2011-01-24 13:43:55

ሃይማኖትን እና እምነትን መኖር


በካሪታስ የሚጠራው የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያ የተራድኦ ማኅበር የሮማ ቅርንጫፍ እና የስደተኞች እና ተጓዦች ጉዳይ የሚከታተለው የሮማ ጽ/ቤት በጋራ እዚህ በሮማ የስደተኞች እና የውጭ አገር ዜጎች የእምነት እና ሃይማኖት ነጻነት RealAudioMP3 በተመለከተ የስደተኞች እና የውጭ አገር ዜጎች የአምልኮ መግለጫ ሥፍራ ማውጫ ሰነድ ማቅረቡ ተገለጠ።
በሮማ አውራጃ 256 በሮማ ከተማ ብቻ 208 የስደተኞች እና የውጭ አገር ዜጎች የአምልኮ የጸሎት ሥፍራ እንዳለ ከሰነዱ ለመረዳት ተችለዋል። ሮማ የካቶሊክ እምነት ማእከል በመሆንዋ ይኸንን ጥሪዋ ኵላዊነት ገጽታው በማጉላት የሃይማኖት እና የእምነት ነጻነት በሁሉም ሥፍራ እንዲጠበቅ የማነቃቃት ኃላፊነት አለባት። የሮማ ሰበካ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር እና የስደተኞች ጉዳይ የሚከታተለው ጽ/ቤት አስተባባሪ ፍራንኮ ፒታው በሮማ የውጭ አገር ዜጎች እና የስደተኞች የጸሎት እና የአምልኮ ሥፍራ ማውጫ እ.ኤ.አ. ከ 1998 ዓ.ም. ጀምሮ መታተም እንደጀመረ ገልጠው፣ በሮማ የውጭ አገር ዜጎች ስደተኞች ካለ ምንም ልዩነት የሂንዱ የቡድሃ፣ የአይሁድ የሲክ የምስልምና እና የሌሎች ሃይማኖት ምእመናን ሁሉም እንደ ቋንቋ እምነቱን የሚገልጥበት የአምልኮ እና የጸሎት ብሎም ባህላቸው እምነታቸውን የሚገልጡበት ቅዱስ ሥፍራ አላቸው። እነዚህ የአምልኮ ሥፍራዎች ለጸሎት እና ስግደት ብቻ ሳይሆን የስደተኛው ማኅበረሰብ ማኅበራዊ እንቅስቃሴዎች የሚያከናውንበት፣ ባህላዊ እቅዶች የሚወጥንበት በተስተናገደበተ አገር ተዋህዶ እንዲኖር የሚታገዝበት ሥፍራ ጭምር መሆኑ ገልጠዋል።
በሮማ የቫልደስ ቤተ ክርስትያን መጋቢ አንቶኒዮ አዳሞ በበኩላቸው በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ይህ በካሪታስ የታተመው የስደተኞች እና የውጭ አገር ዜጎች የአምልኮ ሥፍራ ማውጫ በሮማ አውራጃ እና በሮማ ከተማ የሚኖሩት የውጭ አገር ዜጎች እና ስደተኞች የሚከተሉት ሃይማኖት መሠረት ሃይማኖታቸውን የሚገልጡበት የአምልኮ ሥፍራ የሚጠቁም አቢይ ድጋፍ የሚሰጥ ነው። ስለዚህ የስደተኛውም ይሁን የውጭ አገር ዜጋ ሃይማኖታዊ አድማስ ትኩረት መሰጠት እጅግ አስፈላጊ ነው ካሉ በኋላ በተለይ ደግሞ በዚህ ሳምንት ስለ ክርስትያኖች አንድነት የሚጸለይበት ወቅት መሆኑም አስታውሰው ይኸንን ቅዱስ ዓላማ የሚደገፍ አቢይ ውሳኔ ነው ብለዋል።
በዚህ በአሁኑ ወቅት በግብጽ በናይጀሪያ እና በሌሎች የዓለማችን ክፍሎች የተከሰተው እና በመታየት ላይ ያለው የጸረ ክርስትያን አመጽ ጨርሶ እንዲወገድ የሚያነቃቃ ውሳኔ ብቻ ሳይሆን የክርስትናው እምነት ሌላው የሚያስተናግድ መሆኑና የሁሉም ሃይማኖቶች መቀራረብ የሚያነቃቃ ማኅበራዊ ሰላም እንዲኖር የሚቀሰቅስ መሆኑ የሚመሰክር ተግባር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.