2011-01-28 15:31:20

ቱርክ፦ እውነት ገሃድ እንዲወጣ


በቱርክ እስከንደሩን ከተማ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ሉዪጂ ፓዶቨዜ እ.ኤ.አ. ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ.ም. በሰው እጅ ለሞት መዳረጋቸው የሚዘከር ሲሆን፣ የግድያው ወንጀል የፈጸመው የግል ሹፌራቸው የቱርክ ዜጋ ሙራት አልቱን በእስር ያለ ቢሆንም፣ ተጠያቂው ላይ እየተደረገ ያለው ምርመራ እምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ በውኑ የሚታወቅ ነገር እንደሌለ አባ ዶመኒኮ በርቶሊ በቱርክ አንዚዮኪያ RealAudioMP3 ለምትገኘው ካቶሊክ ቤት ክርስትያን ቆመስ መግለጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ። ስለዚህ የተፈጸመው የቅትለት ወንጀል የሚያጣራው ፍርድ ቤት እያካሄደው ስላለው ምርመራ እና የደረሰበት የምርመራ እውነተኛ ውጤት ለክልሉ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን እና ምእመናን ማሳወቅ ይኖርበታል እንዳሉ የዜናው አገልግሎት ያመለክታል።

ብፁዕ አቡነ ፓዶቨሰ በቱርክ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሓዋርያዊ እንደራሴ የቱርክ ብፅዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር በመሆን ከ 2004 ዓ.ም. ጀምረው ለሞት እስከተዳረጉበት ዕለት እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስያንን እና በቱርክ ማኅበረ ክርስያን እና የሌሎች ሃይማኖት አባላት ጭምር ያገለገሉ መሆናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ አባ በርቶሊ አክለውም እ.ኤ.አ. ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም የላቲን ሥርዓት አምልኮ ግፃዌ መሠረት የተከበረው ጳውሎስ የተለወጠበት ክርቶስ የተቀበለበት ዓቢይ በዓል በእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን አነሻሽነት በየዓመቱ የክርስትያን አንደት ለመረጋገጥ አልሞ ሁሉም አቢያተ ክርስትያን የሚያካሂዱት የጋራ ጸሎት ሳምንት የተጠናቀቀበት ዕለት መሆኑም ገልጠው፣ ዕለቱ በሁሉም በተለያዩ ሃይማኖቶች እና ማኅበረሰብ የጋራ ሰላማዊ ኑሮ እንዲረጋገጥ የተጸለየበት ነበር ካሉ በኋላ በቱርክ ጠርሴስ እና አንዚዮኪያ የሚጎበኙ ከተለያዩ አገር የሚመጡ ምእመናን ለክልሉ ክርስትያን ማኅበርሰብ አቢይ ድጋፍ ናቸው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.