2011-01-26 14:07:56

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እና ድረ መሥክ


45ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያስተላለፉት መልእክት ትላንትና የላቲን ሥርዓተ አምልኮ ግፃዌ የምትከተል እንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የመገናኛ ብዙኃን ጠባቂ የቤተ ክርስትያን ሊቅ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዲ ሳለስ ባከበረችበት ዕለት በይፋ ለንባብ መብቃቱ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ቅዱስ አባታችን እውነት፣ የሕይወት ብሥራት እና ሕጋዊነት በሥነ አኃዝ RealAudioMP3 በተራቀቀው ዘመን በሚል ርእስ ሥር ያስተላለፉት መልእክት፣ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው በድረ መስክ ዘመን ማኅበረ ክርስትያን በታማኝነት እና በተስተዋለ የፈጠራ ችሎት አማካኝነት በመቅረብ መገልገያ መሣሪያው የዕለታዊ ሕይወት ክፍል መሆኑ እንዳይዘነጋው በማሳሰብ፣ ድረ መስክ አዲስ የመገንዘብ እና የማሰብ ሥልት በማረጋገጥ አዲስ ያልተለመደ የግኑኝነት እድል እየፈጠረ መሆኑ አብራርተዋል።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት በማስመልከት ቺቪልታ ካቶሊካ ለተሰየመው መጽሔት የአዘጋጆች ኮሚቴ አባል እየሱሳዊ ካህን አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የድረ መሥክ በተራቀቀው የሥነ አኃዝ ሥር እያረጋገጠው ባለው እድገት አማካኝነት የተለያዩ የመገናኛ የመዋያያ ሐሳብ የሚቀርብበት ገጾች አማካኝነት የሰዎች የግኑኝነት መሆናዊ ባህርይ ላይ እያስከተለው ያለው አቢይ ለውጥ ቅዱስ አባታችን እግምት ውስጥ በማስገባት፣ በዚህ መሣርያ አማካኝነት ሀሳባቸው የሚያቀርቡ፣ መረጃዎች እና ማስታወቂያ ብሎም በዜና መለዋወጥ የሚያደረጉት ግኑኝነቶች ተራ ግኑኝነት ሳይሆን እራሳቸውን እንደሚያስተዋውቁ ያላቸው አመለካከት እና ተስፋ ጭምር የሚያጎሉ ናቸው። ስለዚህ ማኅብረ ክርስትያን በዚህ አዲስ መሣሪያ አማካኝነት የሃይማኖት ጽንሰ ሃሳብ ሳይሆን የሚከተሉ የክርስትና ሕይወት እንዲመሰክሩ መጠራታቸው በጥልቀት አስረድተዋል። ድረ ገጽ በሚገባ መጠቀም ብቻ ሳይሆን የድረ ገጽ ግዜው ጭምር በሚገባ መጠቀም አስፈላጊ ነው። በጥበብ በመጠቀም የሕይወት ትርጉም እውነት ውህደት ለተሰኙት ባጠቃላይ የሰው ልጅ ጥልቅ እና እውነተኛ ፍላጎት መግለጫ መሆን እንዳለበት የሚያብራራ መልእክት ነው ብለዋል።
ሚላኖ በሚገኘው የካቶሊክ መንበረ ጥበብ መምህር የሥነ እደ ጥበብ ሊቅ ፕሮፈሶር ፒየር ቸሳረ ሪቮልተላ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መልእክት መሠረት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የድረ መሥክ እድገት እና ምንጣቄው እጅግ የላቀ ነው። የዚህ መሣሪያ ተጠቃሚው ሰው ከዚህ እድገት ጋር የሚስተካከል ብስለት ያለው መሆን እንዳለበት የሚያሳስብ ነው ካሉ በኋላ፣ ስለዚህ እድገቱ አወንታዊ ጥቅም ያለው ቢሆንም ቅሉ ሊጎዳ እንደሚችል መዘንጋት የለበትም። ድረ ገጽ ተጨባጩን እለታዊ ሕይወታችን የሚያንጸባርቅ እንጂ የኢተጨባጭ ሕይወት የሚኖርበት መድረክ መሆን የለበትም። እውነተኛ መለያ የሚኖርበት እንጂ የሐሰት ሕይወት የሚገነባበት መሣሪያ መሆን እንደሌለበት የሚያሳስብ መልእክት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.