2011-01-26 14:06:36

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለሩሲያው ርእሰ ብሔር የቴሌግራም መልእክት አስተላለፉ


ከትላትና በስትያ በሩሲያ ርእሰ ከተማ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ዶሞደዶቮ የአይሮፖላን ማረፊያ በተጣለው የአሸባሪያን ያጥፍተህ ጥፋ ጥቃት ሳቢያ ሕይወታቸውን ያጡት 35 ሰዎች እና የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ካንድ መቶ አሥር በላይ የሚገመቱትን በማሰብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሩሲያ ርእሰ ብሔር መድቨደቭ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፊርማ የሰፈረበት የሐዘን መግለጫ የቴሌግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር RealAudioMP3 መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉ የጥልቅ ሐዘን መግለጫ የቴሌግራም መልእክት፣ ለሩሲያ ሕዝብ ቅርበታቸውን እና ለሟቾች ቤተሰቦች እግዚአብሔር መጽናናቱን እንዲሰጣቸው በጸሎታቸው እንደሚያስቡዋቸው በማረጋገጥ፣ ለቆሰሉት ጤንነት በመመኘት ብራኬአቸውን አቅርበዋል።
ትላትና በሞስኮ ሊቀ ጳጳስ የእመ አምላክ ሜትሮፖሊታ ብፁዕ አቡነ ፓውሎ ፐዚ ለሞቱት እና ለቆሰሉት እንዲጸለይ ምእመናን በእመ አምላክ ካቴድራል ለጸሎት መጥራታቸው ሲር የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ ብፁዕ አቡነ ፐዚ የተጣለው የአጥፍተህ ጥፋ አደጋ እጅግ የሚያስደነግጥ እና ጥልቅ ሐዘን ማስከተሉንም ገልጠው፣ ማንም በማያስበው እና ባልጠበቀው ሰዓት እና ሁኔታ የሞት አደጋ ሲያጋጥመው በሞታችን ከኛ ጋር ሆኖ የሚሸኘን ማንም የለም ሆኖም ክርስቶስ እንደሚቀበለን እምነታችን ያረጋግጥልናል ካሉ በኋላ በተከሰተው ጥቃት ሳቢያ ሁሉም ለሕይወት ያለው ፍቅር እንዳያጠፋ እና ማንኛውም ዓይነት አመጽ እና ቅትለት መፍትሔ አድርጎ እይዳይመለከት እመ አምላክ ትረዳን ዘንድ በእርሷ አማላጅነት እንጸልይ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.