2011-01-24 13:42:53

ፖርቱጋል፦ የርእሰ ብሔር ምርጫ


71 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የፖርቱጋል ርእሰ ብሔር አኒባለ ካቮኮ ሲልቫ የሥነ ኤኮኖሚ ሊቅ የወግ አጥባቂ የፖለቲካ ርእዮት አንጸባራቂ የርእሰ ብሔር ሥልጣን ተልእኮአቸው አጠናቀው ዳግም እጩ ርእሰ ብሔር በመሆን ለርምጫ ከቀረቡ በኋላ በእጩንት በቀረቡት የሶሻሊስት ርእዮት ተከታይ የሥነ ግጥም ሊቅ ማኑኤል አለግረ በ 53% ድምጽ በመቀድጀ ዳግም ዳግም የፖርቱጋል ርእሰ RealAudioMP3 ብሔር እንዲሆኑ ተመርጠዋል።
ርእሰ ብሔር አኒባለ ካቮኮ ሲልቫ እ.ኤ.አ ከ 1985 እስከ 1995 ዓ.ም. የፖርቱጋል መራሔ መንግሥት ሆነው ማገልገላቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ፖርቱጋል በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኤኮኖሚ ቀውስ እጅግ ከተጠቁት የኤውሮጳ አገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2011 ዓ.ም. የኤክኖሚው ቀውስ በስፋት ሊታይባት እንደሚችል የኤኮኖሚ ሊቃውንት ይናገራሉ። ስለ ፖርቱጋል ወቅታዊ ሁኔታ በማስመልከት የኤውሮጳ ኅብረት የምኅረት በጎ ፈቃድ ማኅበር ሊቀ መንበር አባ ቪቶር መሊሲያስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በፖርቱጋል በሥራ አጥነት ችግር እና በድኽነት የሚጠቁት ብዛት ከቀን ወደ ቀን ከፍ እያለ መሆኑ ገልጠው፣ በሌላው ረገድ እየታየ ያለው ችግር በሕዝቡ መካከል መደጋገፍ መተሳሰብ የመሳሰሉት እሴስቶች እንዲነቃቁ አድርገዋል፣ ቤተ ክርስትያን የአገሪቱ ኅብረተሰብ እና የማኅበራዊ ጉዳይ የሚመለከቱ መዋቅሮች እና ሌሎች የምኅረት የበጎ ፈቃድ ግብረ ሰናይ ማኅበራት ጭምር በኤኮኖሚ ችግር ለተጠቁት አቢይ ድጋፍ እያቀርቡ ናቸው ብለዋል።
በዓለማችን ተከስቶ ያለው የኤክኖሚ ቀውስ ወደ ማኅበራዊ ቀውስ እንዳያዘግም ያሰጋል፣ የዚህ ሁሉ ቀውስ መንስኤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሕይወት ክቡር ዋጋ እና እሴቶች ችላ ማለት መሆኑ ገልጠው። እርሱም ሙስና፣ ከማኅበራዊ ጥቅም ይልቅ በተለያየ ሕገ ወጥ መንገድም ይሁን የግል ጥቅም የማስቀደሙ ሽርጉድ ያስከተለው ችግር ነው፣ ይኸንን መሠረታዊ የኤኮኖሚ ቀውስ መንሰኤ በመለየት ብቻ ነው ተገቢ መፍትሔ የሚገኘው ብለዋል።ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዓለማችን ያለው ችግር መንሰኤ ከማኅበራዊ ሕይወትም ይሆኑ ከኤኮኖሚው መድረክ ሥነ ምግባር ማግለል ያስከተለው መሆኑ የሰጡት ቃል እውነት መሆኑ ለማረጋገጥ ተችለዋል። አለ ሥነ ምግባር እና የሕይወት ክብር ጥበቃ እና እሴቶች ማኅበራዊ ሰብአዊ እና ኤኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ጥረት ባዶ ነው። ስለዚህ ኤውሮጳ ከኤኮኖሚው ቀውስ ለመላቀቅ እሴቶች የሕይወት ክቡር ዋጋ፣ ትብብር መደጋገፍ እና የመተሳሰብ ባህል እንዲሁም የሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ጥበቃ የሚያመለክተው የሥልጣኔዋ መለያ ዳግም ሕያው ማድረግ ይኖርባታል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.