2011-01-14 14:38:41

የኤውሮጳ እና የሰሜን አመሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት


በመካከለኛው ምሥራቅ የገዳማውያን እና ልኡካነ ወንጌል እንቅስቃሴ ነጻነት፣ በእስራኤል እና በቅድስት መንበር መካከል የጋራው ግኑኝነት ብሎም በእስራኤል እና ፍልስጥኤም መካከል የተሟላ ቅን የሰላም ስምምነት ይደረስ ዘንድ፣ በቅድስት መሬት RealAudioMP3 የኤውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ የጋራው ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳይ የሚንከባከብ በመካከለኛው ምሥራቅ ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን ተንከባካቢ ድርገት በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊክ ቤት ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ኣቡነ ፉኣድ ታዋል ጋር በመገናኘት እ.ኤ.አ. ጥር 8 ቀን 2011 ዓ.ም. የጀመረው ሓዋርያዊ ጉብኝት ትላትና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም. ማጠናቀቁ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የኤውሮጳ እና የሰሜን አሜሪካ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፣ ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ጉዳይ እና በመካከለኛው ምሥራቅ ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን ተንከባካቢ የጋራው ድርገት በሐዋርያዊ ጉብኝቱ ፍጻሜ ካወጣው የጋራ መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው፣ በክልሉ ያለው ፍራት ቂም በቀል አለ መተማመን የመሳሰሉት በጠቅላላ ጸረ ሰላም የሆነውን ባህል ከፍትህ የሚመነጭ ሰላም አማካኝነት ብቻ እንደሚወገድ እና ይኸንን ሰላም ለሚያነቃቁት ትብብር እና ድጋፍ እንደሚያቀርቡ በመግለጥ በቅድስት መንበር እና በእስራኤል መካከል ያለው ግኑኝነት እያስገኘው ያለው አመርቂ ውጤት በመጥቀስ፣ በክልሉ ለያይ አጥር ሳይሆን ለሰላም የሚበጅ አገናኝ ድልድይ አስፈላጊ መሆኑ አስምረውበታል።

ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ከፍልስጥኤም መራሔ መንግሥት ሳላም ፋያድ ጋር በመገናኘት የፍልስጥኤም የተለያዩ የፖለቲካ አካላት ለክልሉ ሰላም ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉ አደራ በማለት እስራኤል እና ፍልስጥኤም ፍትሐዊ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችሉት ውሳኔዎች ለማቅረብ ይተጉ ዘንድ ሲያሳስቡ፣ ሁለት ልኡላውያን አገሮች ምሥረታ ለሰላም እና ለጸጥታ ብሎም ለደህንነት መሠረት መሆኑ ባወጡት የፍጻሜ ሰነድ በማመልከት፣ በመጨረሻም የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ገዳማውያን ወንጌላውያን ልኡካን ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ለመግባት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የሚሰጠው የይለፍ ፈቃድ የመንቀሳቀስ ነጻነትን የሚገታ መሆኑ በመግለጥም የክልሉ ማኅበረ ክርስትያን የተጋረጠበት ዘርፈ ብዙ ችግር እንዲወገድ ከሚያግዙት ውስጥ አንዱ የሚሰጣቸው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት መሆኑ ብፁዓን ጳጳሳት በመግለጥ፣ ይህ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ሁሉም ተግቶ እንዲጸልይ በማሳሰብ፣ እግዚአብሔር የመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝብ እንዲባርክ በመማጠን የጋራ መግለጫውን ሰነድ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.