2011-01-19 15:41:00

የክርስያኖች አንድነት እንዲረጋገጥ


ሁሌ በየዓመቱ በሁሉም ካቶሊክ አቢያተ ክርስትያን በክርስትያኖች መካከል እና እንዲሁም በአቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው ልዩነት እንዲወገድ እና የክርስትያኖች አንድነት እንዲረጋገጥ ታልሞ ለክርስትያኖች አንድነት መረጋገጥ ሐሳብ በማድረግ የሚከናወነው የጸሎት ሳምንት ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2011 ዓ.ም. እንደሚከናወን RealAudioMP3 ሲር የዜና አገልግሎት በማሳወቅ፣ በቅድስት መሬት እየሩሳሌም ከተማ በቅዱስ መቃብር ባሲሊካ እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በመካከለኛው ምሥራቅ ስለ ክርስትያኖች አንድነት የሚደረገው የጸሎት ሥነ ስርዓታ እንደሚጀመር የዜናው አገልግሎት ያመለክታል።

የክልሉ ማኅበረ ክርስያን የሁሉም ክርስያኖች አንድነት ያልነበረ ሳይሆን የነበረ ነገር ግን ልዩነቱ ቀጥሎ የመጣ ታሪክ ሲሆን፣ ቀጥሎ የመጣው ልዩነት ተወግዶ ጥንታዊው የክርስትያን አንድነት እና ውህደት ዳግም እውን እንዲሁም ይኽ እንዲረጋገጥ እንደሚጸልይ ሲር የዜና አገልግሎት ሲያመለክት። ስለ ክርስትያኖች አንድነት የጸሎት ሥነ ስርዓት በቅዱስ መቃብር ባሲሊካ ከኦርስቶዶስ ቤተ ክርስያን ጋር በጋራ በመጸለይ ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በብሥራተ ገብርኤል የግሪክ ካቶሊካዊት ቤተ ርክስትያን ጥር 24 ቀን 2011 ዓ.ም. በቅዱስ ዣከስ ጥር 25 ቀን በሉተራን መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስትያን ጥር 26 ቀን የላቲን ሥርዓት በምትከተለው መድኃኔ ዓለም የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ጥር 27 ቀን በጎልጎታ ቅዱስ ሥፍራ፣ ጥር 28 ቀን በቅዱስ ማርቆስ የሶሪያ ሥርዓት የምትከተለው ኦርቶዶስክ ቤተ ክርስትያን፣ ጥሪ 29 ቀን በኢትዮጵያዊት ኦርስቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጥሪ 30 ቀን በቅዱስ ጎዮርጊስ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካቴድራል ስለ ውህደት በሚደረገው የጋራ ጸሎት እንደሚጠናቀቅ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.