2011-01-17 14:17:48

ቤተ ክርስትያን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሁሉም ወዳጅ


በኢጣሊያ የጀኖቫ ከተማ ሊቀ ጳጳስ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ትላንትና እሁድ ጆኖቫ በሚገኘው በቅዱስ ሎርረንዞ ካቲድራል ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ዕለቱ የእንተ RealAudioMP3 ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ዓለም አቀፍ 97ኛው የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ቀን መሆኑ በማስታወስ፣ ቤተ ክርስትያን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሁሉም ወዳጅ ነች በማለት አማኝ ምእመንም የዚህ ተግባር ተከታይ ነው ብለዋል።

በዓለም ሰላም ብልጽግና እና መረጋገት እውን እንዲሆን ቤተ ክርስትያን ትላንትና ዛሬም ያልታከተ ጥረት እንደሚታደርግ ገልጠው፣ የነገው ዓለም ሰላም ብልጽግና እና መረጋጋት የተካነ እደሚሆን ያላትን ተስፋ በክርስቶስ ላይ በማጽናት የነገው ዓለም ጭምር ሰላም ብልጽግና እና መረጋጋት የሰፈነበት እንዲሆን ከወዲሁ በተለያዩ መዋቅሮችዋ አማካኝነት ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚትገኝ ገልጠው። ሁሉም የውይይት የመቀራረብ የመከባበር እና የመቀባበል ባህል እንዲያጎለብት አለ ምንም ልዩነት እንደምታንጽ ገልጠው፣ የተለያዩ ሃይማቶች መቀራረብ መግባባት የሰላም መሠረት ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.