2011-01-19 15:39:06

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ፦ በቤተ ክርስትያን እና በፖለቲካው ዓለም መካከል ያለው ግንኙነት


በቫቲካን ረዲዮ ኢየሱሳዊ ካህን የሥነ ሲንዶስ ሊቅ አባ ዳሪዩስ ኮዋልችዝይክ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በማስመልከት አንዴ በሳምንት በዕለተ ማክሰኞ የሚያሰራጩት አስተምህሮ በመቀጠል ትላትና ሐሴት እና ተስፋ በተሰኘው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ዘንድ፣ በቤተ ርክስትያን እና በፖለቲካው ዓለም መካከል ያለው ግንኙነት በሁለተኛው የቫቲካን ውሳኔዎች ሥር ምን እንደሚመስል በጥልቀት መተንተናቸው ሲታወቅ። አባ ኮዋልችዝይክ ካህን ወንጌላዊ ልኡክ ከፖለቲካው ዓለም የራቀ መሆን አለበት ወይ ለሚለው ጥያቄ፣ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ሕገ ቀኖና አንቀጽ 287 በመጥቀስ ሲመልሱ ካህን የማንም የፖለቲካ ሰልፍ ንቁ አባል እና የተለያዩ የፖለቲካ ሰልፍ RealAudioMP3 መሪ ወይንም የሠራተኛ ማኅበራት ተጠሪ እና አባል መሆን የለበት ማለት እንጂ ስለ ፖለቲካ ግንዛቤ እንዳይኖረው የሚል ወይንም የቤተ ርክስትያን የማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት በማስደገፍ በዓለም የሚታየው ፖለቲካዊ ሂደት በመተንተ አስተያይት መሰጠት የለበትም የሚለው ዘወትር የሚሰማው ሐሳብ እንደማያመለክት ገልጠዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በጋውዲዩም ኤት ስፐስ ሐሴት እና ተስፋ በተሰየመው ውሳኔው ቁጥር 76 በመጥቀስ፣ ቤተ ክርስትያን ከማንም የፖለቲካ ሰልፍ ወይንም የፖለቲካ ማኅበረሰብ ጋር ገዛ እራስዋን የማታደናግር ከማንም የፖለቲካ ሥልት ጋር የተቆራኘች እንዳልሆነች በግልጽ የተብራራ ነው ብለዋል።

በሌላው ረገድ በቁጥር 76 በመቀጠል ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በጋውዲዩም ኤት ስፐስ ውሳኔው አማካኝነት፣ የፖለቲካው ማኅበርሰብ እና ቤተ ርክስትያን ልኡላውያን ናቸው አንዱ በሌላው ላይ ተጽእኖ አያደርግም፣ ሆኖም ግን የፖለቲካው ዓለምም ይሆኑ ቤተ ክርስትያን ለሕዝብ የሚያገለግሉ ናቸው። ምእመናን ከቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ትምህርት ጉዳይ በማይጻረረ መንገድ የተለያዩ የፖለቲካ ስለፍ አባላት እና መሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ።

በአሁኑ ወቅት በስፋት የሚታየው ችግር የካህናት ፖሊቲከኛ መሆን ሳይሆን ክርስትያን የፖለቲካ አባላት በቁጥር ከቀን ወደ ቀን ማነስ እያለም እስከ አለ መኖር እየተደረሰ ያለው ጉዳይ ነው። ስለዚህ የክርስትያን ፖሊቲከኞች መጥፋት ነው አቢይ ችግር ሆኖ ያለው። ዓለማውያን ምእመናን እራሳቸውን ከፖለቲካው ዓለም ማግለል እንደሌለባቸው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔዎች ያስገነዝባሉ፣ ለቤተ ክርስትያን እምነት እና ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተምህሮ እንዲሁም በጠቅላላ ከቤተ ክርስትያን ማኅበራዊ ጉዳይ ትምህርት እና ለተቀበሉት የእምነት ጸጋ ታማኞች በመሆን በፖለቲካው ዓለም ሊሳተፉ እንደሚገባቸው በጋውዲዩም ኤት ስፐስ ተመልክቶ ይገኛል። ስለዚህ በፖለቲካው ዓለም የሚሳተፍ ክርስትያን ክርስትያናዊ ኅሊናውን መከተል ይኖርበታል፣ ይኸንን የቤተ ክርስትያን ትምህርት የሚከተሉ የፖለቲካ አካላት በተለያዩ ብሔራዊ፣ ክፍለ ዓለማዊ እና ዓለም አቀፋዊ መድረክ እንዲኖሩ አስፈላጊ ነው በማለት ለዕለቱ ማክሰኞ ያቀርቡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.