2011-01-17 14:14:49

ሊቀ ጳጳስ ብፅዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ፦ አንድ ሰብአዊ ቤተ-ሰብ


ትላንትና እሁድ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እኩለ ቀን የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ስብከት፣ ዕለቱ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ቀን መሆኑ በማስታወስ ስለ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች መጸለያቸው ሲገለጥ፣ በር.ሊ.ጳ. ፒዮስ አሥረኛ እ.ኤ.አ. በ 1914 ዓ.ም አንድ ብሎ የጀመረው በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሚታሰበው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፈናቃዮች ቀን መሠረት ዘንድሮ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን የሚታሰበው 97ኛው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ተፍናቃዮች ቀን “አንድ ሰብአዊ ቤተ-ሰብ” RealAudioMP3 የሚል ቃል እንዲመራ ቅዱስ አባታችን መወሰናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ የስደተኞች እና የተጓዞች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶኖዮ ማሪያ ቨሊዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በተባበሩት መንግሥታት የቅርቡ አኃዛዊ የማረጋገጫ ሰነድ በዓለም የመኖርያ ፈቃድ ያላቸው ሕጋውያን የሚባሉ በጠቅላላ 214 ሚሊዮን እና ሌሎች ከ 15 እስከ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመንግሥታት የስደተኞች ማስተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሕገ ወጥ ስደተኞች ተብለው የሚገለጡ መኖራቸው ጠቅሰው፣ በዚህ ላይ ሌሎች 15 ሚሊዮን ተፈናቃዮ ዜጎች አሉ ካሉ በኋላ፣ በአገሮቻቸው ውስጥ የሚኖሩ ብዛታቸው እጅግ ከፍ ያለ ስደተኞች ያሉ ቢሆንም ቅሉ፣ በዚህ በተሰጠው አኃዛዊ መግለጫ ዘንድ ያልተጠቀሱ መሆናቸው አብራርተው፣ በሰብአዊ መብት እና ፈቃድ ረገጣ እና ከሌሎች የተለያዩ አመጽ በማምለጥ በስደተኛነት የሚኖሩ ወደ 27 ሚሊዮን የሚጠጉ መሆናቸው እና በብዛት ከአፍሪቃ ሰሃራ በታች ከሚገኙት አገሮች፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከደቡባዊ ምሥራቅ እስያ፣ ከላቲን አሜሪካ አገሮች የመጡ ብዙ ስደተኞች እንዳሉ ብፁዕነታቸው በማስታወስ፣ ስደት ኅብረተ-ሰብአዊ ክስተት የነበረ እና ያለ ነው። በትክክል እና በሚገባ ሰብአዊነት ማእከል ባደረገ እቅድ ማስተዳዳሩ የሁሉም አገሮች ኃላፊነት ነው። ጦርነት አመጽ ድኽነት እርሃብ የአካባቢ ብከላ ወዘተ በመሳሰሉት ችግሮች ተገደው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተለያዩ አገሮች የሚስደዱት ሕዝቦች መብት እና ፍቃድ መሠረታዊ ፍላጎት ዋስትና መስጠት የሁሉም ጥሪ ነው።

ከምሥራቅ አፍሪቃ በተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ተገደው ወደ ምዕራብ ዓለም ለመግባት አቅደው የሚጓዙት የሚያጋጥማቸው ዘግናኝ ችግር ለማንም የተሰወረ አይደለም፣ ሰዎች በሕገ ወጥ መንገድ ከቦታ ቦታ በሚያንቀሳቅሱት የወንጀል ቡድኖች እጅ ሥት እየወደቁ ያለባቸው ዘርፈ ብዙ ችግር እየባሰ ለሞት አደጋ የሚጋለጡት የሞት አደጋ የደረሰባቸው ብዙ ናቸው። እነዚህ ስደተኞች ለመገመቱ በሚያዳግት አደገኛ ጉዞ ምዕራብ ዓለም ገብተው ሲያበቁ፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው ዋስትና ከምሰጠት ይልቅ የሕገ ወጥ ስደተኞች እየተባሉ ወደ መጡበት መሸኘት ለሚለው የጸጥታ እና ደህንነት ጥበቃ ሕግ መሠረት በድጋሚ ለከፋ አደጋ የሚጋለጡ ብዙ ናቸው። የኤውሮጳ ኅብረት ያወገዘው ወሳኔ ሆኖ እያለ በአንዳንድ የኤውሮጳ ኅብረት አባል አገሮች ገቢራዊ ሲሆን ማየቱ ግን እጅግ ያሳዝናል ብለዋል።

ዓለምዊነት በሥፋት እየተረጋገጠበት ባለበት ዓለም፣ የሰው ልጅ እንቅስቃሴ መገደቡ ተገቢ አይደለም። ሃይማኖታዊ ባህላዊ ኤኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ ልዩነት ሳይገድበው ዓለማችን ወደ ኅብረአዊነት እያዘገመ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ባስተላለፉት ዓለም አቀፍ የሰላም መልእክት ሁሉም አንድ ቤተሰብ መሆኑና ይህ በባህል በሃይማኖት እና በተለያዩ ማኅበራዊ ሕይወት መግለጫዎች አማካኝነት የተለያየው ሕዝብ የሚያዋህደው ሰብአዊነቱ ተበክሮ ከዚህ አቢይ ክብር በሚመነጭ መከባበር መቀባበል የሚሉት እሴቶች የተረጋገጠበት ዓለም ማነጽ የሁሉም በተለይ ደግሞ የመንግሥታት ኃላፊነት መሆኑ ገልጠዋል። ቤተ ክርስትያን ይኸንን መሠረታዊ ምክንያት እና ሐዋርያዊ ጥሪዋ አማካኝነት መቼም ቢሆን የምትከተለው መመሪያም ነው። መመሪያ የቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ፍትህ እኵልነት ሰላም የተረጋገጠበት ዓለም ለማነጽ አስፈላጊ ነው። ቅዱስ አባታችን በመልእክቱ የተፈጥሮ ሃብት ለሁሉም የሰው ልጅ የታደለ የሁሉም የጋራ ጸጋ ነው። ስለዚህ በእኵል ለሁሉም ሕዝብ እንዲዳረስ በማሳሰብ፣ በማደግ ላይ የሚገኙት አገሮች የዚህ የተፈጥሮ ሃብት ጸጋ ባለ ቤት ሆነው ከተጠቃሚነቱ ግን ተገለው የሚገኙት በጠቅላላ በድኽነት ሥር ላሉት አገሮች መሠረታዊ ድጋፍ እና ትብብር ተደርጎላቸው የብልጽግና ተካፋይ እንዲሆኑ የበለጸጉ አገሮችን ድጋፍ አደራ በማለት ያስተላለፉት ጥሪ ብፅዕ አቡነ አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በመጥቀስ፣ ለስደት እና ለመፈናቀል የሚዳርጉት ችግሮች መፍትሔ ማፈላለግ የሁሉም መንግሥታት ተቀዳሚ ዓላም ይሆን ዘንድ አሳስበዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.