2011-01-24 13:41:28

በዓለ ምሥረታ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የጸጥታ አስከባሪ ኃይል


በቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ሥር የጠቅላይ ጉዳይ ተተኪ አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ፊሎኒ ትላትና በቅድስት ማርያም ዘካምፖ ሳንቶ ለጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ጸጥታ አስከባሪ ኃይል በሚል መጠሪያ የሚታወቀው ዘብ ጠባቂ ኃይል የተመሠረተበት 505 ዓመት ምክንያት ያረገውን መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት ባሰሙት ስብክበት፣ ለጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ ጠባቂ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሰላምታ እና ቡራኬ አቅርበው፣ እግዚብሔር ለሰው ልጅ በተለያዩ ጥሪ አማካኝነት እንዲከተሉት በማድረግ በተልእኮው እንዲተባበሩ ያደርጋል RealAudioMP3 ፣ ካሉ በኋላ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ጸጥታ አስከባሪ ኃይል የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ለማገልገል መጠራታቸውን አስታውሰው፣ በዚህ ጥሪ አማካኝነት በቤተ ክርስትያን ኵላዊ ተልእኮ ተሳታፊዎች በመሆን ለሚሰጡት አግልግሎት ዳግም በታማኝነት እና በአገልግልጎት መንፈስ ጥሪያቸውን እንዲያድሱ መንፈስ ቅዱስ ኃይሉ እና ብርታቱ እንዲሰጣቸው ጸልየዋል።
ከመሥዋዕተ ቅዳሴው በኋላ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ ጠባቂ ኃይል የኦርኬስትራ ባንድ ባቀረበው የሙዚቃ ትርኢት የተሸኘ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ ጠባቂ ኃይል የሰልፍ ትርኢት ማቅረቡ የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ይህ ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ የዘብ ጠባቂው ኃይል እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 1506 ዓ.ም. በር.ሊ.ጳ. ጁሊዮ ሁለተኛ ጥሪ በ 105 የዘብ ጠባቂ ሃይል አባላት አማካኘት አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ከቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር ለመረዳት ሲቻል፣ የዚህ ዘብ ጠባቂ ቃለ መመሪያም ክብር እና ታማኝነት ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሚል ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 6 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ፊት ቃለ ማኅላውን እንደሚያድሱ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.