2011-01-14 14:37:20

ኵላዊት ቤተ ክርስትያን፦ ለሃይቲ ሕዝብ


እ.ኤ.አ. ጥር 12 ቀን 2010 ዓ.ም. በሃይቲ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሰለባ የሆኑትን ለመዘከር በቅድስት መንበር የሃይቲ ልኡከ መንግሥት መሥዋዕተ ቅዳሴ እንዲቀርብ ያቀረቡት ሃሳብ መሠረት በቅድስት መንበር እና በኢጣሊያ የተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት የተሳተፉበት ሮማ በሚገኘው ር.ሊ. ጳጳሳዊ ባሲሊካ ሳንታ ማሪያ ማጆረ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ መሥዋዕተ RealAudioMP3 ቅዳሴ ማቅረባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ ባሰሙት ስብከት፣ የእግዚአብሔር ቃል ትልቅ ጥልቅ አጽናኝ በእያንዳንዱ ሰው ልጅ ልብ ውስጥ የእምነት የጽናት ምንጭ መሆኑ ጠቅሰው፣ የዛሬ አንድ ዓመት በሃይቲ ተከስቶ በነበረው ርእደ መሬት ሳቢያ 220 ሺሕ ሰዎች የሞት አደጋ እንዳጋጠማቸው እና በደረሰው አሰቃቂው ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ሳቢያም 500 ሺሕ ሕጻናት የሚገኙባቸው በጠቅላላ አንድ ሚሊዮን የሚገመተው የአገሪቱ ዜጋ ለከፋ ችግር መጋለጡ እና ባለፉት ወራት በተከሰተው የወረርሽኝ በሽታ ሳቢያ በሺዎች የሚገመቱት ጭምር ለሞት አደጋ መጋለጣቸው በማስታወስ፣ የእግዚአብሔር ቃል ሥጋችን ለብሶ በመካከላችን የተገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጽናናቱን ይሰጠናል። ሞት ምንም’ኳ የስቃይ ምክንያት ባህርይ ያለው ቢሆንም ቅሉ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ እና በትንሣኤው በኃጢኣት እና በሞት ላይ ድል በመንሳቱ የሞትን ኃይል በማሸነፍ ዘለአለማዊ ሕይወት በሞት ሥር የሚምበረከክ እንዳልሆነ አረጋግጦልናል እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

የቤተሰብ አባላትን ንብረቱ በጥቅላላ ያለውን ሁሉ በማጣት በሃዘን ላይ ለወደቀው ለሃይቲ ተወዳጁ ሕዝብ ከሁሉም የቤተ ክርስትያን ልጆች ድጋፍ እና ትብብር በተለይ ደግሞ ያንድ አባት ልጆች ከመሆናችን የሚመነጨው ሙሉ ድጋፍ የተረጋገጠ ነው። ይኽ ትብብር አደጋው በተከሰተበት ማግሥት በነበረው ጊዜ የሚታጠር ሳይሆን፣ እቅድ እና ተግባር ሆኖ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የሃይቲ ሕዝብ አገሩ ዳግም ታንጻ ቤቱን ያጣው ተገቢ መኖሪያ ቤት አግኝቶ ለመኖር በተስፋ እየጠበቀ ነው። ርእደ መሬት በረግጥ በሰው ሕይወት ላይ ከባድ ጉዳይ በንብረት ላይ ጭምር ለመገመቱ የሚያዳግት ውድመት አስከትለዋል፣ ቢሆንም ግን ከሰው ልጅ ልብ እውነተኛውን ፍቅር የሚያወድም የሚደልዝ ማንም ኃይል የለም፣ ይህ ፍቅር የተስፋ መሠረት ነው ካሉ በኋላ ቅድስት ድንግል ማርያም የሃይቲ ሕዝብ በእግዚአብሔር ላይ ያለው እምነቱን እንዲጠብቅ ዕለታዊ ኑሮው ዳግም በማነጽ በቁሳዊ ዳግመ ግንባታው ላይ ብቻ ሳያተኩር ግላዊ እና ማኅበራዊ ሕይወቱን በማነጽ መንፈሳዊ ሕንጸት ላይ ያተኵር ዘንድ ትደግፈው እና ታበረታታው ዘንድ ድጋፉን እና ብርታቱን ታማልድ ዘንድ መጸለያቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ለሃይቲ ሕዝብ ድጋፍ እና ለአገሪቱ ዳግመ ግንባት የሚቀርበው ድጋፍ እና ትብብር የሚያቀነባበረው ጳጳሳዊ የውሁደ ልብ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ሮበርት ሳራሕ ለሃይቲ ሕዝብ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ድጋፍ ትብብር እና ቅርበት በቅዱስነታቸው ጸሎት ዘወትር የሚዘከሩ መሆንቸውንም ለማረጋገጥ እና የቅዱስነታቸው መልእክት እና ቡራኬ ጭምር ለማስተላለፍ ብሎም ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር ስለ አገሪቱ ሁኔታ በመነጋገር የሃይቲ ሕዝብ ለማዳመጥ እና አብሮ በርእደ መሬት ሳቢያ ሰለባ የሆኑትን ለማሰብ መሥዋዕተ ቅዳሴ በማቅረብ የእንተ ላእለ ኵሉ ቤተ ክርስትያን ቅርበት በማረጋገጥ እየቀረበ ያለው ድጋፍ እና ትብብር ሂደቱንም ለመገምገም እ.ኤ.አ. ከጥር 10 ቀን 2011 ዓ.ም. በሃይቲ የጀመሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ቅድስት መንበር መመለሳቸው የቅስት መንበር የዜና እና የኅትመት ክፍል ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.