2011-01-26 14:10:23

ግብረ ገብ እና ክብር በፖለቲካው ሕይወት


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ከተላንትና በስትያ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ቋሚ ምክር ቤት ጉባኤ በንግግር ሲከፍቱ ይህ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ስብሰባ በኢጣሊያ ስላለችው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ርእሰ ጉዳይ የሚወያይ ብቻ ሳይሆን፣ የኢጣሊያ ሃይማኖታዊ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ኤክኖሚያዊ ጉዳይ ጭምር RealAudioMP3 የሚዳስስ መሆኑ በማስታወስ፣ በአሁኑ ወቅት በኢጣሊያ የፖለቲካው መድረክ እየታየ ያለው ግብረ ገብ አልቦ እና ክብር የሚያጎድል ጸባይ በተመለከተ እየተባለ ያለው እና የተጀመረው ጉዳዩን የማጣራት እና የምርመራው ሂደት ባልተወዛገበ እና ጣልቃ ገብነት በሌለው አሠራር በተገቢው ሥፍራ እንዲከናወን አደራ በማለት፣ አክለውም በዓለማችን የሃይማኖት ነጻነት ካለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከበር ጥሪ አቅርበዋል።
በኢጣሊያው የፖለቲካው እና በሕዝባዊ መድረኮች እየታየ ያለው ግብረ ገብ አልቦ ክብርን የሚያንቋሽሽ ተግባር ሥር በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን እየተባለ ያለው ዜና አሳሳቢ መሆኑ በመጥቀስ፣ ተፈጽመዋል የሚባለው ኢግብረ ገባዊ ተግባር በሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ዘንድ ሊጣራ ይገባዋል። ማንም በሕዝባዊ እና በአገር የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊነት የሚረከብ አካል ሥርዓት የተካነው ሕይወት፣ የተሰጠው ሃላፊነት የሚጠይቀው ግብረ ገባዊ መመዘኛ የሚኖር ከተሰጠው ክብር እና ሃልፊነት ጋር የሚስተካከል ሕገ መንግሥት የሚያመለክተው ደንብ የሚጠብቅ ሕይወት ሊከተል ይገባዋ ካሉ በኋላ ተፈጽመዋል የሚባለው ኢግብረ ገብ ተግባር ጉዳዩ በሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ዘንድ ተጣርቶ እውነት ገሃድ ሆኖ እውነት በሕዝብ መታወቅ አለበት ብለዋል።
በመጨረሻውም በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው ጸረ ክርስትያን አመጽ እጅግ አሳሳቢ መሆኑ በመግለጥ፣ ይህ ዘር የማጥፋት ሥልት የሚከተል ጸረ ክርስያን አመጽ በህሉም ዘንድ እንዲወገዝ በማሳሰብ፣ ማኅበረ ክርስትያን የህብረተሰብ ታካይ ክፍል ሳይሆን አንድ ወሳኝ ክፍል ነው፣ የሃይማኖት ነጻነት የሰላም መሠረት መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት መሪ ቃል መሠረት በማድረግ የሁሉም ሃይማኖት ነጻነት መከበር አለበት ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.