2011-01-26 14:09:25

የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት


እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 24 ቀን እስከ መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓ. በአማኞች እና ኢአማኞች መካከል በመቀራረብ ጥልቅ ውይይት የሚደረግበት የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያዘጋጀው ሃይማኖት መብራ እና የጋራ አመክንዮ በሚል ርእስ ሥር ፓሪስ በሚገኘው የዩኔስኮ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የስነ ጥበብና የባህል ድርጅት ዋና ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በአማንያን ሊቃውንት እና ኢአማኒያን ምሁራን መካከል ውይይት እንደሚደረግ የባህል ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ካወጣው መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ RealAudioMP3 መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በሶርቦና መንበረ ጥበብ ቀጥሎም የዚህ የሁለት ቀን ዓውደ ጥናት ውጤት መሠረት በማድረግ ፓሪስ በሚገኘው በደስ በርናንዲንስ ተቋም የክብ ጠረጴዛ ውይይት እንደሚከናወን የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ይጠቁማል።
የሚካሄደው ዓውደ ጥናት መሠረትም ለሁሉም በተለይ ደግሞ ለወጣት የኅብረተሰብ ክፍል ያተኮረ በኖትረ ዳመ ደ ፓሪስ የሰው ልጅ የላቀው እርሱም የአስተዋይነት ባህርዩ የሚያጎላ የሙዚቃ እና በተለያዩ የሥነ ጥበብ ከያንያን የሥነ ቅብ ባለ ሙያዎች የሚያቀርቡት ትርኢት እንደሚቀርብ እና ጸሎት እና አስተንትኖ ጭምር እንደሚከናወንም የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከሰጠው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.