2011-01-26 14:11:31

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እና የመገናኛ ብዙኃን


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን አባ ዳሪዩስ ኮዋልቺዝክ ዘወትር ማክሰኞች በጣልያንኛ ቋንቋ ስለ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የማይሻሩ ውሳኔዎች በማስደገፍ የጀመሩት የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል ትላንትና ሁለትኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተ ክርስትያን እና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ በተመለከተ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ እ.ኤ.አ. በ 1963 ዓ.ም. ኢንተር ሚሪፊካ - የመገናኛ ብዙኃን RealAudioMP3 መገልገያ መሣሪያዎች በሚል ርእስ ሥር የደነገጉት የጉባኤው የውሳኔ ሰነድ በማስደገፍ፣ የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ በሚገባ ስንገለገልባቸው ለሰው ልጅ ጥቅም እንደሚውሉ በኢንተር ሚሪፊካ ውሳኔ ቁጥር 2 ዘንድ የሰፈረው ሀሳብ በመጥቀስ ካብራሩ በኋላ፣ አክለውም እነዚህ መሣሪያዎች የፈጣሪ እቅድ ለሚቃወም ውድቀት ለምያስከትለው ተግባር መሣሪያ ሊሆኑ እንደሚችሉ እና የሚያስከትለው አደጋ በውሳኔው ተመልክቶ እንደሚገኝ ገልጠዋል።
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፣ ትክክለኛ እና ቅን ኅሊና በመከተል የመገናኛ ብዙኃን መሣሪያ መጠቀሙ አስፈላጊ መሆኑና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የሚሰራጩ ዜናዎች እና የሚቀርቡ መግለጫዎችም ሆነ ማስታወቂያዎች እውነት መሠረት የሚያደርጉ እና የሰውል ልጅ ሰብአዊ መብት እና ፈቃድ እንዲሁም ክብር የሚጠብቅ እና የሚያከብር መሆን አለበት፣ የሰውን ልጅ ልቦና ለመሳብ እና ለመማረክ እየተባለ ሕዋሳት የሚያጠምድ መሣሪያ መሆን የለበትም።
በመብት እና በሥነ ጥበብ መካከል ያለው ግኑኝነት ግብረ ገብ እና ሥነ ምግባር ላይ የጸና መሆን እንዳለበትም ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያሳስባል፣ ስለዚህ የግብረ ገብ ሕግ ይፋዊ ገጽታው በተለይዩ የሰው ልጅ ተግባሮች ላይ የበላይነት አለው። ከግብረ ገብ ሕግ ውጭ የሆነ ሰብአዊ ተግባር ፈጽሞ መኖርም የለበትም፣ ስለዚህ የግብረ ገብ ሕግ በሁሉም ሰብአዊ መስክ መከበር እና መኖር እንዳለበት እና ይኽ ደግሞ ለሰው ልጅ የተሟላ እድገት መሠረት መሆኑ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ያመለክታል። ካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች በጠቅላላ ምእመናን የመገናኛ ብዙሃን በሚገባ ሊገለገሉባቸው ይገባል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.