2011-01-22 14:44:41

አረብ ሊግ፣ የክስትያኖች እና ሙስሊሞች የጋራው መጻኢ ሕይወት


ሙስሊሞች እና ክርስትያኖች በጋራ የሚኖሩ መሆናቸው የዓለም የሥነ ማኅበራዊ ታርክ የሚያረጋገጠው ተጨባጭ እውነት ነው። ስለዚህ ባለፈውም ቢሆን የወቅቱ እና መጻኢው የጋራው ሕይወት ያለ የማይቀር መሆኑ ሁሉ እማኔው እንዳለው የአረብ ሊግ ዋና ጸሓፊ አምር ሙሳ በሁለቱ ሃይማኖቶች መካከል እና ምእመናኖቻቸው መቀራረብ እና ገንቢ የጋራ ውይይት አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝም መሆኑ RealAudioMP3 ትላንትና የተጀመረው ሁለተኛው የአራብ ኤኮኖሚ እና ማኅበራዊ እድገት ጉባኤ ዋዜማ በቅርቡ የተከሰተው ጸረ ሃይማኖት ጥቃት በማስደገፍ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱ ሎ ሶርቫቶረ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ በመጥቀስ፣ ይህ የአረብ ሊግ የአኮኖሚ እና የማኅበራዊ እድገት ጉዳይ ጉባኤ የሃይማኖት ነጻነት ርእሰ ጉዳይ በማድረግ ይፋዊ ውይይት ሲያካሂድ ይህ ትላትና የተጀመረው ጉባኤ የመጀመሪያ መሆኑ የቅድስት መንበር ጋዜጣ ያስታውሳል።

ዋና ጸሓፊ አምር ሙሳ፣ ሁሉም አረቦች አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት አንድነት እንዲኖራቸው ጥሪ በማቅረብ፣ ጉባኤው አመጽ የሚለው ቃል እና ተግባር በማኅበራዊ ሥነ ፍች መሠረት በመወያየት በዓለማችን እያንሰራፋ ያለው የሃይማኖት ፀንፈኛነት እና አሸባሪነት እንዴት ማስወገድ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ጥረት የሚያደርግ ጉባኤ መሆኑ እንዳሰመሩበት ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ ያመለክታል።

በአረብ አገሮች በአንድ የሃይማኖት ማኅበረሰብ ላይ የሚጣለው ጥቃት ካለ ምንም ውጫዊ ጣልቃ ገብነት ጥቃቱ በተጣለበተ አረብ አገር ውስጥ መፍትሔ እንዲያገኝ ማኅበራዊ፣ ፖሊቲካዊ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ውይይት ሊደረግበት እና ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት መፍትሔ መቀየስ ያስፈልጋል እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ አስታወቀ።

የአረብ ሊግ ዋና ጸሓፊ አምር ሙሳ እ.ኤ.አ ጥቅምት 31 ቀን 2010 ዓ.ም. በኢራቅ ርእሰ ከተማ ባግዳድ በካቶሊክ ረዳኢተ ኵሉ ቅድስተ ማርያም ካቴድራል አሸባሪያን የፈጸሙት ጥቃት ምክንያት እና ሰለባ የሆኑትን ለመዘከር ለክልሉ ሕዝብ ቅርበታቸውን ለመግለጥ ይፍዊ ጉብኝት በማካሄድ ከክልሉ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች ጋር በመገናኘት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት አስፈላጊ ነው እንዳሉና ከዚህ ይፋዊ ጉብኝት ቀደም በማድረግ በግብጽ ይፋዊ ጉብኝት በማካሄድ የእስክንድሪያ ፓትሪያርክ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ርእሰ ሲኖዶስ ሸኑዳ ሶስተኛ ጋር በመገናኘት በክልሉ አሸባሪያን በሰነዘሩት ጥቃት ሰለባ የሆኑትን በማሰብ ቅርበታቸው እና ድጋፋቸውን እንዳረጋገጡ የቅድስት መንበረ ዕለታዊ ጋዜጣ ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.