2011-01-24 13:45:10

የካቶሊክ እና የኦርቶዶስ አቢያተ ክርስትያን የጋራ ውይይት


የክርስትያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች እና ለሞስኮ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ሜትሮጶሊታ ሂላሪዮን አልፍየቭ እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን 2011 ዓ.ም. ለሁለቱ RealAudioMP3 አቢያተ ክርስትያን መቀራረብ ያቀደ የጋራ ግኑኝነት በጀርመን ዊይርቡርግ ከተማ እንደሚያካሂዱ ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ይህ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ግኑኝነት ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በሚል ርእስ ሥር ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን፣ የግኑኝነት መርሃ ግብር ያነቃቃው የሚሰቃዩትን አቢያተ ክርስትያን ረዳኤ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ማኅበር መሆኑም ዜኒት የዜና አገልግሎት በመጥቀስ፣ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን የጋራው ግኑኝነት የሮማ አቡን ቀዳሜነት በሚል ጥያቄ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን በር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ጥረት የተጀመረ የጋራው ውይይት ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ የጋራ መልስ ሳያገኝ መቅረቱ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ ርእሰ ጉዳይ ዳግም በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ አሳቢነት ውይይት እንዲደረገበት የቀረበው አወንታዊ ግፊት የሮማ አቡን ቀዳሚነት ውጫዊ ብቻ ሳይሆን ሥነ ቤተ ክርስትያን እና ቲዮሎጊያዊ መሠረት ያለው መሆኑ በመለየት የተለያዩ የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስትያን ውስጣዊ መቀራረብ እና አንድነት እንዲኖራቸው የሚደገፍ የጋራ ውይይት ጭምር መሆኑ ቡፁዕ ካርዲናል ኮች መግለጣቸው ዜኒት የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.