2011-01-19 15:37:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የክርስትና እምነት የመቀበል ጥሪ ዳግም ማነቃቃት


ከተመሠረተ ካርባ ዓመት በላይ የሆነው በነዮካተኩመናለ-አዲስ ንኡሳነ ክርስትያን በሚል ሥም የሚጠራው የክርስትና ሕይወት የመቀበሉ ጥሪ የክርስትና እምነት ከተቀብሉት በኋላም ዕለት በዕለት ጥሪውን እንደ ቀደምት ማኅበረ ክርስትያን መኖር፣ ግብረ ሐዋርትያት ምዕራፍ 4 ከቁጥር 32 እስከ ቁጥር 34 “የመጀመሪያ አማኞች ሁሉ አንድ ልብና አንድ አሳብ ነበራቸው፣ ማንም ሰው ይህ የእኔ ነው የሚለው ነገር አልነበረውም፣ በመካከላቸው ሁሉ ነገር የጋራ ነበር፣ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኅይል ይመሰክሩ ነበር። መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን ያመጡ ስለ ነበር በመካከላቸው አንድም ችግረኛ አልነበረም። ገንዘቡንም አምጥተው ለሐዋርያት ይስረክቡ ነበር። RealAudioMP3 ለእያንዳንዱ እንድ አስፈላጊነቱ ይታደል ነበር። የሚለውን የመጀመሪያ ማኅበረ ክርስትያን የኅብረት ኑሮ በቅዱሳት ሚሥጢራት በኩል የማኅበረ ክርስትያን አባል ከተሆነ በኋላ ይኸንን የክርስትናውን ሕይወት ዕለት በዕለት ልክ ገና እንደተቀበልከው በማሰብ ኅያውነቱን መኖር እና መመስከር የሚለው ከመንፈስ ቅዱስ የተሰጠውን መንፈሳዊ ዓላማ መርህ በማድረግ በኪኮ አርጉአሎ የተቋቋመው ዓለማውያን ምእመናን እና ገዳማውያን እንዲሁም የመንፈሳውያን ማኅበር አባላት ካህናት እና ደናግል ጭምር በአባልነት የሚገኙበት ማኅበር መሥራች እንዲሁም የማኅበሩ ተባባሪ መሥራቾች ካርመን ሄርናንደስ እና አባ ማሪዮ ፐዚ እና ሌሎች ከ 46 አገሮች የተወጣጡ ወደ ዓለም ሂዱ ወንጌልን ስበኩ የሚለው ወደ አሕዛብ የሚያነቃቃ ተልእኮ በመቀበል ወንጌላዊ አገልግሎት ለመፈጸም የሚላኩት 230 የዚህ ማህበር አባላት ከትላትና በስትያ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 አቀባበል ተደርጎላቸው መሪ ቃል እንደተቀበሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን እነዚህ የነዮካተኵመን አባላት እና መንፈሳዊ መሪዎች በቫቲካን ጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው በሰጡት መሪ ቃል፣ ቤተ ክርስትያን ገና ወዳልደረሰችበት ሥፍራ እያንዳንዱ የቤተ ክርስትያን አባል በዚያ ሥፍራ ተገኝቶ ወንጌልን ሲያበሥር በቤተ ክርስትያን ሥም የሚያቀርበው ስብከተ ወንጌል በመሆኑም፣ የቤተ ክርስትያን ኅልውና እና ኅያው ምስክርነት ነው ስለዚህ፣ ወንጌልን ስናበስር በቤተ ክርስትያን ከቤተ ክርስትያን መሆናችን እንዳይዘነጋ አደራ በማለት፣ የሚላከው በእራሱ፣ ገዛ እራሱን የሚልክ ሳይሆን የሚላክ የተልእኮ ጥሪ የሚቀበል ነው። ወደ አሕዛብ በመሄድ ወንጌልን መመስከር ሁሉም የክርስቶስ ተከታይ ማድረግ የሁሉም ማኅበረ ክርስትያን አባል ኃላፊነት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የነዮካተኩመናለ ማኅበር መሥራች ኪኮ አርጉኤሎ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ወደ አለም ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ የሚለው ወንገላዊ ጥሪ የክርስትያኖች ማኅበረሰብአዊ ተልእኮ ነው። ልኡካነ ወንጌል የካህናት እጥረት ወዳለበት ክልል እና አገር የሚላኩ ወንገላውያን የቤተ ክርስትያን ልጆች ናቸው። ቅዱስ አባታችን ለነዚህ ልኡካነ ወንጌል የሰጡት መሪ ቃል የክርስትና እምነት የሚያከትለው ከፍቅር የሚመነጭ ኃላፊነተ እና ተልእኮ በጥልቀት ያስገነዘበ ነበር ብለዋል።

የሚላከው ገዛ እራሱ የሚልክ ሳይሆን ለዚህ ተልእኮ የተገባ የሚያደርገው ቅድመ ዝግጅት እና ሕንጸት ያስፈልገዋል፣ ስለዚህ በዚሁ ጉዳይ ላይ ቤተ ክርስትያን የተሟሉ ልኡካን እንድንሆን በእርሷ ስም የምንላክ በመሆናችንም ሕንጸቱ በመስጠት ሁሉ ለዚህ ተልእኮ ዝግጁ እንዲሆን ታነቃቃለች የጥሪው ኃላፊነት በይፋ ታስረክባለች እውቅና ትሰጣለች፣ ማኅበረ ክርስትያ ለማነጽ በቤተ ክርስትያን ሥር መነጽ ወሳኝ ነው። አለ ቤተ ክርስትያን ተልእኮ የለም ስለዚህ ቅዱስ አባታችን በሰጡት አስተምህሮ እና መሪ ቃል ይኸንን የተልእኮ ሥነ ቤተ ክርስትያናዊ መልኵ በጥልቀት እንዳስረዱ ኪኮ አርጉኤሎ በመግለጥ ይኸንን ተልእኮ በይፋ የተቀበሉት 230 ቤተሰቦች በሚሥጢረ ተክሊል አንድ የሆኑት ባል እና ሚስት የሆኑትን ያጠቃለለ መሆኑ ገልጠው፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ይህ ባህላዊ የቤተሰብ ጥላ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ለአደጋ ተጋልጦ ቤተሰብ ተበታትኖ ተነጣጥለው በመፋታት የተወለዱ ሕፃናት ለማኅበራዊ ሰብአዊ እና ሥነ አእምሮአዊ ችግር በስፋት በተጋለጡበት በአሁኑ ወቅት ወንጌል በባለ ትዳሮች አማካኝነት እንዲስፋፋ ማድረግ አቢይ ትርጉም አለው። ቤተሰብ ማለት ምን ማለት መሆኑ በጥልቀት ይመሰከራል የቅድስት ቤተ ሰብ መንፈሳዊነት በመኖር በኤውሮጳ እና በሌሎች በበለጸጉት አገሮች እና በማደግ ላይ ወደ ሚገኙት አገሮች እየተዛመተ ያለው የግለኝነት ኑሮ በወጣቱ ኅብረተሰብ ዘንድ እየተስፋፋ ያለው አለ ትዳር የመኖር ምርጫ፣ አለ ጥሪ፣ ጥሪህን ሳትለይ በተነዳ ሕይወት የመኖሩ ሂደት እና ይኽ ምርጫ የሚያስከትለው ችግር እንዲወገድ ምን መደረግ እንዳለበት ለሚለው ጥያቄ ወንጌልን በልኡካነ ወንጌል ቤተሰብ በማዳረስ ተግባራዊ መልስ የሚቀርብበት ትልቅ ኃላፊነት ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.