2011-01-17 14:16:16

ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሄር አገልጋይ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ውሳኔ መሠረት ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን 2011 ዓ.ም. ብፅዕና እንደሚታወጅላቸው በቅርቡ በቅድስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል ካሰራጨው መግለጫ ለማወቅ ሲቻል፣ ሁሌ በየዓመት ከሁሉም አገሮች የተወጣጡ ወጣቶችን በማሰባሰብ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አስተምህሮ RealAudioMP3 ምክር፣ የሚለገስበት የተለያዩ መንፈሳዊ እና ባህላዊ መርሃ ግብር የሚረጋገጥበት በጠቅላላ እምነት የሚመሰከርበት ኵላዊነት ቤተ ክርስትያን የምታዘጋጀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እቅድ መሠረት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የዘንድሮው 26ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በስፐይን ርእሰ ከተማ ማድሪድ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 16 ቀን እስከ ነሓሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. እንዲካሄድ መወሰናቸው የሚዘከር ሲሆን፣ ለዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቅድመ ዝግጅት ለማጠናቀቅ የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ርይልኮ የማድሪድ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ሩዎኮ ቫረላ ተመርቶ እ.ኤ.አ. ከ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በማድሪድ ክፍለ ከተማ ኤስኮሪያል ሲካሄድ የሰነበተው ስብሰባ ባለፈው ቅዳሜ ጥሪ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. የዓለማውያን ምእመናን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ስታኒስላው ርይልኮ ከ 84 አገሮች የተወጣጡ የፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ልኡካን እንዲሁም ከተለያዩ 44 የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን እንቅስቃሴዎች የተወጣጡ ልኡካን ያሰባሰበው ጉባኤ በንግግር ሲዘጉ ር.ሊ.ጳ. የእግዚአብሔር አገልጋይ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የዚህ በማድሪድ የቅዱስ ሐዋርያት ጳውሎስ ወደ ቆላስያስ በጻፈው መልዕክት ምዕራፍ 2 ቁጥር 7 “በክርስቶስ ጸንታችሁ እና ተመሥርታችሁ በእምነት ጽኑዎች ሁኑ” በሚለው ቃል ተመርቶ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የዘንድሮው 26ኛው ዓለም አቀፍ የቀጣቶች ቀን ጠባቂ እንደሚሆኑ በይፋ ማሳወቃቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.