባስተላለፉት መልእክት በመጥቀስ፣ በቤተ ክርስትይን እና በክልሉ ኅብረተሰብ ለተሟላ ሕንጸት አቢይ ሚና ያለው ነው ካሉ በኋላ፣ በእምነት እና በምርምር መካከል ያለው የተሟይነት ግኑኝነት የሚገለጥበት የካቶሊክ መንበረ ጥበብ መሆኑ በማስታወስ፣ መንበረ ጥበቡ የሚሰጠው ሰብአዊ የሥነ ምርምር እና መንፈሳዊ ሕንጸት በመቀጠል ለፊሊፒንስ ሕዝብ ብቻ ሳይሆኑ ለክልሉ ጭምር የተሟላ አቢያ የባህል እድገት እንዲረጋገጥ የሚያደርግ መሆኑ እንዳይዘነጋ አደራ በማለት ቡራኬ መስጠታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.